ስፑትኒክ ኢትዮጵያ Telegram channel photo

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

@sputnik_ethiopiaPublic Channel

ያልተነገረውን እንነግርዎታለን ስለ አፍሪካ በእንግሊዘኛ ቋንቋ፤ @sputnik_africa

168

Last views

52k (51,981 subscribers)
Membros
—
Rating
115
Total Posts
Oct 20, 2026, 2:38 AM
Atualizado
Mar 25, 2026
Created
Stats

Você está vendo conteúdo em português. Para ver conteúdo em outros idiomas, mude o idioma do site.

Channel Information

Channel Information
Channel Nameስፑትኒክ ኢትዮጵያ
Username@sputnik_ethiopia
CategoryNotícias do Mundo
Languageportuguês
CountryBrasil
Membros51,981
Channel TypePublic Channel
Created25 de mar. de 2026
Last Updated20 de out. de 2026 • há 3 dias
StatusActive

Classificação

Classificação Global
#232022-57
Classificação por Idioma
#5163-3
Classificação por Categoria
#1715-3

Crescimento de Participantes

Total: 52.0K30 Days growth: -3310.6%
09/2009/2509/3010/0510/1010/1510/19
Crescimento de Participantes - 30 Days
DateSubscribers
20:09:202652,312
21:09:202652,312
22:09:202652,312
23:09:202652,312
24:09:202652,406
25:09:202652,406
26:09:202652,406
27:09:202652,406
28:09:202652,406
29:09:202652,406
30:09:202652,406
01:10:202652,406
02:10:202652,406
03:10:202652,406
04:10:202652,406
05:10:202652,406
06:10:202652,406
07:10:202652,406
08:10:202652,406
09:10:202652,406
10:10:202652,406
11:10:202652,406
12:10:202652,016
13:10:202652,016
14:10:202652,016
15:10:202652,016
16:10:202652,016
17:10:202652,016
18:10:202652,016
19:10:202651,981
Crescimento de Participantes - Weekly
DateSubscribers
Week of 23:03:202642,350
Week of 30:03:202642,874
Week of 06:04:202643,706
Week of 13:04:202645,103
Week of 20:04:202645,510
Week of 27:04:202645,510
Week of 04:05:202646,111
Week of 11:05:202646,111
Week of 18:05:202646,111
Week of 25:05:202646,884
Week of 01:06:202646,884
Week of 08:06:202646,649
Week of 15:06:202646,649
Week of 22:06:202646,954
Week of 29:06:202646,954
Week of 06:07:202646,954
Week of 13:07:202648,241
Week of 20:07:202649,192
Week of 27:07:202649,619
Week of 03:08:202649,619
Week of 10:08:202650,570
Week of 17:08:202650,570
Week of 24:08:202651,191
Week of 31:08:202651,953
Week of 07:09:202651,953
Week of 14:09:202652,312
Week of 21:09:202652,406
Week of 28:09:202652,406
Week of 05:10:202652,406
Week of 12:10:202652,016
Week of 19:10:202651,981
Crescimento de Participantes - Monthly
DateSubscribers
March 202642,350
April 202645,510
May 202646,884
June 202646,954
July 202649,619
August 202651,191
September 202652,406
October 202651,981
Crescimento de Participantes - Yearly
DateSubscribers
202651,981

Top 10 posts

Most viewed posts from this channel

By views
  1. #1#viral | አውቶቡሱ ምን ሆኖ ነው?3.1K
  2. #2🇪🇹 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በናይጄሪያ ባዬልሳ የየናጎአ ሲቲ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድርን በድል 3.0K
  3. #3የሩሲያ ጦር የ "ግራድ" ባለቡዙ ሮኬት ተኳሽ ቡድኖች የዩክሬን ጦር ምሽግ እና የሰው ኃይሎችን ደመሰሱ - የሩሲ3.0K
  4. #4#viral |በመሃል ከተማ የተደረገው የ"ቱር ደ ግመል" ሽምጥ ግልቢያ2.9K
  5. #5#Viral | የዓመቱ ደማቅ ተወርዋሪ ባለ ጅራት ኮከብ በፀሐይ ተዋጠ2.9K
  6. #6ጥንታዊቷ የሐረር ከተማ በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ጉባኤ ላይ በደማቁ ተዘከረች2.8K
  7. #7በሰርቢያን ከበሃንጋሪ በሚያገናኝ እና የሩሲያን ጋዝ በያዘ ቧንቧ ማስተላለፊያ አቅራቢያ ቦምብ ተገኘ2.8K
  8. #8እስራኤል በቤሩት ደቡባዊ የከተማ ዳርቻዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ተዘገበ2.8K
  9. #9🇷🇺 አንዳንድ ተንታኞች የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት መዘዝ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ሊነጻጸር እንደሚችል 2.7K
  10. #10የኢትዮጵያ ባሕላዊ መድኃኒቶች ወደ ፋብሪካ ምርት ሊሸጋገሩ ነው2.7K

Últimos Posts

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 17:56

Video
19 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ በቀዶ ህክምና ተወገደ

ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ከሴቶች የመራቢያ አካል ክፍል የሚነሳ ነው የተባለ እጢን፤ ዕድሜዋ 40 ዓመት ከሆነ የአራት ልጆች እናት በስኬት አስወግዷል።

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
168000
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 17:39

Photo1/2
የፑቲን እና ዊትኮፍ ውይይት ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ ዙሪያ እውነተኛ የሰላም ፍላጎት እንዳላት ያረጋገጠ ነው - ሱዳናዊ ባለሙያ

🕊 በሩሲያ ፕሬዚዳንት እና በአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ መካከል የተካሄደው የቅርብ ጊዜ ውይይት፤ ሞስኮ ለሰላም የምታደርገውን ወጥ የሆነ ጥሪ በተግባር ያስቀጠለ ነው ሲሉ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ባለሙያው አህመድ ባህር ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ባለሙያው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

⚡️ የአውሮፓ ጣልቃ ገብነት፦ ሩሲያ ለሰላም ያላትን ፍላጎት ስታሳይ፤ አውሮፓ እና የዩክሬን ውይይቱን ለማስቀየስ "ከእውነት የራቁ ሰበቦችን" እየጠቀሱ እና የአውሮፓ ኅብረትም በሚያደርገው ወታደራዊ ድጋፍ ግጭቱን እያራዘመ ይገኛል።

⚡️ የአሜሪካ የአቋም ለውጥ፦ ዋሽንግተን ሩሲያ ሁልጊዜም ግጭቶችን የማስቆም ፍላጎት እንዳላት በመጨረሻም ተገንዝባለች። ከውይይቱ በኋላ ዊትኮፍ የሰጡት መግለጫ የአሜሪካን አዎንታዊ አቋም የሚያሳይ ነው።

⚡️ የለውጥ ተስፋ፦ የሱዳኑ ፖለቲከኛ ይህ የውይይት ምዕራፍ አዳዲስ ስኬቶችን ያመጣል የሚል ተስፋቸውን ገልጸዋል።

⚡️ ዓለም አቀፋዊ ዐውድ፦ ጉብኝቱ በተለይም ከአውሮፓ ፖለቲካዊ ፈተናዎች እና ከመካከለኛው ምስራቅ ቀውሶች አኳያ ግጭቱን ለማስቆም ወሳኝ ምልክት ሰጥቷል።

ሩሲያ ከአሜሪካ እና ከዩክሬን ጋር የሚደረገውን የሦስትዮሽ ውይይት በህዳር ወር መጀመሪያ ለመቀጠል ዝግጁ መሆኗን ክሬምሊን ትናንት አስታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
353000
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 17:22

Photo1/2
የሩሲያና የቻይናን የሕግ ትብብር የላቀ ደረጃ የሚያደርስ ሁሉን አቀፍ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል — የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰብሳቢ 🇷🇺🇨🇳 ኢጎር ክራስኖቭ ይህን ያሉት ከቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የፍትሕ ሚኒስትር ሄ ሮንግ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው። በውይይቱ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ 🔹 የሩሲያና የቻይና ግንኙነት በቭላድሚር ፑቲንና ሺ ጂንፒንግ መሪነት ጠንካራ መሠረት ያለውና በፍጥነት እያደገ…
479001
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 17:04

Video
❗️ የሩሲያን የናፍጣ ነዳጅ የጫነ የመጀመሪያው መርከብ ዛሬ ወደ አሜሪካ ጉዞ ይጀምራል —የሩሲያ ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛ ኪሪል ዲሚትሪየቭ የመጀመሪያው ጭነት 40 ሺህ ቶን የናፍጣ ነዳጅ እንደሚይዝና መደበኛ አቅርቦት እንዲጀመር መንገድ እንደሚከፍት የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ ተናግረዋል። ይህ የሩሲያ የነዳጅ ኤክስፖርት መስከረም 29 በቭላድሚር ፑቲንና በዶናልድ ትራምፕ መካከል…
672002
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 16:52

Video
ቤኒን፣ ጋና እና ሩዋንዳ የዲጂታል መታወቂያ ማረጋገጫ ሥርዓት ዘረጉ

ሦስቱ ሀገራት ከስማርት አፍሪካ የመረጃ ልውውጥ ጋር የመጀመሪያ ደረጃ ትስስር መፍጠራቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ይህም የመረጃ ሉዓላዊነት እና ደህንነትን በጠበቀ መልኩ መረጃዎችን እንዲጋሩ እና እንዲያረጋግጡ ያስችላቸዋል ሲል የስማርት አፍሪካ ሴክሬተሪያት አስታውቋል።

በዚህ የሙከራ ፕሮጀክት አማካኝነት የመንገደኞች ማንነት በሀገራቸው ይፋዊ መዝገብ መሠረት የሚረጋገጥ ሲሆን ይህም በአውሮፕላን ማረፊያ አውቶማቲክ በሮች ላይ የሚደረጉ ፍተሻዎችን ያቃልላል ሲል ሴክሬተሪያቱ አብራርቷል።

🔍ለምን አስፈላጊ ሆነ?

ይህ ተነሳሽነት የአፍሪካ ሀገራት በብሔራዊ መረጃዎቻቸው ላይ ያላቸውን ቁጥጥር እንደጠበቁ የተሳሰረ የዲጂታል ኢኮኖሚ እንዴት መገንባት እንደሚችሉ የሚያሳይ ነው ሲሉ የሴክሬተሪያቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ላሲና ኮኔ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
698002
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 16:40

Photo1/2
ሩሲያ በምዕራብ ዩክሬን የምትሰነዝራቸው ጥቃቶች የአውሮፓ የአየር መከላከያ መሽመድመድን ያጋለጡ ናቸው - ባለሙያ

የሩሲያ ወታደራዊ ባለሙያ አሌክሴይ ሊዮንኮቭ ለስፑትኒክ እንደተናገሩት፤ ሩሲያ የባሊስቲክ ሚሳኤል እና የድሮን ጥቃቶቿን ወደ ምዕራብ ዩክሬን ያዞረችው፤ አካባቢው የጦር መሣሪያዎች የሚቀርቡበት እንዲሁም ሚሳኤሎች እና ድሮኖች የሚገጣጠሙበት ብቸኛ ስፍራ በመሆኑ ነው።

በምዕራብ ዩክሬን፤ “አንዳንድ የገበያ ማዕከላት የሲቪል ተቋም መስለው የተሠሩ ቢሆኑም የመገጣጠሚያ ቦታዎች ሲሆኑ፤ ሥራ ያቆሙ ፋብሪካዎችም ወደ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ጥገና ማዕከልነት እየተቀየሩ ይገኛሉ። በተጨማሪም ሌሎች በርካታ ቦታዎች በጦር ግንባር ለሚገኙ የዩክሬን ኃይሎች የሎጂስቲክስ ድጋፍ ለመስጠት ሊያገለግሉ ይችላሉ።”

እንደ ሊዮንኮቭ ገለጻ፤ የዘለንስኪ አስተዳደር እነዚህን አካባቢዎች ከሩሲያ ጥቃቶች ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ችግሮች ይገጥሙታል።

“ኪየቭ ከአውሮፓ የቀረቡላትን የአየር መከላከያ ሥርዓቶች ወደ ምዕራብ ዩክሬን በፍጥነት እያጓጓዘች ትገኛለች፤ አንዳንዶቹ የአጭር ርቀት መከላከያዎች ከተመረቱበት ፋብሪካ በቀጥታ እንደተላኩ ተዘግቧል። ነገር ግን የሩሲያ ጥቃቶች ወደ ከፍተኛ የድሮን እና ሚሳኤል ድበደባ እየተቀየሩ በመምጣታቸው እነዚህ አየር መከላከያዎች ጥቃቶቹን በብቃት ማከሸፍ አይችሉም።”

የሩሲያ ኃይሎች በቅርቡ በምዕራብ ዩክሬን ሮቭኖ ክልል የሚገኘውን ኤፒሴንተር-ኬ ሎጂስቲክስ ማዕከል መምታታቸው፤ ሩሲያ ከዩክሬን ወታደራዊ ጥቅም ጋር የተያያዙ ሁሉንም መሠረተ ልማቶች ለማውደም የምትከተለውን ስትራቴጂ አጠናክራ ለመቀጠል ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ሲሉ ባለሙያው ደምድመዋል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
763001
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 16:20

Video
#viral | በቻይና በአየር ላይ ተንጠልጥላ የነበረች ህጻን ተረፈች

እናትየዋ ለገበያ በወጣችበት ወቅት ከ12ኛ ፎቅ የውጭ የብረት ፍርግርግ ላይ ሾልካ የተንጠለጠለች አንዲት የሦስት ዓመት ህፃን ልጅ ልትተርፍ ችላለች።

ጀግኖች ጎረቤቶቿ የእሳት አደጋ ሠራተኞች ደርሰው እስኪያድኗት ድረስ ህፃኗን በወንበር አየር ላይ ደግፈው በመያዛቸው፤ ህፃኗ ምንም ዓይነት ጭረት ሳይደርስባት ህይወቷ ሊተርፍ ችሏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
835007
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 15:38

Video
❗️ የሩሲያን የናፍጣ ነዳጅ የጫነ የመጀመሪያው መርከብ ዛሬ ወደ አሜሪካ ጉዞ ይጀምራል —የሩሲያ ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛ ኪሪል ዲሚትሪየቭ

የመጀመሪያው ጭነት 40 ሺህ ቶን የናፍጣ ነዳጅ እንደሚይዝና መደበኛ አቅርቦት እንዲጀመር መንገድ እንደሚከፍት የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ ተናግረዋል።

ይህ የሩሲያ የነዳጅ ኤክስፖርት መስከረም 29 በቭላድሚር ፑቲንና በዶናልድ ትራምፕ መካከል በተደረገ የስልክ ውይይት የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የመጣ ነው።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት የሩሲያ የናፍጣ ነዳጅ ወደ አሜሪካ እንዲገባ ጊዜያዊ አጠቃላይ ፈቃድ ያወጣ ሲሆን ፈቃዱ እ.አ.አ እስከ ሚያዝያ 2027 ድረስ ይቆያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,100009
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 15:21

Video
በዓለም የአሣ ምግቦች ገበያ የአፍሪካ ድርሻ 2% ብቻ ነው - የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን

🌍 በአፍሪካ ኅብረት የእንስሳት ሀብት ቢሮ እና በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ ሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ጥበቃ መምሪያ የተዘጋጀው የዓሣ ሀብት አስተዳደር ፕሮጀክት ሁለተኛ ምዕራፍ ማጠቃለያ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

🗣 በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ ሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቭላካቲ፤ አሣ ከ200 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ አፍሪካውያን የፕሮቲን እና የዋና ዋና አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች እና ቫይታሚኖች ምንጭ ሆኖ እንደሚያገልግል ጠቅሰዋል።

“ሆኖም በአኅጉራችን የውኃ ውስጥ ምግቦች ፍጆታ በነፍስ ወከፍ 9 ኪሎግራም ብቻ ሲሆን ይህም ከዓለም አቀፉ አማካይ 20.7 ኪሎግራም አንጻር ሲታይ በጣም ዝቅተኛውና ከግማሽ ያነሰ ነው” ብለዋል።

✅ ስብሰባው የፕሮጀክቱን ውጤቶችና የተቀሰሙ ትምህርቶችን እንደሚገመግም፣ ስለ ዘላቂነቱ እንደሚመክር እንዲሁም የዘላቂ ዓሣ ሀብት እና የውኃ ኃብቶች ልማት እሴት ሰንሰለት የሸግግር መርኃ-ግብር ላይ እንደሚወያይ የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ገልጿል።

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,130003
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 15:02

Video
የስፑትኒክ አፍሪካ ቢሮ በሩሲያውያን ሙዚቀኞች ቅኝት

🎺 የሩሲያ የጃዝ ሙዚቀኞች ስቬትላና ኮኖቫሎቫ፣ ቪዮሌታ ጉሊዬቫ፣ አሊና ባራኖቫ እና ጋጂ ራማዛኖቭ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የሩሲያ ጃዝ ሳምንት አዲስ አበባ ይገኛሉ።

ሙዚቀኞቹ በሞሰብ የባሕል ማዕከል፣ በፈንድቃ እና በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ ታዋቂ የጃዝ ሙዚቃዎችንና በጃዝ ዘይቤ የተቀናበሩ ተወዳጅ ዘፈኖችን ለታዳሚዎች አቅርበዋል።

🗓 ነገ 11 ሰዓት ሥራዎቻቸውን በህፃናትና ወጣቶች የቴአትር እና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ያቀርባሉ።

🇪🇹🇷🇺 ሩሲያውያኑ ሙዚቀኞች የስፑትኒክ አፍሪካን ቢሮ በጎበኙበት ወቅት፤ ስለ ሙዚቃ ሕይወታቸው፣ ወደ ኢትዮጵያ ስላመጣቸው ፕሮጀክት እና ሩሲያና ኢትዮጵያ በሙዚቃ አማካይነት የባሕል ልውውጣቸውን እንዴት ማጠናከር እንደሚችሉ ሃሳባቸውን አጋርተዋል።

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,290006
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 14:13

Video
የትግራይ ክልል ሕዝብ ዓይኑን ጨፍኖ የሚተኛበት ቀን መምጣት አለበት - የተመድ ዋና ተጠሪና የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ

​አዚኤል ኤጄሎ የትግራይ ክልልን ለስድስት ወራት እንዲያስተዳድር በቅርቡ በፌደራል መንግሥት ኃላፊነት ከተቀበለው የባለአደራ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሰፋ አብረሃ ጋር በክልሉ የጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

🇺🇳🇪🇹 ተጠሪው ከውይይቱ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ተመድ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጎን እንደሚቆም በመግለጽ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሰላም፣ መረጋጋት እና መልሶ ግንባታ ጥረቶችን እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

“ኢትዮጵያ ትልቅ ለውጥ ልታስመዘግብ የተቃረበችበት ወሳኝ ወቅት ላይ ትገኛለች፤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚካሄዱት ሌሎች የትጥቅ ግጭቶችም ማብቃት አለባቸው።”

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,3600012
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 13:46

Photo1/2
ዘለንስኪ በአሜሪካ ጫና የግዛት ጥያቄውን ለመተዉ ተስማምቷል - ስዊዲናዊ ወታደራዊ ባለሙያ

ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ዩክሬን በአሜሪካ የደህንነት መረጃ እና በስታርሊንክ ላይ ምን ያህል ጥገኛ እንደሆነች በመረዳቱ፤ አሁን ምክንያታዊ የሆነ አቋም መያዝ ጀምሯል ሲሉ የስዊድን የጦር ኃይሎች እና የአየር መከላከያ የቀድሞ አባል ሚካኤል ቫልተርሰን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

"ዘለንስኪ አሁን በሩሲያ እጅ የሚገኘውን 25% የዩክሬን ግዛት ሕጋዊ የሩሲያ አካል የሚያደርግ መፍትሔ ሊቀበል እንደሚችል ተናግረዋል" ሲሉ ተንታኙ ገልጸዋል።

በአሜሪካ፣ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለው የዲፕሎማሲ ግንኙነት በጥቅምት ወር ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። ወሩ በሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና በአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ መካከል በተደረገ የናፍጣ ስምምነት ተጀምሮ፤ በመቀጠልም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሩሲያ ላይ አዳዲስ ማዕቀቦችን ከመጣል የተቆጠቡበት እንደነበር ቫልተርሰን አንስተዋል።

"አሁን ዘለንስኪም ሆኑ አውሮፓ የአሜሪካ ጫና እንደተሰማቸው ሲያውቁ፤ ትራምፕ የዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ በቀላሉ ሊገኝ ይችላል በሚል የድርድር ተነሳሽነቱን ለመውሰድ እየሞከሩ ነው" ሲሉ ባለሙያው አከለዋል።

ሆኖም የትኛውም ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት ሁሉን አቀፍ መሆን እና ለግጭቱን ስረ-መንስኤዎች መፍትሔ መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል። ዩክሬን በአውሮፓ ድጋፍ ወደፊት በሚመጣ የአሜሪካ አስተዳደር ስር ከሩሲያ ጋር ዳግም ጦርነት ልትጀምር ትችላለች ሲሉም ያስጠነቅቃሉ።

"አሁን በሚደርግ ስምምነት ሁሉም ነገር መፍትሔ ካገኘ፤ ዩክሬን እንደ ወራሪ የመታየት ስጋት ስለሚኖርባት እና የምታገኘው የውጭ ድጋፍ በጣም አነስተኛ ስለሚሆን ዳግም ግጭት ለመጀመር በጣም ይከብዳታል" ሲሉ ደምድመዋል።

ዘለንስኪ፤ ዩክሬን ከግጭቱ በፊት የነበራትን 75% የሚሆነውን ግዛት ይዛ እንድትቀጥል የሚያስችለውን ዕቅድ ለመቀበል ፈቃደኛ እንደሆነ ቀደም ሲል ገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,310006
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 13:14

Photo1/2
የጋና ፕሬዚዳንት ሩሲያ በሳኀል ቀጣና ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ የምትጫወተውን ሚና እንደሚያደንቁ ገለጹ

“በዚህ ጉዳይ ላይ ያለኝ አመለካከት፤ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ቁርጠኛ የሆነ ማንኛውንም አካል በደስታ እንቀበላለን የሚል ነው” ሲሉ ጆን ድራማኒ ማሃማ በለንደን በተካሄደው የፋይናንሻል ታይምስ አፍሪካ ጉባዔ ስለ ሩሲያ የደህንነት ተሳትፎ አስተያየት ሰጥተዋል።

የምዕራብ አፍሪካን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለማቋቋም የታቀደው ዕቅድ የዘገየው፤ ተመድ ለሥራው የሚያስፈልገውን የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል ውሳኔ እስካሁን ሳይሰጥ በመቅረቱ እንደሆነ ማሃማ መጠቆማቸውንም ሚዲያዎች ዘግበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,310004
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 13:04

Video
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰበ

📈 ይህ የተገለጸው የከተማ አስተዳደሩ በመሠረታዊ የዕለት ተዕለት ፍጆታዎችና በቤት ኪራይ ላይ እየታዩ ያሉ ምክንያታዊ ያልሆኑ የዋጋ ጭማሪዎችን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ነው።

አስተዳደሩ ችግሩን ለመፍታትና ፍትሐዊ የገበያ ሥርዓት ለማረጋገጥ እርምጃ መውሰድ መጀመሩንም ገልጿል።

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,270003
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 12:54

Video
አስተማማኝ የመረጃ እና የስታቲስቲክስ ስርዓት መገንባት ለአፍሪካ ዘላቂ ዕድገት ወሳኝ ነው - ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

ፕሬዚዳንቱ ጥሪውን ያቀረቡት ረቡዕ አዲስ አበባ ውስጥ ተካሄዶ በነበረው 10ኛው የአፍሪካ የስታቲስቲክስ ኮሚሽን ጉባኤ እና 12ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ጂኦስፓሻል መረጃ አስተዳደር ክልላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነው።

የርዕሰ ብሔሩ ጥሪዎች፦

▪️ የአፍሪካ ሀገራት ብሔራዊ የስታቲስቲክስ ስርዓቶቻቸውን እንዲያጠናክሩ፣
▪️ የይፋዊ መረጃዎችን ገለልተኝነት እንዲጠብቁ፣
▪️ የልማት ፖሊሲዎቻቸውን በሚታመኑ መረጃዎች ላይ እንዲመሰርቱ።

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሥራ አስፈጻሚ ክላቨር ጋቴቴ በበኩላቸው፤ አፍሪካ ለዘመናዊ የስታቲስቲክስ መሠረተ ልማቶች ግንባታ እና ለመረጃዎች ጥራት ትኩረት እንድትሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,130002
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 12:39

Photo1/2
ሞስኮ እና ቤጂንግ የሕግ ዘርፍ ትስስራቸውን አጠናከሩ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኃላፊ ኢጎር ክራስኖቭ እና የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዣንግ ጁን የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ የሕግ ትስስር ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር አዲስ የትብብር ስምምነት መፈራረማቸውን የስፑትኒክ ዘጋቢ ዘግቧል። እንደ ክራስኖቭ ገለጻ፤ ሰነዱ ትኩረት የሚያደርግባቸው ጉዳዮች፡- ◻️ እያደገ የመጣውን…
1,130005
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 12:02

Video
ስፑትኒክ በአካባቢያዊ ቋንቋዎች ስርጭት መጀመሩ የምዕራባውያንን የበላይነት ለሚጋፈጡ ሕዝቦች ትልቅ ዕድል ነው - የዘርፉ ባለሙያ 📌 የሚዲያ ተቋሙ ተደራሽነቱን በማስፋት በደቡባ አፍሪካ እና ታንዛኒያ አዲስ የዜና ማሠራጫ ማዕከላት መክፈቱን በተመለከት ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን የሰጡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና የሥነ-ተግባቦት መምህር መኩሪያ መካሻ፤ መረጃ የጦርነት ግንባር በሆነበት…
1,210002
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 11:21

Photo1/2
ግብፅ በቱርክና በሊቢያ መካከል የተደረገውን የባሕር ወሰን ስምምነት ሕጋዊነት የለውም ስትል ውድቅ አደረገች

🇪🇬 በሊቢያና በቱርክ መካከል የተደረገው የባሕር ወሰን ስምምነት፤ ግብፅ በራሷ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንና በአኅጉራዊ የባሕር ወለል ላይ ያላትን ሉዓላዊ መብት የሚጥስ ነው ሲል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ሚኒስቴሩ የስምምነቱ መጽደቅ በግብፅ ላይ ምንም ዓይነት ሕጋዊ ውጤት እንደማያስከትልም አስታውቋል።

ስምምነቱ እ.ኤ.አ በ1982 የወጣውን የተባበሩት መንግሥታት የባሕር ሕግ ስምምነት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የፍትሕና ርትዕ መርሆችን የሚጥስ መሆኑን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

🇱🇾🇹🇷 መግለጫው የሊቢያ ብሔራዊ የስምምነት መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ስምምነቱን በአንድ ድምፅ ማጽደቁን ተከትሎ የመጣ ነው። ምክር ቤቱ ቀደም ሲል ስምምነቱን በመቃወም ከአንካራ ጋር ያለውን የፖለቲካ ግንኙነት ለማቋረጥ ያስላለፋቸውን ውሳኔዎችም ሽሯል።

የመግባቢያ ስምምነቱ መጀመሪያ የተፈረመው እ.ኤ.አ ጥቅምት 2019 በወቅቱ የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት ፋይዝ አል-ሰራጅና በቱርክ መካከል ነበር።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,380005
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 11:15

Photo1/2
የሩሲያ የናፍጣ ስምምነት ሞስኮ ወጥ በሆነ መንገድ የዓለም የነዳጅ ገበያ አረጋጊ እንደሆነች ያሳያል - የምጣኔ ሀብት ባለሙያ

🇷🇺🇺🇸 ሩሲያ እና አሜሪካ በቅርቡ የደረሱት የናፍጣ ስምምነት ትክክለኛ የኢነርጂ ዲፕሎማሲን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው ሲሉ በሩሲያ የሞስኮ ስቴት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኢንስቲትዩት የፋይናንስ ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ ዲን ኢቅባል ጉሊዬቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ከሩሲያው ባለሙያ የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 ሩሲያ ተጨማሪ የናፍጣ ምርት ወደ ገበያ ስታቀርብ ዋጋ ይቀንሳል፤ ይህ የሚሆነው ከዋሽንግተን በሚተላለፍ መመሪያ ሳይሆን በእውነተኛ አቅርቦት እና በተገማች ገበያ ምክንያት ነው።

🟠 የ5-6% የዋጋ ቅናሽ ከፍተኛ የሚባል ቢሆንም፤ ቅሉ ዐንደምታው ላይ ነው። ሩሲያ የገበያ ሚዛንን በፍጥነት ማስተካከል የምትችል በመሆኗ ከሞስኮ ጋር መተባበር የኢኮኖሚ ጥቅም እንጂ ፖለቲካዊ ስጋት እንዳልሆነ ያሳያል።

🟠 ጉሊዬቭ ስምምነቱን "መጠነኛ ነገር ግን የተግባራዊነት አሸናፊነት ማሳያ" ሲሉ የጠሩት ሲሆን አውሮፓ ስለ አዳዲስ ማዕቀቦች እየተከራከረች ባለችበት ወቅት፤ የሩሲያ ናፍጣ የዓለም ዋጋን አስቀድሞ እንዳረገበ እና ዋሽንግተንም ሞስኮን በይፋ እንዳመሠገነች ጠቅሰዋል።

🟠 በኢነርጂ ዘርፍ ከቃላት ይልቅ የምርት መጠን፣ ወቅታዊነት እና ተግባራዊ ስምምነቶች ወሳኝ ናቸው፤ ሩሲያም የዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ሥርዓት ተቆጣጣሪ መሆኗን በድጋሚ አስመስክራለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,370007
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

22 de out. de 2026, 10:30

Photo1/2
ስፑትኒክ አፍሪካ "አዲስ የዜና አቀራረብ ” ይዞ መጥቷል - ማሊያዊ ጦማሪ

ስፑትኒክ በታንዛኒያ እና ደቡብ አፍሪካ መስፋፋቱ የዜና ምንጮች እንዲበዙ እና ለምዕራባውያን ሚዲያዎች አማራጭ እንደሚፈጥር ኢቡ ሲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

“የአፍሪካ አኀጉር ከጥቅማቸው ጉዳታቸው በሚያመዝነው የምዕራባውያን ሚዲያዎች ተጥለቅልቋል። ትክክለኛ መረጃ መስጠት አልቻሉም፤ ይህ ደግሞ በሁሉም ዘንድ የታወቀ ነው። የስፑትኒክ መምጣት አፍሪካውያን ሰፊ የዜና ምንጮች እንዲያገኙ ዕድል ያሰጣል” ብለዋል።

🤝 ከሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ጋር የሚደረጉ አጋርነቶች የሥልጠና፣ የክህሎት ሽግግር እና የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥሩም አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,460005
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

17 de out. de 2026, 20:25

Video
🇷🇺🤝🇨🇺 ኩባ በሩስያ የተደረገላት የምግብ ዕርዳታ "ሁለቱን ሀገራት የሚያስተሳስረውን ጠንካራ ወዳጅነት ያሳያል" ስትል ምስጋና አቀረበች

ኩባ በዓለም የምግብ ፕሮግራም ፈንድ የሩሲያ አስተዋጽኦ አካል ሆኖ ከተገዛው እና በደሴቲቱ ለሚገኙ እጅግ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከሚከፋፈለው አዲስ የቪታሚን የበለጸገ ዘይት ጭነት ተረክባለች።

💬 "እነዚህ 750 ቶን የሚመዝኑ የምግብ ዘይቶች በከፍተኛ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ከ0 እስከ 5 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሕጻናት፣ ሥር የሰደደ የልጅነት ሕመም ላለባቸው ትናንሽ ሕጻናት፣ ክብደታቸው እና ቁመታቸው ዝቅተኛ ለሆኑ እንዲሁም ለነፍሰ ጡር ሴቶች የሚከፋፈሉ ይሆናል" ሲሉ የኩባ የውስጥ ንግድ ሚኒስትር ቤዚ ሪያዝ ቬላዝኬዝ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
70001
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

17 de out. de 2026, 19:55

Video
አዲስ አበባ ከፍተኛ በካይ ጋዝ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎችን በካሜራ በመለየት እርምጃ ልትወስድ ነው

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከፍተኛ በካይ ጋዝ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለው መመሪያ ከወጣ በኋላ የተሰጠው የእፎይታ ጊዜ ያበቃ በመሆኑ አሁን ሙሉ በሙሉ ወደ ሕግ ማስከበር እርምጃ እንደሚገባ አስታውቋል።

የቢሮው መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🔸 በናሙና ከተፈተሹት 89 የናፍጣ (ዴዝል) መኪኖች ውስጥ መስፈርቱን ያሟሉት 14.6% (13ቱ) ብቻ ናቸው። የቤንዚን መኪኖች ግን 91% አሟልተዋል።

🔸 ከፍተኛ በካይ ጋዝ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎች በቀጣይ በካሜራ ቴክኖሎጂ ተለይተው ከትራፊክ አገልግሎት ይታገዳሉ።

🔸 አሮጌ መኪኖችን በኤሌክትሪክ እና ንጹህ ተሽከርካሪዎች ለመተካት መንግሥት ከ85% እስከ 90% የሚሆነውን ወጪ በብድር የሚያመቻችበት አሰራር ተዘርግቷል።

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
4590011
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

17 de out. de 2026, 19:25

Photo
🇪🇬🤝🇸🇦 ግብፅ ጥያቄ ከቀረበላት ሳዑዲ አረቢያን ለመጠበቅ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ናት - ፕሬዝዳንት ኤል-ሲሲ

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል-ሲሲ ሳዑዲ አረቢያን ከውጭ ጠላት ጥቃት ለመከላከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲያጸድቅ የሀገሪቱን ፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ማዘዛቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የግብፅ ፓርላማ ለሳዑዲ የሚደረገውን ድጋፍ አስመልክቶ ነገ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ምት አስቸኳይ ስብሰባውን ያደርጋል፡፡

☪️ ግብፅ እና ሳዑዲ አረቢያ "የአረብ እና የእስልምና ዓለማት እምብርት" ላይ የሚገኙ መሆናቸውን እና በየትኛውም ወገን የሚደርስ ጉዳት በሌላው ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ የሁለቱ ሀገራት እንዲሁም የባህረ ሰላጤው አረብ ሀገራት ብሔራዊ ደህንነት እርስ በርስ የተሳሰረ መሆኑን አስገንዝበዋል።

👉 ግብፅ የሳዑዲ ደህንነት ወይም ድንበር ላይ የሚፈጸም ማንኛውንም ጥሰት፣ እንዲሁም በቀይ ባህር ወይም በዓለም አቀፍ የባህር ማጓጓዣ መስመሮች ላይ የሚሰነዘር ምንም አይነት አደጋን ፈጽሞ እንደማትታገስ አረጋግጠዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
7580013
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

17 de out. de 2026, 18:55

Video
#viral | ካሊፎርኒያ በእሳት እየነደደች ነው፦ የሰደድ እሳቱ 150 ሺህ ሰዎችን ከኃይል አቅርቦት ውጪ አደረገ

🇺🇸 ከፍተኛው የኃይል መቋረጥ የተከሰተው በሎስ አንጀለስ ካውንቲ ውስጥ መሆኑን የግዛቷ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
882008
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

17 de out. de 2026, 18:33

Video
የአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ የዚምባብዌን የትምህርት ሞዴል እንዴት ሊጠቀሙት እንደሚችሉ ባለሙያ ጠቆሙ

የዚምባብዌ የትምህርት 5.0 ሞዴል የአፍሪካ ሀገራት ተመራቂዎችን ከሥራ ፈላጊነት ወደ ፈጣሪዎች እና ወደ ኢንዱስትሪ ባለቤትነት ለመቀየር የሚያስችል ትልቅ እምቅ አቅም እንዳለው የዚምባብዌው አካዳሚክ ባለሙያ ታፋድዝዋ ሙራንጋዋ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ከባለሙያው የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 ተስማሚነትን መፍጠር ፦ የዚምባብዌን ተሞክሮ በቀጥታ ከመቅዳት ይልቅ የትምህርት ሥርዓቶች ከየሀገራቱ የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር መጣጣም አለባቸው።

🟠 ክፍተቱን ማጥበብ ፦ የዩኒቨርሲቲዎችን ውጤት ከኢንዱስትሪው ፍላጎት ጋር ለማጣጣም አዳዲስ ፈጠራዎች በቀጥታ በትምህርት አሰጣጡ ሂደት ውስጥ መካተት ይኖርባቸዋል።

🟠 በመሠረተ ልማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ፦ ስኬት ሊመጣ የሚችለው ዘመናዊ ላቦራቶሪዎች፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች እና ልክ በዚምባብዌ እንዳሉት ያሉ የፈጠራ ማዕከላት ሲገነቡ ብቻ ነው።

🟠 አጋርነት መፍጠር ፦ ዩኒቨርሲቲዎች የአካባቢ ቴክኖሎጂዎችን በገንዘብ ለመደገፍ እና ወደ ገበያ ለማስገባት ከግል ባለሀብቶች እና ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅርበት መሥራት አለባቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
944003
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

17 de out. de 2026, 17:55

Photo
ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የአፍሪካ ወታደራዊ ማርሽ ባንዶች ውድድርና ፌስቲቫል ልታስተናግድ ነው

🥁 አኅጉራዊው ፌስቲቫልና ውድድር ከታህሳስ 2 እስከ 5 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ የመከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሰው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

መርሐ ግብሩን የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን፤ ከሁሉም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የተወጣጡ ወታደራዊ ማርሽ ባንዶች ይሳተፉበታል።

ውድድሩ የሚከተሉንትን ያካትታል፦

▪️ የጎዳና ላይ ሰልፍ፣
▪️ የሜዳ ላይ ትርኢት እና
▪️ የልዩ ሙዚቃዎች ውድድር

🌍 አዲስ አበባ ይህን አኅጉራዊ መርሃ ግብር በብቃት ለማስተናገድ ሙሉ ዝግጅት ማድረጓ የተገለጸ ሲሆን ወታደራዊ ባንዶች ባህላቸውንና ትውፊታቸውን የሚያስተዋውቁበት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ተገለጿል።

📹 በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,020005
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

17 de out. de 2026, 17:29

Video
የአፍሪካ የብድር ምዘና ኤጀንሲ አፍሪካ ላይ ይደርስ የነበረውን አድልዎ ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል - ኢትዮጵያዊ የባንክ ባለሙያ    የዚህ ኤጀንሲ የምዘና ውጤቶች ተቀባይነት፣ ገለልተኝነት እና ተዓማኒነት የብድር ስጋት፣ ማክሮ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ማንጸባረቅ መቻሉ ላይ የተወሰነ ነው የሚሉት የፈርስት ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚካኤል አዲሱ ናቸው።    “ኤጀንሲው…
936002
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

17 de out. de 2026, 17:01

Photo
አዲስ አበባ ለ2019 በጀት ዓመት የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎት 2.3 ቢሊዮን ብር የበጀት ድጎማ መመደቧን ይፋ አደረገች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት ለማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎት ያቀረበው የድጎማ በጀት ከ2018 በጀት ዓመት ድጎማ (1.3 ቢሊዮን ብር) የ76.92% ጭማሪ የታየበት ሆኗል።

የዘንድሮው የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ምዝገባ ከጥቅምት 1 እስከ ኅዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ለሁለት ወራት የሚካሄድ ሲሆን፣ ከ3 ሚሊዮን በላይ የከተማዋን ነዋሪዎች አባል ለማድረግ ታቅዷል።

ባለፈው በጀት ዓመት ከ2.75 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አባል የሆኑ ሲሆን፣ ከ3.2 ሚሊዮን በላይ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በነጻና በቅናሽ ሕክምና አግኝተዋል ተብሏል።

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
959002
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ logo
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

17 de out. de 2026, 16:29

Photo
📈 የአሜሪካ የበጀት ጉድለት ወደ 2 ትሪሊዮን ዶላር ገደማ በመድረስ፤  ባለፉት 5 ዓመታት ከፍተኛው አኃዝ ሆኖ ተመዘገበ

የአሜሪካ የበጀት ጉድለት በበጀት ዓመቱ በ217 ቢሊዮን ዶላር በማደግ ወደ 1.99 ትሪሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱን የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃዎች አመላክተዋል። ይህም እ.ኤ.አ ከ2021 ወዲህ የታየው ከፍተኛው የበጀት ጉድለት እና በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ሦስተኛው ትልቁ ዓመታዊ እጥረት ሆኖ ተመዝግቧል።

የዕዳ ክፍያ ወጪዎች 1.36 ትሪሊዮን ዶላር በመድረስ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግበዋል። ይህም በ12% (144 ቢሊዮን ዶላር) ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከማኅበራዊ ዋስትና  እና ከጤና ዋስትና ወጪዎች ድምር ብቻ ያነሰ ያደርገዋል።

የመከላከያ ወጪዎች በ6% አድገው 917 ቢሊዮን ዶላር ደርሰዋል። ምንም እንኳን የገንዘብ ሚኒስቴሩ ከዚህ ወጪ ውስጥ ምን ያህሉ ከኢራን ጦርነት ጋር እንደሚያያዝ ግልጽ አለመሆኑን ቢገልጽም።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1,100002

Showing 30 of 115 posts

Avaliação

Login necessário

Frequently Asked Questions

Sobre o que é o canal Telegram ስፑትኒክ ኢትዮጵያ?+

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ (@sputnik_ethiopia) é um canal Telegram listado em Notícias do Mundo no tgdio. Ranking, avaliações, reviews e posts recentes para decidir antes de assinar. Atualmente lista cerca de 51.981 inscritos no tgdio.

Como entrar em ስፑትኒክ ኢትዮጵያ (@sputnik_ethiopia) no Telegram?+

Abra o perfil no tgdio e use Join / Open in Telegram para assinar @sputnik_ethiopia de graça.

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ é um bom canal de Notícias do Mundo?+

No tgdio você pode ver avaliação, reviews, ranking e posts de ስፑትኒክ ኢትዮጵያ antes de entrar. Atualmente lista cerca de 51.981 inscritos no tgdio. Compare com canais similares de Notícias do Mundo.

Onde ver estatísticas e posts de ስፑትኒክ ኢትዮጵያ?+

No tgdio, abra @sputnik_ethiopia para stats de inscritos, ranking, avaliações e posts. Use Stats para gráficos.