✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች Telegram channel photo

✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች

@orthodox_pic21Public Channel

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን:: ➾ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምስሎች የምታገኙበት ነው ✞ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ http://t.me/Orthodox_tewahdo_nen

ReligiãoportuguêsBrasil

2

Last views

48.3k (48,308 subscribers)
Membros
—
Rating
61
Total Posts
Oct 20, 2026, 10:52 PM
Atualizado
Mar 31, 2026
Created
Stats

Você está vendo conteúdo em português. Para ver conteúdo em outros idiomas, mude o idioma do site.

Channel Information

Channel Information
Channel Name✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች
Username@orthodox_pic21
CategoryReligião
Languageportuguês
CountryBrasil
Membros48,308
Channel TypePublic Channel
Created31 de mar. de 2026
Last Updated20 de out. de 2026 • anteontem
StatusActive

Classificação

Classificação Global
#115417+298
Classificação por Idioma
#2415+16
Classificação por Categoria
#1902+8

Crescimento de Participantes

Total: 48.3K30 Days growth: +5781.2%
09/2109/2610/0110/0610/1110/1610/20
Crescimento de Participantes - 30 Days
DateSubscribers
21:09:202647,730
22:09:202647,730
23:09:202647,730
24:09:202647,730
25:09:202647,730
26:09:202647,730
27:09:202647,730
28:09:202647,730
29:09:202647,730
30:09:202647,730
01:10:202647,730
02:10:202647,730
03:10:202647,730
04:10:202647,730
05:10:202647,730
06:10:202647,730
07:10:202647,730
08:10:202647,730
09:10:202647,730
10:10:202647,730
11:10:202647,730
12:10:202647,730
13:10:202648,096
14:10:202648,096
15:10:202648,096
16:10:202648,096
17:10:202648,096
18:10:202648,096
19:10:202648,096
20:10:202648,308
Crescimento de Participantes - Weekly
DateSubscribers
Week of 30:03:202645,577
Week of 06:04:202645,704
Week of 13:04:202645,716
Week of 20:04:202645,710
Week of 27:04:202645,710
Week of 04:05:202645,710
Week of 11:05:202645,680
Week of 18:05:202645,680
Week of 25:05:202645,680
Week of 01:06:202645,609
Week of 08:06:202645,609
Week of 15:06:202645,532
Week of 22:06:202645,757
Week of 29:06:202645,757
Week of 06:07:202645,757
Week of 13:07:202646,233
Week of 20:07:202646,422
Week of 27:07:202646,574
Week of 03:08:202646,574
Week of 10:08:202646,574
Week of 17:08:202647,087
Week of 24:08:202647,362
Week of 31:08:202647,580
Week of 07:09:202647,580
Week of 14:09:202647,730
Week of 21:09:202647,730
Week of 28:09:202647,730
Week of 05:10:202647,730
Week of 12:10:202648,096
Week of 19:10:202648,308
Crescimento de Participantes - Monthly
DateSubscribers
March 202645,449
April 202645,710
May 202645,680
June 202645,757
July 202646,422
August 202647,362
September 202647,730
October 202648,308
Crescimento de Participantes - Yearly
DateSubscribers
202648,308

Últimos Posts

✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች logo
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች

10 de set. de 2026, 15:31

Photo
ነሐሴ 15/2018
#ፆመ_ፍልሰታ_ለማርያም_15ኛ_ቀን
#ቅዱስ_ቂርቆስ_ወ_ኢየሉጣ
#ሰማዕቱ_ቅዱስ_ሚናስ

#በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሣስባሉ መዝ.44፥16

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን #ለእናታችን_ማርያም_ትንሣኤና_ዕርገት ዋዜማ እንኳን አደረሰን እንዲሁም #ለቅዱሳኑ_ቂርቆስ_ወኢየሉጣ_ወሚናስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን

👉የጠፋ በግ አዳምን የፈለገው ባገኘውም ጊዜ የተሸከመው እውነተኛ ቸር ጠባቂያችን #ክርስቶስ ካንቺ የተወለደ እመቤታችን #ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ

👉 #እግዚአብሔር በብሩህ ደመና ተጭኖ መጥቶ በማኅፀንሽ ያደረ #እመቤቴ_ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ

👉በቅዱሳን ነቢያት በቅዱሳን መላእክት አድሮ የሚኖር ካንች ተወልዶ የተገለጸልን #እመቤታችን_ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ

👉ከወለድሽው በኋላ ማኅተመ ድንግልናሽ እንዳይለወጥ አድርጎ የጠበቀሽን #አማኑኤልን የወለድሽው #እመቤቴ_ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ

👉ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይለወጥ #ንጉሥ_ክርስቶስን የወለድሽ #እመቤቴ_ማርያም ሆይ ሰላምታ ይገባሻል

👉እኛ ከምንወደው እሱም ከሚወደን ልጅሽ ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ #ለምኝልን

👉እናታችን ማርያም የቅዱሣን ሁሉ መሠብሠቢያ የምትሆን ቅድስት ሀገርሽን ኢትዮጵያን በምልጃ ፀሎትሽ አስቢያት እኛንም ልጆችሽን ልጅሽ #ክርስቶስ ይቅር ይለን ዘንድ ለምኝልን በዚህ እለት የሚታሰቡ #ቅዱሣን ምልጃ ፀሎታቻዉ የከበረ ቃል ኪዳናቸዉ ከኛ ጋራ ይሁን

👉የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን" ✝️💒✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል ነሐሴ 15/2018 ዓ/ም

📱 https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.tiktok.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://YouTube.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.Instagram.com/@Orthodox_tewahdo_nen
873004
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች logo
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች

10 de set. de 2026, 15:31

Photo
ነሐሴ 14/2018
#ፆመ_ፍልሰታ_ማርያም_14ኛ_ቀን
#ፃድቁ_አቡነ_አረጋዊ
#ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችንን መድኃኒታችንን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንለምንበት #እናታችን_ማርያምን በምልጃ ፀሎቷ እንድታስበን ለምንማፀንበት ሐዋርያት የእናታችን #ማርያምን የከበረ ሥጋዋን ላገኙበት የሱባኤ ማጠናቀቅያ እንኳን አደረሰን

👉አምላክን የወለደሽ #እናታችን_ማርያም እጅግ ርህሩህና አዛኝ የሆንሽ እመቤት ነሽና ባንቺ ጥበቃ ከተማፀኑ እርዳታሽንም አማላጅነትሽንም የፈለጉ ሁሉ አንድ ስንኳ አልቀረባቸዉምና የኛንም የልጆችሽን ልመና ሰምተሽ ተቀብለሽ ከልጅሽ ዘንድ አማልጅን

👉የተመሰገንሽ የከበርሽ እናታችን ማርያም ሆይ በልጅሽ በአምላካችን በመድኃኒታችን #ክርስቶስ ዘንድ ስለ ኃጢአታችን ስርየት ለምኝልን በዚህ ምድር አኗኗራችንም የበረከት እንዲሆንልን የጉስቁልና ኑሮን ያርቅልን ዘንድ ከልጅሽ ዘንድ አማልጅን

👉ስለአስራት ሀገርሽ ኢትዮጵያ ከልጅሽ #ክርስቶስ ዘንድ ለምኝልን ማልጅልን ከሚታይም ከተሰወረም መከራ ልጅሽ ይጠብቀን በፀሎትሽ ረዳትነት በልጅሽ አዳኝነት እንታመናለን አባቶቻችን ሐዋርያትን እንደባረክሽ እኛንም ባርኪን "አሜን"

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው ቅዱሣን አባቶቻችን ፃድቁ #አቡነ_አረጋዊ እና #ቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ በፀሎት በምልጃቸዉ ይጠብቁን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን" ✝️💒✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል ነሐሴ 18/2018 ዓ/ም

📱 https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.tiktok.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://YouTube.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.Instagram.com/@Orthodox_tewahdo_nen
1,000002
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች logo
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች

10 de set. de 2026, 15:31

Photo
ነሐሴ 13/2018
#በዐለ_ደብረ_ታቦር
#ፆመ_ፍልሰታ_ለማርያም_13ኛ_ቀን

በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነዉ
እርሱን ስሙት ማቴ.17፥1-8

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችንና መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ብርሐነ መለኮቱን ለገለጠበት አመታዊ #የደብረ_ታቦር ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን

👉ይህ በአል ከጌታችን ዘጠኙ #አበይት_በዐላት መካከል አንዱ ነው በአሉ በየአመቱ ነሐሴ 13 ላይ ይከበራል

👉#ቡሔ ማለት በደብረ ታቦር የተገለጠወ የጌታችን የፊቱ ብርሐን ፀዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መሆን ያስረዳል ስለዚህ የብርሐን ብርሐናዊ ማለት ነው

👉ታሪኩም በሶስቱ ወንጌላት ላይ የተፃፈ ሲሆን ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ ክርስቶስ ስምንቱ ሐዋርያትን ከእግር ደብር፣"ሶስቱን ቅዱሳን ጴጥሮስ ያዕቆብ ዮሐንስን" ይዙአቸው ወደ ደብረ ታቦር ተራራ በመውጣት የሞተውን ሙሴን አስነሰቶ የተሰወረውን ኤሊያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ #የሕያዋን_አምላክ እና ሙታንን አንሺው እርሱ መሆኑን ብርሀኑን የገለፀበት እለት ነዉ ማቴ.17፥1-9

👉ብዙ ተራራ እያለ #ደብረ_ታቦር_ተራራን የመረጠበት አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገለፅ

👉በነብዩ ዳዊት #ታቦርና_አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ መዝ.88፥12 በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሀኑን ሲገልፅ የብርሐኑ ነፀብራቅ እስከ #አርሞንኤም_ተራራ ድረሰ እንደሚታይ የተነገረው ትንቢትን ለመፈፀም ነው

👉ለምን ሙሴ እና ኤሊያስን መረጠ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠየቃቸው እንደመለሱለት ሁሉ በእውነት #የሙሴ እና #የኤሊያስ ጌታ እና አምላካቸው እርሱ #ኢየሱስ_ክርስቶስ መሆኑን በተራራው ላይ መስክረዋል ማቴ.16፥13 አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበዐሉ ረድኤትና በረከት ያሣትፈን

👉እንዲሁም በዚህ እለት የሊቀ ነብያት #ቅዱስ_ሙሴ የልደቱ መታሠቢያ ክብረ በአል ነዉ ረድኤት በረከቱ ይድረሰን እመቤታችን ማርያም ልጅሽ #ክርስቶስ ፀጋና ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን" ✝️💒✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል ነሐሴ 13/2018 ዓ/ም

📱 https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.tiktok.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://YouTube.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.Instagram.com/@Orthodox_tewahdo_nen
726001
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች logo
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች

10 de set. de 2026, 15:31

Photo
ነሐሴ 11/2018
#ፆመ_ፍልሰታ_ለማርያም_11ኛ_ቀን
#እናታችን_ቅድስት_ሐና
#ማህሌታዊዉ_ቅዱስ_ያሬድ

👉#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንለምንበት እናታችን #ማርያምን በምልጃ ፀሎቷ እንድታስበን ለምንማፀንበት ለጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አያት ለሆነችዉ #ለቅድስት_ሐና እና #ለቅዱስ_ያሬድ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #ሐና ማለት በእብራይስጥ #የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው ሐና, ዮሐና, ሐናኒያ,የሚሉት የእብራይስጥ ስሞች ትርጉማቸው ተወራራሽ ነው የዚህች የብፅዕት ሐና ክብሯን ለመናገር የሚችል የለም እርሷ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ለክርስቶስ ለእግዚአብሔር #ወልድ በስጋ አያቱ ሆናለችና

👉አንድም ለሰማይና ለምድር ንግስት ለሆነች ድንግል ማርያም እናት ሆናለችና ከአለም ሴቶች ሁሉ የቅድስት ማህፀን እንደምን ይክበር በፍጥረት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥንተ ዐብሶ የአዳም በደል መተላለፍ የቀረው #በቅድስት_ሐና_ማህፀን ነው ለዚህም አንክሮ ምስጋና ይገባል

👉ይስሐቅን የተሸከመች የሳራ ማሕፀን ብሩክ ከተባለች ድንግል #ማርያምን የተሸከመች የሐና ማህፀን እንደምን አይባልም ከፍጥረታት አለም #እግዚአብሔር ድንግል ማርያምን እንደመረጠ ሁሉ ቅድስት ሐናንም በስጋ ለአያትነት መርጧታል

👉እመቤታችንም ከአባቷ ከቅዱስ ኢያቄም ከእናቷ ከቅድስት ሐና ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች ተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች ግንቦት 1ቀን ሊባኖስ በምትባል አካባቢ #ተወለደች

👉እመቤታችን በፆም በጸሎትም የተገኘች የስዕለት ልጅ ናት ንጽሕት በመሆኗም #ማኀደረ_መለኮት የእግዚአብሔር ማደሪያ ሆናለች ከዚህ በኋላ እመቤታችን በእናት በአባቷ ቤት 3 ዓመት ተቀመጠች

👉 #ኢያቄምና_ሐናም ልጃቸውን ሲያሳድጉ ስላደረገላቸውም ሁሉ እግዚአብሔርን ፈፅመው እያመሰገኑት 3 ዓመት ኖሩ በፆም እና በፀሎት ተወስነው ለድሆችና ለጦም አደሮች ምጽዋት እየሰጡ በጐ ሥራን አበዙ

👉ልጃቸውንም #ድንግል_ማርያምን በንፅሕና ሲያሳድጉ ሦስት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ ሐና ባሏን ኢያቄምን ወንድሜ ሆይ ልጃችንን #ለቤተ_እግዚአብሔር_ብፅዐት አድርገን እንስጥ ልጃችን ቤተ እግዚአብሔርን ልታገለግል እንጂ በዚህ ዓለም እኛን ልታገለግል እንዳልተሳልን አስብ አለችው ኢያቄምም ይህን ነገር ከሚስቱ በሰማ ጊዜ ደስ አለው

👉 #ነቢየ_እግዚአብሔር_ዳዊት ‹‹ልጄ ሆይ ስሚ እይ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ ክርስቶስ ውበትሽን /ንጽሐ ባሕርይሽን/ ወድዷልና›› መዝ.44 ቁ.10-11 ብሎ እንደተናገረ ለወላጆቿ የብፅአት ልጅ የሆነችው ድንግል ማርያም ከእናት ከአባቷ ተለይታ ታህሣሥ 3 ቀን በ 3 ዓመቷ ወደ መቅደሰ ኦሪት ገብታለች

👉 #እናታችን_ማርያምም በታላቅ ክብር ወደ ቤተ መቅደስ ገብታለች ካህኑ ዘካሪያስም ስለምትመገበው ምግብ በተጨነቀ ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ከሰማያት ወርዶ አንድ ክንፉን ጋርዶ አንድ ክንፉን አጐናጽፎ ኅብስቱን አብልቷት ወይኑን አጠጥቷት የብርሃን ፅዋ እና የብርሃን መሶብ ይዞ ወደ ሰማይ ተመልሷል

👉እመቤታችንም ከዚህ በኋላ ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላአክት ጋር እየዘመረች ፈጣሪዋን እያመሰገነች 12 ዓመት #በቤተ_መቅደስ ተቀመጠች

👉የተወደዳችሁ የተዋህዶ ልጆች ለአባ ሕርያቆስ ለቅዱስ ኤፍሬም ለቅዱስ ያሬድ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለፀች #እመቤታችን_ማርያም እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን

👉ለበላኤ ሰብዕ የተለመች እመ አምላክ ለኛም ትለመነን ከልጅዋ ከወዳጅዋ #ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን

👉አምላካችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሀገራችንን ኢትዮጲያን በምህረት አይኑ ይጎብኝልን የእናታችን ማርያም ምልጃና ፀሎት ቃል ኪዳን ከኃጢአት በስተቀር የምንመኘዉን በጎ ነገር ሁሉ ይፈፅምልን በረከት ረድኤቷ ለሁላችንም ይድረሰን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን" ✝️💒✝️

👉 ሰለሞን የገብርኤል ነሐሴ 11/2018 ዓ/ም

📱 https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.tiktok.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://YouTube.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.Instagram.com/@Orthodox_tewahdo_nen
887006
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች logo
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች

10 de set. de 2026, 15:31

Photo
ነሐሴ 10/2018
#ፆመ_ማርያም_10ኛ_ቀን
#መስቀለ_ኢየሱስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምናመሰግንበት #እናታችን_ማርያምን በምልጃ ፀሎቷ እንድታስበን ለምንማፀንበት #ለመስቀለ_ኢየሱስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

#መስቀል ሀይላችን ነዉ"ኃይላችን መስቀል ነዉ

👉ዲያብሎስን ያየውም ያላየውም የሚያውቀውም የማያውቀውም ሁሉ ይጠላዋል የሚጠላበት አንድ ምክንያት አለው ለምንድነው ዲያብሎስ የሚጠላዉ?

👉መጀመሪያ #ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን የሰውን ፍቅር ስለቆረጠ ስለበጠሰ ሲሆን

👉ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የነበረውን የጥል ግድግዳ ደግሞ የናደችው የፍቅር መሠረት #ድንግል_ማርያም ስለሆነች ሰው ሁሉ ዲያብሎስን እንደሚጠላ ሁሉ ድንግል ማርያምን ደግሞ የግድ መውደድ አለበት

👉ለምን ቢሉ ዲያብሎስ የዘጋውን በር ለመክፈት ምክንያት ሆና የተገኘች #እናታችን_ማርያም ስለሆነች ነዉ

👉እዚህ ላይ ነበር ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም የተናገረው ድንግል #ማርያም የሁላችን መመኪያ ናት የመጀመሪያው መርገም በእርሷ ምክንያት ስለጠፋ ይልና ወደ መጨረሻው ሲሄድ ምን ይላል በሄዋን ምክንያት በዕፀ በለስ ምክንያት ዲያብሎስ ያዘጋው በር #በድንግል_ማርያም ሁለተኛ ተከፈተ ስለዚህ በእመቤታችን የተዘጋው ስለተከፈተ የግድ ማንም ይሁን ማን እመቤታችንን መውደድና ማክበር አለበት

👉ዲያብሎስን ደግሞ የግድ ማንም ይሁን ማን መጥላት አለበት ለምን ቢሉ ፍቅር የተቋረጠዉ በዲያብሎስ ሲሆን ፍቅር የቀጠለዉ #በድንግል_ማርያም ይህን ማነፃፀር ነው ይህን ያነፃፀረ ሰው ሁሉ ድንግል ማርያምን ይወዳል

👉የእመቤታችን ፍቅር እንደሌሎቹ አይደለም በጣም ለየት ያለ ነው ለምን ከፈጣሪ ጋር የተያያዘ ስለሆነ የደህንነታችን ምክንያት ስለሆነች ጭምር ይሄ ፍቅር #የእግዚአብሔር ፍቅር ነው ለምን ቢሉ እመቤታችን እኮ #በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለች ፍቅር ናት

👉እመቤታችን አማላጃችን #እናታችን_ማርያም

✝️ የነቢያት ትንቢታቸው
✝️ የሐዋርያት ትምሕርታቸው
✝️ የወንጌላዊው ዮሐንስ የመስቀል ስር ስጦታ
✝️ የአባ ሕርያቆስ የሕይወቱ ጌጥ
✝️ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የአፉ ጣዕም
✝️ የቅዱስ ኤፍሬም በረከት
✝️ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እመቤት

👉በዚህ ሁሉ እየመሰልን #እናታችን_ማርያምን እንወዳታለን እናከብራታለን ምልጃና ፀሎቷ ሁላችንንም ይጠብቀን ረድኤት በረከቷ ከኛ ጋራ ይሁን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን" ✝️💒✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል ነሐሴ 10/2018 ዓ/ም

📱 https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.tiktok.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://YouTube.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.Instagram.com/@Orthodox_tewahdo_nen
936001
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች logo
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች

10 de set. de 2026, 15:31

Photo
ነሐሴ 8/2018
#ፆመ_ፍልሰታ_ለማርያም_8ኛ_ቀን
#ፃድቁ_አቡነ_ኪሮስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት #እናታችን_ማርያምን በምልጃ ፀሎቷ እንድታስበን ለምንለምንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ኪሮስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን

እናታችን #ማርያም መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ
ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ ምሳ.31፥29

👉 #ክርስቶስን ያከበሩ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ እውነትን የመሰከሩ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ ታላላቅ የምድር ነገስታትን ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ ከነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ

👉 #እናታችን_ማርያም ሆይ አንቺ እኮ ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ ሁሉ በእርሱ የሆነ ከሆነውም አንዳችም እንኳን ያለርሱ ያልሆነ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት የሁሉ ፈጣሪ የሁሉ አምላክ የሆነው #የኢየሱስ_ክርስቶስ እናት ነሽ

👉 #እናታችን_ማርያም በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም የለችም አትኖርምም ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ

👉እናት ስትሆኝ ድንግል ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ #እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ ለዓለም ሁሉ ድህነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ

👉እናቴ ሆይ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር አዎ አሁንም እላለሁ መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ ምሳ.31፥29

👉የእናታችን #ማርያም ምልጃና ፀሎት የከበረዉ ቃል ኪዳኗ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ አባታችን #አቡነ_ኪሮስ ረድኤት በረከት ያሣትፈን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን" ✝️💒✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል ነሐሴ 8/2018 ዓ/ም

📱 https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.tiktok.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://YouTube.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.Instagram.com/@Orthodox_tewahdo_nen
1,000005
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች logo
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች

10 de set. de 2026, 15:31

Photo
ነሐሴ 5/2018
#ፆመ_ማርያም_5ኛ_ቀን
#ብርሐናተ_አለም_ጴጥሮስና_ጳዉሎስ
#ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት #ለቅዱስ_ጴጥርስና #ለቅዱስ_ጳዉሎስ ለፃድቁ አባታችን #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን

👉እጅግ ሩህሩህና አዛኝ የሆንሽ #እናታችን_ማርያም ባንቺ ጥበቃ ከተማፀኑ እርዳታሽንም የፈለጉ ሁሉ አንዳችንም ነገር አላጡምና ምስጋና ይገባሻል

👉አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ ግብፅ ነው አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ #እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች

👉በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን #ጻድቁ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ

👉አባታችን ዓይን በገለፁ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለዉ ተነስተው "ስብሐት #ለአብ ስብሐት #ለወልድ ስብሐት #ለመንፈስ_ቅዱስ ከፅልመት ወደ ብርሐን ያመጣኸኝ ብለው አመስግነዋል

👉በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን መስለዋል አባታችን #ጻድቁ_አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማፀነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል

👉የፃድቁ አባታችን #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ረድኤት በረከታቸው አይለየን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው ቅዱሣን #ብርሃናተ_አለም_ጴጥሮስ_ወ_ጳዉሎስ እንዲሁም ሌሎች ቅዱሣን ምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቀን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ሀገራችንን ይጠብቅልን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን" ✝️💒✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል ነሐሴ 5/2018 ዓ/ም

📱 https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.tiktok.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://YouTube.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.Instagram.com/@Orthodox_tewahdo_nen
974004
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች logo
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች

26 de ago. de 2026, 09:58

Photo
ነሐሴ 4/2018
#ፆመ_ማርያም_4ኛ_ቀን
#ወንጌላዊው_ቅዱስ_ዮሐንስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት #ለፆመ_ማርያም አራተኛ ቀን እና ለወንጌላዊዉ #ለቅዱስ_ዮሐንስ ወርሐዊ መታሰቢያ በዐል እንኳን አደረሰን

👉የአብ ሙሽራው #ማሪያም_ሆይ ላንቺ ሠላምታ ይገባሻል የወልድ እናቱ #ማሪያም_ሆይ ላንቺ ሠላምታ ይገባሻል የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ንፅህት አዳራሽ #ማሪያም_ሆይ ሠላምታ ላንቺ ይገባሻል ወርቅና ብር ሀላፊ ጠፊ ነው ስለዚህም ከዚህ አለም ብልፅግና ይልቅ አንችን መውደድ እመርጣለሁና ቸርነትሽን አታርቂብን

👉እመቤታችን #ማሪያም ሆይ አሁንም በመዓልትና በለሊትም ጠብቂን ከመከራ ስራ ከመከራ ነፍስ ሰውሪን ለዘላለሙ አሜን

👉ነባቢ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስ ማለት #የእግዚአብሔር ፀጋ ደስታ ማለት ነው አባቱ ዘብዴዎስ እናቱ ማርያም ባውፍልያ ትባላለች ቁጥሩ ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት የሆነ ያዕቆብ የተባለ ወንድም ነበረው ማቴ.4፥21, 20፥20 ,ማር.1፥20

👉ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ አስቀድሞ የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ደቀ መዝሙር ነበር ዮሐ.1፥35 #ቅዱስ_ዮሐንስ ከአባቱና ከወንድሙ ጋር ዓሳ በሚያጠምድበት በገሊላ ባህር ላይ መረቡን ሲያበጅ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ለሐዋርያነት ጠራው

👉በመጀመሪያ ቃል ነበር ብሎ የቃልን ስጋ መሆን የነገረን የድንግል ማርያም ምዕመናንን ወክሎ የተቀበለ ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በሕይወተ ስጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን ያለው #ወንጌላዊው_ቅዱስ_ዮሐንስ ነው

👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ብዙ መጠሪያ ስሞች አሉት እነሱም፦

1,ዮሐንስ ታኦሎጎስ( ነባቢ መለኮት)
2,ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ
3,ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ
4,ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
5,ዮሐንስ አቡቀለምሲስ
6,ዮሐንስ ቁፅረ ገፅ
7,ዮሐንስ ድንግል
8,ዮሐንስ ወንጌላዊው
9,ዮሐንስ ዘንስር

👉የሚሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ የወንጌላዊዉ #ቅዱስ_ዮሐንስ በረከቱ ረድኤቱ ከሁላችን ጋር ይሁን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን" ✝️💒✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል ነሐሴ 4/2018 ዓ/ም

📱 https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.tiktok.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://YouTube.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.Instagram.com/@Orthodox_tewahdo_nen
699002
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች logo
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች

26 de ago. de 2026, 09:58

Photo
ነሐሴ 3/2018
#ፆመ_ማርያም_3ኛ_ቀን
#እናታችን_ባዕታ_ማርያም

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በእናታችን #ማርያም ስም #በፆምና_በፀሎት ለምናመሰግንበት ለእናታችን ለአማላጃችን ለወላዲተ ቃል #ባዕታ_ማርያም ቤተ መቅደስ ለገባችበት ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

" ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ " ( መዝ.45፥4)

👉 #ባዕታ ማለት ባዕት ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን መግባት ማለት ነው ባዕታ ለማርያም ስንል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታኅሣሥ 3 ቀን ወደ #ቤተ_መቅደስ የገባችበት እለትን በመሆኑ ወር በገባ በ3ኛው ቀን የምናከብረው ታላቅ ቀን ነው

👉#ማርያም ማለት መርሕ ለመንግስተ ሠማያት ማለት ነው ወደ መንግስተ ሠማያት መርታ የምታስገባ ማለት ነው

👉 #ማርያም ማለት ፀጋ ወሀብት ማለት ነው ለሰው ልጆች ድህነት ምክንያት እንድትሆን ከአምላክ የተሰጠች ታላቅ ስጦታ ናትና

👉#ማርያም ማለት የሕያዋን እናት ማለት ነው

👉 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የስደት ልጅ በመሆኗ ቅዱስ እያቄምና ቅድስት ሃና #በቤተ_መቅደስ እንድታድግ ብለው በ3 ዓመቷ አምጥተዋት ለሊቀ ካህኑ ለዘካሪያስ አስረከቧት ነገር ግን ካህኑ ምን በልታ ታድጋለች ብሎ ቢጨነቅም መልአኩ ቅዱስ #ፋኑኤል ከሠማይ መናን እያወረደ እየመገበ 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ኖራለች

👉እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም #እግዚአብሔርን እያመሰገነች ለመላእክት እያገለገለች ሐርና ወርቅን እያስማማች እየፈተለች በንፅህና በቅድስና #በቤተ_መቅደስ በምስጋና ኖራለች

👉እርሱ ጌታችን #ክርስቶስ መርጧታልና ልክ 15 ዓመት ሲሆናት ከሲዖል የታሰርነውን እኛን ለማዳን ሲል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ 9 ወር ከ5 ቀን በማህጸኗ አደረ ተወልዶ አደገ

👉በዚህ ምድር ሲኖር አዳኛችን #ክርስቶስ ወንጌልን አስተማረ ምሳሌ ሆነ መከራን ተቀበለ በቀራኒዮ መስቀል ላይ ክቡር ደሙን አፈሰሰ ክቡር ሥጋውን ቆረሰ በእርሱ ሞት እኛን ነፃ አወጣን ክብርና ምስጋና ለስም አጠራሩ ይሁን ምስጋና ለድህነታችን ምክንያት ለሆነችው ለእናታችን #ባዕታ_ማርያም ይሁን

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለሀገራችን ሠላሙን ለህዝባችን ፍቅር አንድነትን ይስጥልን የእናታችን #ባዕታ_ማርያም ፍቅር በረከቷ ምልጃና ፀሎቷ ከኛ ጋር ይሁን መድኃኒታችን #ክርስቶስ #የእናታችን_ማርያምን ምስጋናዋን በአንደበታችን ፍቅሯን በልባችን ይሣልብን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ የመልአኩ #ቅዱስ_ፋኑኤል ጥበቃዉ የአባታችን #ዜና_ማርቆስ ፀሎትና ምልጃ አይለየን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን" ✝️💒✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል ነሐሴ 3/2018 ዓ/ም

📱 https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.tiktok.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://YouTube.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.Instagram.com/@Orthodox_tewahdo_nen
693005
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች logo
✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች

26 de ago. de 2026, 09:58

Photo
ነሐሴ 2/2018
#ፆመ_ፍልሰታ_ማርያም_2ኛ_ቀን

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በእናታችን ማርያም ምልጃና ፀሎት ቃል ኪዳን ይማረን ይራራልን ይቅር ይበለን

👉የኛ እናት #ማርያም ሁሌ ጠዋት ሲነጋና አይኖቼ ሲበሩ የመጀመሪያ ስራዬ ስዕልሽን ማየት ነው ልክ አይኖቼ ሲያዩሽ የሚሰማኝ ደስታ አለም ሁሉ በቀመሰው እላለሁ

👉የኔ #ማርያም በርግጥ አለም ብዙ የለህም የምትለኝ ነገር አለ እንደውም የምትነቅፈኝ የምትሰድበኝ የምትናገረኝ የምታስፈራራኝ ብዙ ነገር አለ

👉እኔ ግን ሁሌም #ሀያ_አራት_ሰዓት አንቺ አለም እኔኮ የንግስት ልጅ ነኝ ወደ አንቺ የመጣሁት ለትምህርት እንጂ ልኖርብሽ አይደለም አንቺ የኔ እኔም የአንቺ አይደለንም ደግሞስ እናቴ ልታደርግልኝ የማትቸለው ነገር እንደሌለ አንቺም እኔም እናውቃለን ነገር ግን ከአንቺ ለኔ የሚጠቅመኝ ምንም ነገር ስለሌለ ነው ዝም ያልኩሽ እላታለሁ

👉 #ማርያም እናታችን አሁንም ሆነ ወደ ፊት የአለምን ነገር አትስጪኝ ነገሩ ለአንቺ መንገር አይጠበቅብኝም ምክንያቱም እኔን ከራሴ በላይ ታውቂኛለሽ የነፍሴ ሰላሟንም ትረጂያለሽ

👉 #ማርያም እናታችን ሁሌም የሚገርመኝ የአንቺ መሆኔ ነው ይህ ለኔ ዘወትር የሚያስደስተኝና የሚያስደንቀኝ ነገር ነው ከዚህ ሌላ በዓለም ቀልቤን የሚገዛ ምንም ነገር የለም ሁሌም አንቺ የኔ እኔም የአንቺ ነኝ

👉ተፃፈ በትንሹ ሔኖክ

👉እናታችን #ወላዲተ_አምላክ_ማርያም ልጅሽ ወዳጅሽ አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ፀጋዉና ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን ምስጋናሽን በአንደበታችን ፍቅርሽን በልባችን ሳይብን አሳድርቢን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን"

👉ሰለሞን የገብርኤል ነሐሴ 2/2018 ዓ/ም

📱 https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.tiktok.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://YouTube.com/@Orthodox_tewahdo_nen - 📱 https://www.Instagram.com/@Orthodox_tewahdo_nen
821002

Showing 30 of 61 posts

Avaliação

Login necessário

Frequently Asked Questions

Sobre o que é o canal Telegram ✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች?+

✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች (@orthodox_pic21) é um canal Telegram listado em Religião no tgdio. Ranking, avaliações, reviews e posts recentes para decidir antes de assinar. Atualmente lista cerca de 48.308 inscritos no tgdio.

Como entrar em ✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች (@orthodox_pic21) no Telegram?+

Abra o perfil no tgdio e use Join / Open in Telegram para assinar @orthodox_pic21 de graça.

✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች é um bom canal de Religião?+

No tgdio você pode ver avaliação, reviews, ranking e posts de ✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች antes de entrar. Atualmente lista cerca de 48.308 inscritos no tgdio. Compare com canais similares de Religião.

Onde ver estatísticas e posts de ✞ ኦርቶዶክስ ምስሎች?+

No tgdio, abra @orthodox_pic21 para stats de inscritos, ranking, avaliações e posts. Use Stats para gráficos.