ነሐሴ 11/2018
#ፆመ_ፍልሰታ_ለማርያም_11ኛ_ቀን
#እናታችን_ቅድስት_ሐና
#ማህሌታዊዉ_ቅዱስ_ያሬድ
👉#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንለምንበት እናታችን #ማርያምን በምልጃ ፀሎቷ እንድታስበን ለምንማፀንበት ለጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አያት ለሆነችዉ #ለቅድስት_ሐና እና #ለቅዱስ_ያሬድ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #ሐና ማለት በእብራይስጥ #የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው ሐና, ዮሐና, ሐናኒያ,የሚሉት የእብራይስጥ ስሞች ትርጉማቸው ተወራራሽ ነው የዚህች የብፅዕት ሐና ክብሯን ለመናገር የሚችል የለም እርሷ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ለክርስቶስ ለእግዚአብሔር #ወልድ በስጋ አያቱ ሆናለችና
👉አንድም ለሰማይና ለምድር ንግስት ለሆነች ድንግል ማርያም እናት ሆናለችና ከአለም ሴቶች ሁሉ የቅድስት ማህፀን እንደምን ይክበር በፍጥረት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥንተ ዐብሶ የአዳም በደል መተላለፍ የቀረው #በቅድስት_ሐና_ማህፀን ነው ለዚህም አንክሮ ምስጋና ይገባል
👉ይስሐቅን የተሸከመች የሳራ ማሕፀን ብሩክ ከተባለች ድንግል #ማርያምን የተሸከመች የሐና ማህፀን እንደምን አይባልም ከፍጥረታት አለም #እግዚአብሔር ድንግል ማርያምን እንደመረጠ ሁሉ ቅድስት ሐናንም በስጋ ለአያትነት መርጧታል
👉እመቤታችንም ከአባቷ ከቅዱስ ኢያቄም ከእናቷ ከቅድስት ሐና ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች ተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች ግንቦት 1ቀን ሊባኖስ በምትባል አካባቢ #ተወለደች
👉እመቤታችን በፆም በጸሎትም የተገኘች የስዕለት ልጅ ናት ንጽሕት በመሆኗም #ማኀደረ_መለኮት የእግዚአብሔር ማደሪያ ሆናለች ከዚህ በኋላ እመቤታችን በእናት በአባቷ ቤት 3 ዓመት ተቀመጠች
👉 #ኢያቄምና_ሐናም ልጃቸውን ሲያሳድጉ ስላደረገላቸውም ሁሉ እግዚአብሔርን ፈፅመው እያመሰገኑት 3 ዓመት ኖሩ በፆም እና በፀሎት ተወስነው ለድሆችና ለጦም አደሮች ምጽዋት እየሰጡ በጐ ሥራን አበዙ
👉ልጃቸውንም #ድንግል_ማርያምን በንፅሕና ሲያሳድጉ ሦስት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ ሐና ባሏን ኢያቄምን ወንድሜ ሆይ ልጃችንን #ለቤተ_እግዚአብሔር_ብፅዐት አድርገን እንስጥ ልጃችን ቤተ እግዚአብሔርን ልታገለግል እንጂ በዚህ ዓለም እኛን ልታገለግል እንዳልተሳልን አስብ አለችው ኢያቄምም ይህን ነገር ከሚስቱ በሰማ ጊዜ ደስ አለው
👉 #ነቢየ_እግዚአብሔር_ዳዊት ‹‹ልጄ ሆይ ስሚ እይ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ ክርስቶስ ውበትሽን /ንጽሐ ባሕርይሽን/ ወድዷልና›› መዝ.44 ቁ.10-11 ብሎ እንደተናገረ ለወላጆቿ የብፅአት ልጅ የሆነችው ድንግል ማርያም ከእናት ከአባቷ ተለይታ ታህሣሥ 3 ቀን በ 3 ዓመቷ ወደ መቅደሰ ኦሪት ገብታለች
👉 #እናታችን_ማርያምም በታላቅ ክብር ወደ ቤተ መቅደስ ገብታለች ካህኑ ዘካሪያስም ስለምትመገበው ምግብ በተጨነቀ ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ከሰማያት ወርዶ አንድ ክንፉን ጋርዶ አንድ ክንፉን አጐናጽፎ ኅብስቱን አብልቷት ወይኑን አጠጥቷት የብርሃን ፅዋ እና የብርሃን መሶብ ይዞ ወደ ሰማይ ተመልሷል
👉እመቤታችንም ከዚህ በኋላ ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላአክት ጋር እየዘመረች ፈጣሪዋን እያመሰገነች 12 ዓመት #በቤተ_መቅደስ ተቀመጠች
👉የተወደዳችሁ የተዋህዶ ልጆች ለአባ ሕርያቆስ ለቅዱስ ኤፍሬም ለቅዱስ ያሬድ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለፀች #እመቤታችን_ማርያም እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን
👉ለበላኤ ሰብዕ የተለመች እመ አምላክ ለኛም ትለመነን ከልጅዋ ከወዳጅዋ #ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን
👉አምላካችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሀገራችንን ኢትዮጲያን በምህረት አይኑ ይጎብኝልን የእናታችን ማርያም ምልጃና ፀሎት ቃል ኪዳን ከኃጢአት በስተቀር የምንመኘዉን በጎ ነገር ሁሉ ይፈፅምልን በረከት ረድኤቷ ለሁላችንም ይድረሰን
👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን" ✝️💒✝️
👉 ሰለሞን የገብርኤል ነሐሴ 11/2018 ዓ/ም
📱
https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen - 📱
https://www.tiktok.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱
https://YouTube.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱
https://www.Instagram.com/@Orthodox_tewahdo_nen