🩸የብልጽግና አገዛዝ በንፁሃን አማራዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የተሰጠ መግለጫ‼️
ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም
በአማራ ህዝብ ላይ ሁለንተናዊ ጦርነት የከፈተው የብልፅግና አገዛዝ ሲቪሊያንን ዒላማ ያደረገ ጥቃቱን እንደቀጠለበት ይገኛል። በዚህ ያልተቋረጠ የዘረ ፈጅ ጥቃት ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ በወለጋ፣ በሸዋ፣ በጎንደር እና በጎጃም ጠቅላይ ግዛቶች በንፁሃን አማራዎች ላይ ያነጣጠረ አሰቃቂ፣ በጅምላ የሚፈጸም የድሮን እና የከባድ መሳሪያ ጥቃት ፈፅሟል።
1ኛ) #በምስራቅ_ወለጋ_ዞን:-
ከሰሞኑ ተጠናክሮ በቀጠለው ጭፍጨፋ በጊዳ አያና ወረዳ:-
ፈንደቃ ፣ አንዶዴ፣ መንደር 3፣ መንደር 22፣ በጭበጭ ጊዮርጊስ እና መለከታ የተባሉ አነስተኛ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል። ከጥቃቱ የተረፈ ከ65ሺ በላይ ንፁሃን አማራወች በጫካ እየተሰቃዩ ይገኛለሉ።
በቀጠለው የብልፅግና ፀረ አማራ ጥቃት ጊዳ አያና ወረዳ - አሊ ከተማ በከባድ መሳሪያ ሰፈርን በመደብደብ፣ ከቤት መውጣት ያልቻሉ አረጋውያንን እና ታማሚዎችን ጨምሮ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ አቃጥሏል።
ኪረሙ ወረዳ - ወደሳ ዲማ ቀበሌ የ76 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ ንጹሃን አማራን ኢላማ ያደረገ ግድያ ዘረፋ እና ማፈናቀል ተፈፅሟል፤ በዚህ ጥቃት ምክንያት የቀበሌው ህዝብ ወደ ጫካ ተበትኗል።
2ኛ) #ደቡብ_ጎንደር
ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ላይ ደራ ወረዳ - ሳና ከተማ - ሳና 1ኛ ደ/ት/ቤት ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በመማር ላይ የነበሩ ከ15 በላይ ታዳጊ ተማሪዎች ተጨፍጭፈዋል። የ60 ዓመት አዛውንት የሆኑት የት/ቤቱ ጥበቃ አቶ እሸቴ ከበደ በከባድ ሁኔታ ቆስለዋል።
በተመሳሳይ በቀን ከረፋዱ 5:40 ላይ አንዳ ቤት ወረዳ - ወለሽ ከተማ በከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የነዋሪዎች ሱቆች ወድመዋል - ወጣት አበረ ክንዴ እና ወ/ሮ አህቴናት ደርብ ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል።
3) #ምስራቅ_ጎጃም_ዞን
ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ባሶ ሊበን ወረዳ - ሻይ ቤት በሻይ ቤት ቁጭ ባሉ ንፁሃን ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት አጉማስ ስማቸው፣ አብኔ፣ ይድነቅ መንግስቴ፣ ቁሜ አመራ፣ ከባድ መንበሩ የተባሉ ሲቪሊያን ተገድለዋል፤ አወቀ ጌታቸው እና ደርብ ላቀ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
4ኛ) #ደቡብ_ወሎ_ዞን:-
ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በሳይንት ደንሳ ወረዳ ባልታጠቁ ዜጎች አሰቃቂ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞ
አንዷለም ጌታቸው የተባለ የአማራ ባንክ ጥበቃ፣ ደረሰ መንግስቴ የተባለ የአቢሲኒያ ባንክ ጥበቃ፣ ቃልኪዳን ፍሰሃ የተባለች በዚህ ዓመት 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀች ተማሪ፣ ወይንሸት ላንተነው የተባለች የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ከተገደሉት መካከል ይገኙበታል።
እንዲሁም ደምሰው ንጉሴ እና ዘለቀ ኃይሌ የተባሉ የአማራ ባንክ ጥበቃወች፣ እያሱ አለሙ የተባለ የመኪና ረዳት፣ ሳባ አንባቸው የተባለች ሰላማዊ ነዋሪ፣ እሱባለው ንጉስ የተባለ የ8 ዓመት ህፃን፣ ሀና በቀለ የተባለች የአቢሲኒያ ባንክ ጥበቃ እና ስንታየሁ የተባለች በግል ስራ የምትተዳደር እናት ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ስማቸው እስካሁን ያልታወቀ ከ10 በላይ ንፁሃን የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል።
5ኛ) #ሸዋ_ጠቅላይ_ግዛት
ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ቡልጋ አውራጃ ፉራ እና ሲቻት ቀበሌዎች በድሮን፣ ሮኬት፣ BM፣ ሞርተር እና ዙ-23 በተፈጸመ ጥቃት ሚጣ እንዳለ የተባለች የ3 ዓመት ህፃን ጨምሮ 4 ሰዎች ተገድለዋል፣ 5 ከባድ ቁስለኛ ሲሆኑ እና ከ10 በላይ ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል።
እንዲሁም ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም
በአዊ ዞን ፋግታ ድማማ በተባለ ቦታ በሲቭሊያን መኖሪያ አካባቢ በተፈፀመ የጀት ድብደ በርካታ መንደሮችን ሲያወድም 10 የአርሶ አደር ከብቶችንም ገድሏል ።
#የአፋብን_መልዕክት
ይህ ከትምህርት ቤት እስከ ባንክ፣ ከሻይ ቤት እስከ መኖሪያ ቤት ድረስ የሚፈጸመው ጥቃት የአማራን ህዝብ ዘር ለማጥፋት የታቀደ የመጨረሻው የፋሽስታዊ የጥፋት ዘመቻ ነው። አገዛዙ ንፁሃንን በምድር በታንክና መድፍ፣ በሰማይ ደግሞ በድሮን እየጨፈጨፈ ይገኛል።
በመሆኑም:-
1ኛ) ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ፣ ለEU፣ ለUN እና ለሰብአዊ መብት ተቋማት ጥሪያችን በሲቪል ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የድሮን ጦርነት በገለልተኛ አካል እንዲያጣራ እንጠይቃለን፣
2ኛ) የሰብአዊ መብት ተቋማት እና የረድኤት ድርጅቶች በአገዛዙ ጥቃት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ሲቪሊያን አስፈላጊውን የሰብአዊ እርዳታ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፤
3ኛ) ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና የአማራ ህዝብ አገዛዙ ሀገራችንን በጦርነት ቀውስ ውስጥ በማስገባት የሲኦል ምድር ከማድረግ ወደ ኋላ የማይል የሽብር መንግስት በመሆኑ ሁለንተናዊ ትግል በማድረግ ብልፅግና አገዛዝን በማስወገድ የሰላም አየር እንድንተነፍስ እና ሀገራችንን ከፈፅሞ መጥፋት እንድንታደግ ጥሪ እናቀርባለን።
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም
@NISIREamhra