️ ንስር አማራ🦅 Telegram channel photo

️ ንስር አማራ🦅

@nisireamhraPublic Channel

የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ። 💚💛❤️ እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhra2 @NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅 ንስር ዐማራ🦅 #የግፉአን_ድምፅ t.me/NISIREamhra

MemesportuguêsBrasil

9.1k

Last views

68.2k (68,237 subscribers)
Membros
—
Rating
62
Total Posts
Oct 20, 2026, 4:03 PM
Atualizado
Mar 29, 2026
Created
Stats

Você está vendo conteúdo em português. Para ver conteúdo em outros idiomas, mude o idioma do site.

Channel Information

Channel Information
Channel Name️ ንስር አማራ🦅
Username@nisireamhra
CategoryMemes
Languageportuguês
CountryBrasil
Membros68,237
Channel TypePublic Channel
Created29 de mar. de 2026
Last Updated20 de out. de 2026 • ontem
StatusActive

Classificação

Classificação Global
#49937-3798
Classificação por Idioma
#1001-43
Classificação por Categoria
#1397-121

Crescimento de Participantes

Total: 68.2K30 Days growth: +3.7K5.8%
09/2109/2610/0110/0610/1110/1610/20
Crescimento de Participantes - 30 Days
DateSubscribers
21:09:202664,492
22:09:202664,492
23:09:202664,492
24:09:202664,492
25:09:202664,492
26:09:202664,492
27:09:202664,492
28:09:202664,492
29:09:202664,492
30:09:202664,492
01:10:202664,492
02:10:202664,492
03:10:202664,492
04:10:202664,492
05:10:202664,492
06:10:202664,492
07:10:202664,492
08:10:202664,492
09:10:202664,492
10:10:202664,492
11:10:202664,492
12:10:202664,492
13:10:202668,180
14:10:202668,180
15:10:202668,180
16:10:202668,180
17:10:202668,180
18:10:202668,180
19:10:202668,180
20:10:202668,237
Crescimento de Participantes - Weekly
DateSubscribers
Week of 23:03:202662,612
Week of 30:03:202662,593
Week of 06:04:202662,765
Week of 13:04:202662,618
Week of 20:04:202662,539
Week of 27:04:202662,539
Week of 04:05:202662,539
Week of 11:05:202662,810
Week of 18:05:202662,810
Week of 25:05:202662,810
Week of 01:06:202664,349
Week of 08:06:202664,349
Week of 15:06:202663,782
Week of 22:06:202663,564
Week of 29:06:202663,564
Week of 06:07:202663,564
Week of 13:07:202663,356
Week of 20:07:202663,693
Week of 27:07:202663,816
Week of 03:08:202663,816
Week of 10:08:202663,816
Week of 17:08:202663,898
Week of 24:08:202664,075
Week of 31:08:202664,014
Week of 07:09:202664,014
Week of 14:09:202664,492
Week of 21:09:202664,492
Week of 28:09:202664,492
Week of 05:10:202664,492
Week of 12:10:202668,180
Week of 19:10:202668,237
Crescimento de Participantes - Monthly
DateSubscribers
March 202662,612
April 202662,539
May 202662,810
June 202663,564
July 202663,693
August 202664,075
September 202664,492
October 202668,237
Crescimento de Participantes - Yearly
DateSubscribers
202668,237

Top 10 posts

Most viewed posts from this channel

By views
  1. #1🔥በወገል ጤና ከተማ ላለፉት አራት ቀናት ከባድ የከበባ ማጥቃት ሲያካሂድ የቆየው ጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝ በ19.0K
  2. #2🔥#አርበኛ_ዘመነ_ካሴ_ከግምባር‼️18.7K
  3. #3🔥ወረዳውን ዘርፎ የተሰደደው የብልፅግና ከፍተኛ አመራር በተሰደዱበት ከተማ በመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች18.1K
  4. #4🔥"ለአብይ ወንበር የረገፈው ወጣት አስከሬን መቅበር ከሰው አቅም በላይ በመሆኑ በእስካቫተር ማሽን እየተቆፈረ 17.8K
  5. #5🔥#የአገዛዙ_ሰራዊት_አባላት_በጅምላ_ተቀበሩ‼️ አፋብን ምኒሊክ 1ኛ ዕዝ በምስራቅ ግንባር ደላንታ እና ተሬ በ17.6K
  6. #6🔥#የአገዛዙ_ሰራዊት_አባላት_በጅምላ_ተቀበሩ‼️17.4K
  7. #7🔥#የደግፉኝ_ተማፅኖ‼️17.3K
  8. #8🔥#የድል_ዜና‼️17.2K
  9. #9🔥የብልፅግናን ፀረ-ሕዝብ አገዛዝ ውድቀትን የተረዱ በርካታ የሚሊሻ አመራርና አባላት የህልውና ትግሉን እየተቀላ16.0K
  10. #10Post #3075415.2K

Últimos Posts

️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

17 de out. de 2026, 22:47

Photo
🔥#ምርኮኛው_ከመማረኩ_በፊት😂😄

ምርኮኛው የመሀልሜዳ ከንቲባ 😂
9,07000130
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

17 de out. de 2026, 21:03

Photo
🔥#ሰበር_ዜና‼️

​የመንዝ ጌራ ወረዳ መሀል ሜዳ ከተማ ከንቲባ እና የሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ኃላፊው በጀግናው ሠራዊታችን ቁጥጥር ሥር ዋሉ።

​ጥቅምት 7 /2019 ዓ.ም.

​በጀብደኛው አፋብን አሳምነው 5ኛ ዕዝ የመሀል ሜዳ ከተማ ከንቲባ እና የሰላምና ደህንነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተማረኩ።

​ አሳምነው 5ኛ ዕዝ መሀል ሜዳ ከተማን ተቆጣጥሮ እያስተዳደረ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም በመሐል ሜዳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ቢሮ በመግባት የሕዝብ ዶክመንቶችን በክብር ከጠበቀ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ምስሎች አውርዶ መቅደዱ ይታወሳል።

​ከንቲባውና የሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ኃላፊው ለማምለጥ ሙከራ ባደረጉበት ወቅት፣ እነሱን ለማውጣት ጠላት በከባድ መሣሪያ ጫና ለመፍጠር ሞክሮ ነበር። ይሁን እንጂ የመጣው የጠላት ኃይል በጀግናው ሠራዊታችን ጠንካራ ክንድ ተመቶ ሳይሳካለት ቀርቷል፤ እነዚህን :-
👉1) አስር አለቃ አያሌው ጣሰው (የሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ኃላፊ)
👉2)ጌታቸር ባይሳሳሁ (የመሀል ሜዳ ከንቲባን) የብልጽግና አመራሮችን ጀግናው ምኒልክ ክፋለጦር በቁጥጥር ሥር ማዋል ችሏል። ከንቲባውና ባልደረባው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሰማው ሕዝብም ደስታውን እየገለጸ እንደሚገኝ የግንባር መረጃችን አክሎ ገልጿል።

​ሕዝብን በማስጨፍጨፍ ከአማራ ሕዝብ ትግል ማምለጥ አይቻልምና ሌሎች አመራሮች፣ ሚሊሻዎች፣ የአድማ ብተና አባላት እና ፖሊሶች እጃችሁን ለፋኖ ስጡ።

​ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

©​አፋብን አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!!

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጥቅምት 07/2019 ዓ.ም
@NISIREamhra
12,10000187
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

17 de out. de 2026, 12:24

Photo
🔥የብልፅግናን ፀረ-ሕዝብ አገዛዝ  ውድቀትን የተረዱ በርካታ የሚሊሻ አመራርና አባላት የህልውና ትግሉን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ‼️

           ጥቅምት 07/2019 ዓ.ም
        ----------//------------//-----

የብልፅግና አገዛዝ ስርዓትን ሲያገለግሉ የቆዩት በርካታ የሚሊሻ አባላትና የመከላከያ አባል አፋብን አሳምነው 5ኛ ዕዝን በክብር መቀላቀላቸው ታወቀ።

ለሕዝባዊ ትግሉ እጃቸውን የሠጡት የአገዛዙ ሠራዊት አባላት እንደገለፁት፡ ሠሞኑን በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከፋኖ ጋር በነበረው ከባድ አውደ ውጊያ፣ የብልፅግና ስርዓት የተደመሰሱበትን የሠራዊት አባላት በጅምላ በአንድ ጉድጓዳ ሕዝብ እዳያያቸው በማለት ሲቀብር ስናይ፣ ፀረ-ሕዝብ መሆኑንና ለራሱ ሠራዊትም ክብርና ሞራል የሌለው መሆኑን በማረጋገጣችን ነው ብለዋል።

ወደ አፋብን አሳምነው 5ኛ ዕዝ አፄ አምደጽዮን ኮር አፄ ምኒልክ ክፍለ ጦርን የተቀላቀሉት 16 የሚሊሻ አባላትና 1 የመከላከያ አባል እደገለፁት፡ ስርዓቱ በጭካኔ ሲገዛን ፋኖ ግን በክብር ተቀብሎናል ሲሉ ገልፀዋል። ሕዝባዊ ትግሉን ለምትቀላቀሉ ሁሉ ፋኖ በክብር የሚቀበል መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።


     ➠ የተቀላቀሉ አባላት፦
1. መኮንን አየለ----- አባል        
2. ናይ ኃይለጊዮርጊስ-----አባል
3. ጣልባቸው ተክሌ------አመራር    
4. ወ/አማኑኤል ሸዋረጋ----- አባል
5. ኃ/ሚካኤል ወ/ጊዮርጊስ-----አባል
6. ጋረደው በላይሁን-------አባል         
7. ዘውዴ በላይነህ-------አባል             
8. ገብሬ ሙላት-----አባል                 
9. ወልዴ ገ/መድኅን------አባል          
10. አለሙ ማሞ------አባል              
11. ወንዶሰን ተፈራ--------አባል           
12. አስፋው ሸዋንጣስ-------አባል       
13. ተረፈ ሸዋታጠቅ-------አባል        
14. አደፍርስ ተጋፋው--------አባል         
15. ያሬድ ታለ-------አባል                   
16. ሸገኔው ፋንታሁን-------አባል        
17. ታየረ ትስፍተወልድ-------አባል
18. አማን ሳሚ-------- የመከላከያ አባል

➠ ይዘው የተቀላቀሉት ንብረት፦
   ✔ 4 ሁለት እግር ክላሽኮቭ መሳሪያ
   ✔ 7 SKS መሳሪያ
   ✔ 1 የመኔ ክላሽኮቭ መሳሪያ
በጠቅላላ=> 12 መሳሪያ በመያዝ ተቀላቅለዋል።


" ክብር ለትግሉ ሠማዕታት!
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

©አፋብን አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!!

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጥቅምት 07/2019 ዓ.ም
@NISIREamhra
16,00000185
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

17 de out. de 2026, 00:22

🔥#የደግፉኝ_ተማፅኖ‼️

የአገዛዙ ኃይል በነገው ዕለት ቅዳሜ ማለትም (በጥቅምት 07/2019 ዓ.ም) በተለያዩ የአማራ ቀጠናዎች ገቢያ ቀኖችን ለመጠቀም በማሰብ የብልፅግና የድጋፍ ሰልፍ ሊያደርግ በግዴታ ጠርቷል።

ለአብነትም በጋሸና እና በኮን ከተማ ነገ 12 ስዓት ጀምሮ ለመንግስት ድጋፍ አድርጉ ተብሎ ተገዷል መንግስት ሰራተኛው በተለይ መምህሩ በግዴታ እንዲወጣ አስገዳጅ መልክት እየተላከ እንደሆነ የንስር አማራ ምንጮች ገልፀዋል።

አስገዳጁ ሰልፍ እንድትገኙ በማለት የማስጠንቀቂያ መልዕክት እየላካችሁ የምታስገድዱ አካለት ር/መ/ር ፣ሱፐርቫይዘር አርፋችሁ ተቀመጡ ስንል እናስጠየቅቃለን!!

በሰይፍ ዘመን ሰልፍ የለም!

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም
@NISIREamhra
17,30000177
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

16 de out. de 2026, 20:49

Photo
🔥#አርበኛ_ዘመነ_ካሴ_ከግምባር‼️

ለአገዛዙ ቅዤትና ራስ ምታት የሆነው አርበኛ ዘመነ ካሴ ጎጃም ነው ሲባል ቤንሻንጉል ፤ ጎንደር ነው ሲባል ወሎ ፣መቀሌ ነው ሲባል * ፤ ገለነዋል ሲባል 4ኪሎን ሊረከብ ከጓዶቹ ጋር ሲተም ታገኘዋለህ💪

የአማራን ብሎም የኢትዮጲያን ህዝብ ከአሸባሪው ብልፅግና አገዛዝ ነፃ ሳያወጣ፣ ፍትህና እኩልነት ሳያሰፍን ጉዞውን ለሰከንድ የማያቆመው እረፍት የለሹ መሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ዛሬም ከጓዶቹና ከጀግናዊ የፋኖ ሰራዊት በጋራ በመሆን ስራ ላይ ነው።

#በታች ነው ሲሉት #በላይ_ዘለቀ💪 ማለት አሁን ነው። #በርታለን_መሪያችን_አርበኛ_ዘመነ_ካሴ‼️

ገደልነው ያላችሁ የብልፅግና ሚዲያ ሚሊሾች አላችሁ😁

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም
@NISIREamhra
18,70000324
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

16 de out. de 2026, 20:11

Photo
🔥ወረዳውን ዘርፎ የተሰደደው የብልፅግና ከፍተኛ አመራር በተሰደዱበት ከተማ በመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ትዕዛዝ ታሰሩ‼️

ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም

ሰሞኑን ጀግናው የአፋብን አሳምነው 5ኛ ዕዝ ባካሔደው መጠነ ሰፊ ጠንካራ መብረቃዊ ኦፕሬሽን በሸዋ በርካታ የወረዳ ከተሞች በፋኖ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ በመርሀቤቴ አውራጃ የሚዳ ሬማ ወረዳ የብልፅግና አመራሮች ከፍተኛ የዘረፋ ተግባር ፈፅመው ወደ አጎራባች አለም ከተማ መሸሻቸው ይታወቃል።

ስደተኞቹ የህዝብ ሀብትና ንብረት ዘራፊዎች የሚዳ ሬማ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች የሆኑትና የወረዳው ዋና አስተዳደር ኃላፊ አቶ ሰይድ ኢብራሒም እንዲሁም ከባህል ተወዛዋዥነት ወደ ከፍተኛ የብልፅግና ፓርቲ አመራርነት ያደገው የወረዳው ምክትል አስተዳደር ኃላፊ አቶ አባይነው ወንዶሰን ወረዳው ላይ የፈፀሙት ከፍተኛ ዝርፊያና ወንብድና የህዝብ ልጅ በሆነው ጀግናው የአማራ ፋኖ መጋለጡን ተከትሎ በሸሹበት መርሀቤቴ አለም ከተማ በመከላከያ ከፍተኛ አመራር ትዕዛዝ ሰጭነት መታሰራቸው ተረጋግጧል።

ለመሆኑ ጀግናው ሰራዊታችን በታላቅ ህዝባዊ አቀባበልና ድምቀት ወደ መራኛ ከተማ እና ሬማ ከተማ ሲገባ በብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች የተዘረፉ የወረዳው ማህበረሰብ ሀብትና ንብረቶችን በዝርዝር ይዞ የሚመጣ መሆኑን የአፋብን አሳምነው 5ኛ ዕዝ የአፄ ዓምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ከወዲሁ ለመላው ሰራዊታችንና ህዝባችን መግለፅ ይወዳል።

#የብልፅግና_አመራሮች_መጨረሻ😂

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም
@NISIREamhra
18,10000121
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

16 de out. de 2026, 19:31

Photo
🔥#የድል_ዜና‼️

የአሸባሪው ስርዓት የአፈና ኦፕሬሽን በነፃነት ታጋይ የተራራው ራስ ጉና እና አንበሳው ጋይንት ክ/ጠር አናብስቶቹ በመልሶ ማጥቃት ድል ተጠናቀቀ።
ቀን 6/2/2019 ዓ/ም

በዛሬው ዕለት የአሽባሪውና አማራ ጠሉ ስርዓት ከክምር ድንጋይ ከተማ በሌሊት ወደ ላይ ጋይንት ወረዳ በመጓዝ ጥጥራ ከሚባለው ቦታ ላይ ከጠዋቱ 1:00 ደፈጣ በመያዝ በተደረገ አውደ ውጊያ የአፋብን 3ኛ በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር እና አንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር ለኬላ የወጡ አባላትን አፍኖ ከበባ ውስጥ በማስገባት ለመደምሰስ ያደረገው ሙከራ ከሽፎና ኪሳራ አስተናግዶ ተመልሷል።

ይህ አሸባሪና ህዝብ ጠል የሆነው ስርአት ከጉና በጌምድር ወረዳ ክምር ድንጋይ ከተማ በመነሳት በሌሊት ተጉዞ ለማፈን ባደረገው ሙከራ የተራራው ራስ ጉና እና የአንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር ክንደ ብርቱ የነፃነት ታጋይ ነበልባሎች ከበባውን በመስበር የመልሶ ማጥቃት አፀፋውን በመስራት የጠላት ሀይልን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ በተጨማረም ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንዲያሰተናግድ በማድረግ ታላቅ ጀብድን ፈፅመዋል።

በመጨረሻም የጠላት ሀይል የሀይል ጭማሪ ቢያደርግም የአናብስቶችን ምት መቋቋም ባለመቻሉ እየፈረጠጠ ወደ ቦታው አስከሬኑን እየጉተተ ተመልሷል ሲል አርበኛ ጌትነት ሲሳይ (የተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ) ለንስር አማራ ገልጿል!

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም
@NISIREamhra
17,20000126
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

16 de out. de 2026, 15:10

Video
🔥"ለአብይ ወንበር የረገፈው ወጣት አስከሬን መቅበር ከሰው አቅም በላይ በመሆኑ በእስካቫተር ማሽን እየተቆፈረ በጅምላ እየተቀበረ ይገኛል‼️

አንድ ሦስተኛውን እንኳን እስከሁን መቅበር አልተቻለም። በጣም በርካታ የብልፅግና መከላከያ ሠራዊት አስከሬን ነው የወደቀው።

እስካሁን ከ16 በላይ የጅምላ ጉድጓዶች በእስካቫተር ማሽን ተቆፍረው የአገዛዙ ወታደሮች አስከሬን በጅምላ የተቀበሩ ሲሆን ቢያንስ በአንድ ጉድጓድ ከ12 እስከ 17 ወታደር በጅምላ ተቀብሯል።

ገና አስከሬን ተሰብስቦ አላለቀም።"

#ማሳሰቢያ:-

በዬትኛውም ቀጠና ከአገዛዙ ጎን የተሰላፋችሁ ኢትዮጵያዊ #ለፋኖ_እጅ_በመስጠት ወድ ህይዎታችሁን አትርፉ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን‼️

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም
@NISIREamhra
17,80000190
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

16 de out. de 2026, 14:58

Video
🔥#የአገዛዙ_ሰራዊት_አባላት_በጅምላ_ተቀበሩ‼️ አፋብን ምኒሊክ 1ኛ ዕዝ በምስራቅ ግንባር ደላንታ እና ተሬ በወሰደው መብረቃዊ ጥቃት በርካቶች መደምሰሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል። የተደመሰሱ የአገዛዙ ወታደሮች በርካታ በመሆናቸው አስከሬናቸው በእሳካቫተር ማሽን እየታፈሱ በጅምላ ተቀብረዋል‼️ አገዛዙ የድሀን ልጅ በግዳጅ አፍሶ እያመጣ ስልጣኑን ለማስጠበቅ አማራ ምድር ላይ እንደ ቅጠል እያረገፈው ይገኛል።…
17,60000146
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

16 de out. de 2026, 14:51

Video
🔥#የአገዛዙ_ሰራዊት_አባላት_በጅምላ_ተቀበሩ‼️

አፋብን ምኒሊክ 1ኛ ዕዝ በምስራቅ ግንባር ደላንታ እና ተሬ በወሰደው መብረቃዊ ጥቃት በርካቶች መደምሰሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል። የተደመሰሱ የአገዛዙ ወታደሮች በርካታ በመሆናቸው አስከሬናቸው በእሳካቫተር ማሽን እየታፈሱ በጅምላ ተቀብረዋል‼️

አገዛዙ የድሀን ልጅ በግዳጅ አፍሶ እያመጣ ስልጣኑን ለማስጠበቅ አማራ ምድር ላይ እንደ ቅጠል እያረገፈው ይገኛል። ኢትዮጵያዊያን እምቢኝ በማለት ልጆቻች ታፍሰው እየሄዱ ወድቀው ተመቅረት አድኗቸው ‼️

#ማሳሰቢያ:-

በዬትኛውም ቀጠና ከአገዛዙ ጎን የተሰላፋችሁ ኢትዮጵያዊ #ለፋኖ_እጅ_በመስጠት ወድ ህይዎታችሁን አትርፉ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን‼️

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም
@NISIREamhra
17,40000163
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

16 de out. de 2026, 00:05

Photo
🔥በወገል ጤና ከተማ ላለፉት አራት ቀናት ከባድ የከበባ ማጥቃት ሲያካሂድ የቆየው ጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝ በጠላት ላይ እጅግ ከፍተኛ ኪሣራ በማድረስ አንፀባራቂ ድል ተቀዳጀ‼️

የትብብር ለሕልውና አካል የሆነው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝ በምስራቅ ግንባር አኩሪ ገድል ፈፅሟል።

በምኒልክ 1ኛ ዕዝ 102ኛ እና 16ኛ ኮሮች የተወጣጡ ውስን አሃዶች በጠላት 11ኛ ዕዝ ስር የምትገኘው 16ኛ ክፍለጦርን በማዘዣ ጣቢያዋ ወገልጤና ቻይና ካምፕ ላይ ለአራት ቀናት በመቁረጥ በወሰደው እርምጃ ክፍለጦሯን መበታተን ችሏል።

አገዛዙ ከሰው አልባ ተዋጊ ድሮን ጀምሮ የጦር ጄትና ሌሎች ሜካናይዝ መሣሪያዎችን ተጠቅሞ ከበባውን ለመስበር ያደረገው ሙከራ ከሽፎ ጦሩ የአፈር ሲሳይ ሆኖ ቀርቶበታል።

በተጨማሪም ይሄንን ከበባ ለመስበር መነሻቸውን ከተንታ አጅባር ያደረጉ በ11ኛ ዕዝ 204ኛ ኮር ከ35ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ እና 3ኛ ሬጅመንቶች እንዲሁም ከ84ኛ ክፍለ አንዲት ሬጅመንት ይዞ ለመግባት ቢሞክርም፡ ነገር ግን በዕዙ አርበኞች ተቆርጦ ሁለቱ ሬጅመንቶች ሙሉ በሙሉ ሲደመሰሱ አንድኛው ሬጅመንት በ101ኛ ኮር አናብስቶች ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበት ተበታትኗል።

ደላንታ ላይ ተቆርጣ ጥብቅ እርምጃ የተወሰደባት 16ኛ ክፍለጦር ከውስን አሃዶቿ በስተቀር ስትደመሰስ አንድ ዙ23ን ጨምሮ ሌሎች ሜካናይዝድ መሣሪያዎቿንና ወታደራዊ ንብረቷን ማውደም ተችሏል።

በተጋድሎው ከተደመሰሱ የክፍለጦሯ ወታደሮች መካከል አንድ ኮሎኔልን ጨምሮ ማዕረጋቸውን ለጊዜው በውል መለየት ያልተቻለ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንደሚገኙበት ለማረጋገጥ ተችሏል።

በውጊያው ከፍተኛ ኪሳራ የተከናነበው የአገዛዙ ኃይል ከትናንት ጥቅምት 04/2019 ዓ/ም ምሽት ጀምሮ ወገልጤና ከተማን በድሮን ሲደበድብ አድሮ የዋለ ሲሆን በተጨማሪም ተዋጊ ሚግ በመጠቀም ከተማዋንና በዙሪያዋ የሚገኙ የእርሻ ሰብልና የንፁኋን መኖሪያ ቤቶችን አውድሟል።

በዚህም ህፃናትን ጨምሮ ንፁኋኖችን በገፍ ገድሏል፣ የቤት እንስሳትን ጨፍጭፏል እንዲሁም ሀብት ንብረት አውድሟል።

ከምስራቅ ግንባር አስተባባሪዎች የተሰጣቸውን ተልዕኮ በድል ያጠናቁት የጀብደኛው 1ኛ ምኒልክ ዕዝ አሃዶች በአሁን ሰዓት ስትራቴጂክ ቦታዎችን በመቆጣጠር ተጨማሪ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በመፈፀም ላይ ናቸው ሲል ዕዙ በህዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም
@NISIREamhra
19,00000229
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

11 de set. de 2026, 03:57

🔥#ሰበር_ቪዲዮ‼️

በአፋብን ምንሊክ 1ኛ ዕዝ መብረቃዊ ጥቃት 12ኛ ዕዝ ይኮራባትና ይተማመንባት የነበረችው 71ኛ ክ/ጦር ወሎ ቤተ አማራ ቀጠና ከገባች 24 ሰዓታት ሳይሞላት ዳውንት ግንባር ላይ እንደ በረዶ ቀልጣ ከቀረችው ክፍለ ጦር እድለኛ ሆነው #ከተማረኩ #ምርኮኞች ጋር የተደረገውን ቆይታ በንስር አማራ የዩቱዩብ ገፅ ይመልከቱ‼️

ምርኮኞችን ምን አሉ ? ለአብይ አህመድና ጓዶቹ ይድረስ‼️

ቪዲዮ ለመመልከት ማስፈንጠሪያ link ይጫኑ የንስር አማራ የዩቲዩብ ገፅ ይወዳጁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/agIy8KI2344?si=NPJPrAG483D6QBri
Video Thumbnail
417003
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

11 de set. de 2026, 03:57

አባታችን ተማርኳል ፣እኛም ተደግመናል!
#ምኒልክ_ዕዝ_ይችላል💪

ወሎ ቤተ-አማራ ቀጠና 24 ሰዓት የሞላ ሳትቆይ ደላንታ ዳውንት ላይ በአፋብን ምኒሊክ ዕዝ ሙሉ በሙሉ ከተደመሰሰችው 12ኛ ዕዝ 71ኛ ክፍለ ጦር በምርኮ የተረፉ ወታደሮች ካደረጉት መፈክር የተወሰደ...!

#ቀሪህም_እጅ_ስጥ_እየመጡ_ነው‼️

ከምርኮኞች ገር የተደረገ ቆይታ ንስር ዩቲዩብ ላይ ይመልከቱ👇👇👇👇
https://youtu.be/agIy8KI2344?si=NPJPrAG483D6QBri

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጳጉሜ 05/2018 ዓ.ም
Video Thumbnail
4,6200079
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

11 de set. de 2026, 03:57

፭) ለአገዛዙ የሰቆቃ ሰላባወች:-
በዚህ አዲስ ዓመት መባቻ ላይ፣ በትግላችን ማዕከል የምናስባቸው እና የደማቸው ጥሪ የሚያስቆጣን ወገኖቻችን መኖራቸውን አንዘነጋም።

​በሃይማኖታቸው ምክንያት መከራና ሰቆቃ እየደረሰባቸው ያሉ የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ ቤተ-እምነቶቻቸው ሲደፈሩ እና ሲቃጠሉ የታገሱት የመከራ ፅዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ነዉ።

​በየማጎሪያው ያለ ፍርድ በበቀል እና በተረኝነት ስሜት የታጎሩ የፖለቲካ እና የማንነት እስረኞች፣ በማሰቃያ ክፍሎች ውስጥ አካላቸው የጎደለ እና ህይወታቸው ያለፈ ወገኖቻችን ፍትህ የማግኘት መብታቸውን ማስከበር የትግላችን አንዱ ግብ ነው።
​
በልማት ስም ከቀያቸው የተፈናቀሉ፣ ንብረታቸው የወደመባቸው፣ የአገዛዙን ጥቃት በመሸሽ ስደት ሀገር የሚሰቃዩ ወገኖቻችን ወደ ቀደመ ቀያቸው ተመልሰው በክብር እና በነፃነት የሚኖሩበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንታገላለን።

በመጨረሻም

ትግላችን የህልውናችንን ዋስትና በብረት ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፣ የሁሉም ብሔሮችና ብሔረሰቦች እኩልነት፣ ህግ የበላይነት እና ፍትህ የሰፈነባትን፣ የትኛውም ዜጋ በቋንቋው እና በማንነቱ የማይገፋባትን ከነባር ስልጣኔዋ፣ ታሪካ እና ባህሏ ያልተቃረነች ፍትሃዊ ኢትዮጵያን የመገንባት ስልታዊ ግብ አለው።

ያለፈው አመት ለአማራም ሆነ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ወሳኝ የሆነ ዕድል ተፈጥሯል፤ የያዝነው አመት ደግሞ ይህን የትብብር ዕድል ተጠቅመን ህልውናችንን የምናረጋግጥበት፣ የጠላት የማጥፊያ አቅሞቹን ሰብረን በአሸናፊነት በአዲስ ፖለቲካዊ መድረክ ሀገርን ወደ ተሟላ እና ዘላቂ ሰላም ለማሸጋገር የምንሰራበት ይሆናል።

በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ!

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጳጉሜ 05/2018 ዓ.ም
5,9200059
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

11 de set. de 2026, 03:57

መስከረም 01/ቀን 2019 ዓ.ም

መላው የአማራ ህዝብ እና ኢትዮጵያዊያን፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አመራርና አባላት፣ የብልፅግናን አገዛዝ በየግንባሩ የምትታገሉ ፀረ ብልፅግና ኃይሎች፣ አፍሪካውያን ወንድሞቻችንና ለመላው የዓለም ሕዝብ፤ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) እንኳን ለ2019 ዓ.ም አደረሳችሁ፣ አደረሰን ይላል!

ሀገራችን ኢትዮጵያ አዲሱን ዓመት እየተቀበለች ያለችው የቀውስ አገዛዙ በነደፈው የጥፋት ፕሮጀክት ምክንያት ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ውስጥ ሆና ነው። የህዝባቸውን ህልውና ባስቀደሙ ብሔራዊ ኃይሎች እና በኢትዮጵያዊነት ላይ ሁለንተናዊ አደጋ በደቀነው የአገዛዙ ኃይል መካከል በሚደረግ ጦርነት ምክንያት በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የእልቂት እና የቀውስ ምዕራፍ ውስጥ እንገኛለን። ከሀገራዊ ቀውሱ ባሻገር ብልፅግና በጎረቤት ሀገራት የውስጥ ሰላም ላይ ጭምር በደቀነው አደጋ ምክንያት የቀይ ባህር ከባቢን ጨምሮ የቀጣናው መልክዓ ፖለቲካ በዘላቂ አለመረጋጋት ውስጥ እንዲገባ ሆኗል።

እንደ ሀገር ሙሉ ሉዓላዊነታችንን ለታዳጊ ኢምፔሪያሊስቶች በማከራዬት ኢትዮጵያን ተላላኪ መንግስት ያደረገው አረመኔያዊ አገዛዝ የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘም ብቻ የውስጥ ጦርነቶችን ከማፋፋም አልፎ፣ አደገኛ ቀጣናዊ ቀውሶችን እያወለደ አገሪቱን ወደማያባራ ቀጠናዊ ጦርነት በመምራት ወደ ጥልቁ ገደል ለመክተት እየተንደረደረ ይገኛል። ዘመኑ ባፈራቸው የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ሁሉ ንጹኃንን በድሮን መደብደብ፣ በታሪካዊ ከተሞችና በሃይማኖት ቦታዎች ላይ ከባድ መሣሪያ በመተኮስ፣ ኢትዮጵያዊያንን በማንነታቸው ማሳደድ፣ ማሰርና ማፈናቀል የአገዛዙ መገለጫዎች ከሆኑ ውለው አድረዋል።

አገዛዙ የኢትዮጵያንን ማንነት እና ወጥ ስልጣኔ ምልክት የሆነውን ዘመን መለወጫን ጊዜን ለመለወጥ በምክክር ኮሚሽን ስም አጀንዳ በማድረግ ከኢትዮጵያዊ ማንነታችን እና ከታሪካችን ጋር የተጋጨ መሆኑንም አሳይቶናል።

በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነው ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ ስሁት ትርክትን እና አጥፊ ፖሊሲዎችን እና ስልቶችን መነሻ ያደረገም ጭምር መሆኑ ይታወቃል።

የአማራ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ያደረገውን ሰላማዊ ትግል እና የለውጥ ተስፋ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ስልጣን ላይ የወጣው አገዛዝ የአማራን ሕዝብ ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት ሁሉን አቀፍ ጦርነት እያደረገ ይገኛል። ለጨቋኞች ተንበርክኮ የማያውቀው የአማራ ሕዝብም የአገዛዙን የህልውና አደጋ ቀንበር ለመስበር በጽናት መራር ትግል እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ዘርፈ ብዙ ድሎችንም ማስመዝገብ ችሏል።

የጠላትን ወረራ በመመከት የተደረጉት ወታደራዊ ተጋድሎዎች በጦረኝነት ለወረራ የመጣውን ሰራዊት የውጊያ አቅም እና ሞራል በተደጋጋሚ መስበር ችለዋል።

በዚህም የአማራ ህዝብ በመሪ ድርጅቱ አማካኝነት የገጠመውን የዘር ማጥፈት ጦርነት እየመከተ ይገኛል። ባለፈው አመት በተለያየ ቦታ የተገኘቱት የውጊያ ድሎች ባሻገር በተለይ በስልጠና ዘርፍ የታየው ሽህ ክንዶችን በአንዴ አሰልጥኖ ማስመረቅ የተቻለበት በመሆኑ በትግሉ ወቅት ትልቅ አቅም መጨመር ችሏል።
ከእነዚህ እና መሠል ድሎች ባሻገር 2018 አመት ምህረት በአማራ ህዝብ ትግል ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ድሎችም ተመዝግበዋል።

፩. የአፋብን ውልደት
ትግሉ ባልተማከሉ አደረጃጀቶች ውስጥ መቆዬቱ የራሱ ታክቲካዊ ፋይዳ የነበረዉ ቢሆንም አቅምን የሚከፋፍል በመሆኑ የአደረጃጀት አንድነትን ማረጋገጥ ግዴታ ነበር።
የአማራ ህዝብም በታሪኩ እና በትግል ሂደቱ መራር በሆነ መንገድ የተረዳው ተጨባጭ እውነት ቢኖር አንድነት መተኪያ የለሽ ስትራቴጂካዊ አቅም መሆኑን ነው።

በአማራነት የመደራጀትና የመታገል ጉዳይ ግለሰባዊ እና ጠባብ ቡድናዊ ፍላጎትን፤ ትናንሽና መለስተኛ ቅራኔና ፀብን፥ ኩርፊያና ልዩነትን መተውና ለወል ፍላጎታችን መሰለፍን ይጠይቃል። ከትናንትም ሆነ ከዛሬ ነገሮቻችን መካከል መርጦ መዘንጋት እና ለይቶ ማንሳትን፣ ስለጋራ አማራዊ ፍላጎታችን በአንድ መስመር መሰለፍን ይጠይቃል።

ይህንን የማይታበል ሀቅ በመቀበል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስረታን ማሳካታችን የአመቱ ዋነኛ ፖለቲካዊ ስኬት ነበር። በዚህ ውስጥ የትግሉ ስትራቴጂካዊ አቅሞችን በማሰባሰብ እና በአንድ ድርጅታዊ ማዕቀፍ ስር ህልውናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ትግል ውስጥ ሁሉም አቅሞች እንዲውሉ ለማድረግ መድላድሉን መፍጠር ተችሏል። ይህም የአመቱ ስኬት ብቻም ሳይሆን በቀጣይ ጊዜያት ለሚያደርጋቸው ትግሎች ወሳኝ ስትራቴጂካዊ አቅም ሆኖ የሚቀጥል ነው።

፪. የዓለምን ትኩረት የሳበው ተጋድሏችን

አፋብን ከምስረታው ማግስት በሁሉም ዕዞቹ ውስጥ ከትግሉ መነሻ ጀምሮ የነበረውን ህዝባዊ ድጋፍ የትግል ግለቱን ለማስቀጠል እንዲያስችል በሁሉም አካባቢዎች የተደረጉት ህዝባዊ መድረኮች ወሳኝ ህዝባዊ ንቅናቄ ፈጥረዋል። በነዚህ መድረኮች ህዝቡ በአጀንዳዎቹ ላይ የበለጠ ግልጸኝነት በመፍጠር፣ የትግሉን አላማ ለማሳካት ያለውን ቁርጠኝነት እና መነሳሳት ያሳየበት ነበር። በዚህም የአደረጃጀት አንድነቱን፣ ህዝባዊ ደጀኑን በአላማ በማስተሳሰር መሬት ላይ ይበልጥ መትከልና ማጽናት ተችሏል።

ከዚህ በተጨማሪ የአማራ ህዝብ የትግልን አላማዎች በሀገር ውስጥ ብሎም በአለምአቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ፣ በተመሳሳይ በአንድ ድምጽ በስፋት ማሰማት ተችሏል። ለአማራ ህዝብ ጥሪ ለወትሮው ጆሮ ባለመስጠት የምስክርነት እና የትርጓሜ ግፍ ሲፈጸምበት ቢኖርም ዛሬ ግን በተለያዩ ሀገራት፣ በተለያዩ ቋንቋዎች አማራ ለራሱ እውነት መመስከር ብሎም ማስረዳት ችሏል።
በዚህም በአማራ ህዝብ ትግል ዙሪያ በተዛባ መልክ ተስፋፍተው የኖሩ ትርክቶችን ለማረም ጥቂት ዕድል ተገኝቷል። የአማራ ህዝብ መደመጥ በመቻሉም ህዝቡን ነጥሎ ለማጥቃት እና ለማስጠቃት ከዳግመ ጣሊያን ወረራ ጀምሮ የተተከሉ የጥላቻ ግምብ ለማፍረስ እና ጥርጣሬን አስወግዶ በህዝቦች መካከል መልካም ግንኙነት ለመፍጠር የሚያስችል ድልድይ እየተፈጠረም ይገኛል።

፫) የፖለቲካ ርዕደ መሬት የፈጠረው የትብብር ማዕቀፍ

ዘረ ፈጁን አገዛዝ በማስወገድ በፋሽስታዊ ዕሳቤ ተተክሎ የኖረውን የትውልዶች ጦርነት በህዝባዊ ትግላችን መቀልበስ እና ህልውናን በዘላቂነት ማረጋገጥ አንደኛው ተልዕኳችን ነው። አማራን ለማጥፋት የተነሳው ዘረ ፈጅ አገዛዝ ሌሎች ህዝቦችንም በጉልበት ጨፍልቆ ከመግዛት አልያም ከመጥፋት ውጭ ሌላ አማራጭ አላስቀመጠም። ለዚህም እንዲመቸው የህዝቦች የጎንዮሽ መልካም ግንኙነት እንዲበላሽ እና ቅራኔወች እንዲሰፉ በሙሉ አቅሙ እየሰራ ይገኛል።

ይሁንና እርስ በዕርስ እንዲተላለቁ የተደገሰላቸው ህዝቦች እና ብሔራዊ ሀይሎች የጥፋት ትርክት እና ሴራን አክሽፈው፣ ለህልውናቸው ሲሉ የጋራ ጠላትን በጋራ ለመታግል መግባባታቸዉን የሚያውጁበት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል።

በየትኛውም የዓለም ማዕዘን ተከስተው የነበሩ ፀረ-ህዝብ አገዞች የተገረሰሱት የጋራ እጣ ፋንታን በሚጋሩ ፀረ ጭቆና የትግል ኃይሎች ነው። ይህ መሠረታዊ እውነት ህዝባዊ አላማን አንግበው በሚታገሉ ብሔራዊ ሕዝባዊ ኃይሎች መካከል ያሉትን ልዩነቶች ተቀራርበው እንዲሰሩ አስችሏል። በእርግጥም እንኳንስ የሁሉም ህዝቦች ብሎም ሀገር የህልውና አደጋ ውስጥ ወድቀው አይደለም፤ የአንድ ማህበረሰብ የህልውና አደጋ ብቻዉን ህዝባዊ ኃይሎች እንዲተባበሩ የሚያስገድድ በቂ ምክንያት ነው።

በሀገራችን በከፍተኛ የእርስ በእርስ መጠራጠር ብሎም መገፋፋት ውስጥ እንዲኖሩ ከፍተኛ ሴራ የተሰራባቸው ህዝቦች የጠላትን እንዲሁም የውጭ ሀይሎችን ጸረ ትብብር ጫና ተቋቁመው በአብሮነት ለመቆም መነሳት የአመቱ ብሎም የክፍለ ዘመኑ ትልቅ ድል ነው። በዚህም የህዝቦችን የተሳሰረ ዕጣ ፈንታ ከጋራ የህልውና ስጋት ባሻገር ለሀገር ግንባታ በጋራ መስራት የሚቻልበትን ፖለቲካዊ መደላድል ለመፍጠር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

በመሆኑም እንደ አማራ ሕዝብ ሁሉ ለሕልውናቸው፣ ለባህላቸው፣ ለማንነታቸውና ለፍትሕ የሚታገሉ ሌሎች የኢትዮጵያ ወንድምና እህት ሕዝቦች በጋራ መቆማቸውንና መተሳሰራቸውን የሚያውጁበት ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን።

፬. በህዝባችን እና በሰራዊታችን ተጋድሎ የከሸፉት የአገዛዙ የስልጣን ማራዘሚያ ፕሮጀክቶች

ያለፈው 2018 ዓ. ም ፖለቲካዊ መዋቅሩን በወታደራዊ አገዛዝ እየለወጠ ያለዉ ዘረ-ፈጁ አገዛዝ በምርጫ ስም ህጋዊ የጭፍጨፋ እውቅና እና ካርድ ለማግኘት እንዲሁም በብሔራዊ ምክክር ስም ግለሰባዊ ቅዠቶችን የብሔራዊ ምክክር ውጤት ለማድረግ በቢሊዬኖች የሚቆጠር ገንዘብን በማባከን በሰፊው የደከመበት ዓመት ነበር።
ይሁን እንጅ የአማራ ህዝብን ጨምሮ መላው ኢትዮጵያዊ ባደረገው ተጋድሎ እና የነቃ እንቅስቃሴ ምክንያት አገዛዙ በምርጫ ስም ዓለምን ማታለል የማይችልበትን ይልቁንም ምርጫን ስልጣን ላይ ለመቆዬት የሚጠቀምበት የማጭበርበሪያ ስልት መሆኑን ማሳዬት ተችሏል። በምርጫም ሆነ በምክክር ስም የህልውና አደጋ የተደቀነበትን ህዝብ የህልዉና ጥያቄ ማዳፈን እንደማይቻል ተረጋግጧል። በመሆኑም ያለፈው ዓመት አገዛዙ ብሔራዊ አጀንዳወችን ለይስሙላ በማጉላት፣ ያልተደረገ ምርጫን እንደተደረገ በማስመሰል እንዲሁም በተጧጧፈ ጦርነት ውስጥ ሆኖ ብሔራዊ ምክክር በሚል ስም ስልጣንን ህጋዊ ቅቡልነት ያለው ለማድረግ ያደረጋቸው ሙከራወች ሙሉ በሙሉ የከሸፉበት መሆኑ በታሪክ የሚታወስ ነው።

ይህ አዲስ ዓመት ተራ የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን የአማራን ህዝብ ከምድር ገጽ ለማጥፋት፣ ታሪኩን ለመደምሰስ፣ ሀብቱን ለመዝረፍ እና ስነ-ህዝባዊ አወቃቀሩን ለመቀየር በአገዛዙ የታወጀውን የዘር ማጥፋት ጦርነት በመመከት፣ የህዝባችንን ፍጹም አሸናፊነት የምናበስርበት ታሪካዊ ምዕራፍ እንዲሆን እየተመኘን ተከታዮችን ጥሪወች እናቀርባለን!

፩) ለመላው የአማራ ህዝብ:-

አረመኔያዊውን ግፍና መከራ በትዕግስትና በጀግንነት እያሸነፍክ ላለኸው ኩሩ ሕዝባችን፣ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍትሕ፣ የዕረፍትና የታሪካዊ ክብርህ መመለሻ ዓመት እንዲሆንልህ ንቅናቄያችን ከትላንት በተሻለ መልኩ ደምና አጥንቱን ከስክሶ ህልውና እና ነጻነትን ለማስከበር ከምንጊዜውም በላይ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኑን ዛሬም እንደ ትላንቱ ያረጋግጣል። ስለሆነም የምታደርገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ደጀንነት ከምንግዜውም በላይ አጠናክረህ እንድትቀጥል ታሪካዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የትኛውም ስትራቴጂም ሆነ ታክቲክ አንድነትን አያክለውም፤ አንድነትን የሚያሳጣ አማራጭ በምንም መመዘኛ ተገቢ፣ አስፈላጊ አለያም ጠቃሚ ሊሆን አይችልም። ህዝባዊ አንድነት፣ መዋቅራዊ አንድነት እና የአመራር አንድነት የትግላችን አይተኬ ስትራቴጂካዊ አቅሞቻችን ናቸው።

በየትኛውም ጊዜ በተለይ ደግሞ በዚህ ወቅት አንድነትን የትግሉ ስትራቴጂካዊ አቅም መሆኑን ተረድተን አቅማችንን እንጠብቅ። ከዚህ በተቃራኒ የሆነ አካሄድ እና አሰላለፍ በጋራ እንታገል። አማራን በንዑስ ማንነት እና የጥቅም ትስስር በትኖ፣ የጀመረውን ዘር ማጥፋት በስኬት ለማጠናቀቅ ጠላት ከፋፍሎ ሊያጠፋን እየሰራ እንደሆነ ተረድተን አማራ ከብዙ አመታት በኋላ ያገኘውን ብሔራዊ አንድነት በጥንቃቄ ልንጠብቅ እና ከአቆርቋዥ ከፋፋዮች በጽናት ልንከላከለው ይገባል።

በተጨማሪም አማራው የህዝብ እና የድርጅት አንድነት ባሳካበት አመት ህዝቡን ከከበባ እና ንጥልነት አውጥቶ በሀገር ውስጥ ካሉ ብሔራዊ ሀይሎች ጋር መተባበር መቻሉ ለአማራም፣ ለሌላውም ብሎም ለሀገር ትልቅ ዕድልን አስገኝቷል። ይህን መልካም ዕድል እና ተስፋ መንከባከብ ይገባል።

፪) ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አመራርና አባላት፦

አማራ ተገፍቶ እና ተበድሎ የሚጠፋ ህዝብ ሳይሆን፣ በመከራ ውስጥ ታድሶ፣ የብረት ምሽግ ሆኖ የሚነሳ የጽናት አምድ ነው! የታጠቁ ድሮኖች፣ የተደረደሩ ታንክና መድፎች የተበላሹ የፕሮፓጋንዳ ማሽኖች የጊዜያዊ ጉልበት ምልክቶች እንጂ የህዝብን የእውነት እና የፍትህ ፍላጎት አይሰብሩም። የጠላቶቻችን ውድቀት ተቃርቧል፤

የብልፅግናን አገዛዝ አረመኔያዊ ጥቃት መክታችሁ፣ የሕዝባችሁን ሕልውና ለማስከበር በዱር በገደሉ የምታሳዩት የጀግንነት ታሪክ በአሁኑ ትውልድ ብቻ ሳይሆን፣ በመጪውም ትውልድ ዘንድ ታሪክ በወርቅ ቀለም የሚከትበው አኩሪ ገድል መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

አዲሱ 2019 ዓ.ም የሕዝባችንን ከሕልውና አደጋ አውጥተን፣ ነፃነት እና እኩልነትን የምናረጋግጥበት እንዲሁም ወንጀለኞችን ለፍርድ አደባባይ የምናቀርብበት የድል ዓመት እንዲሆን፣ ከምንጊዜውም በላይ ከፍተኛ አደራና ቃል-ኪዳናችንን የምናድስበት ዘመን እንዲሆን እንመኛለን።

፫) ለጸረ አገዛዝ ብሔራዊ ሀይሎች

ካለፉት ስምንት አመታት የተማርነው ወሳኝ እውነት በተራ ለመበላት ወረፋ የምንጠብቅበት ጊዜ እና ሁኔታ ላይ አለመሆናችን ነው።
እናም ሁሉም ህዝባዊ ሀይል ለህልውናው በአንድ የጋራ ጠላት ላይ በሁሉም ግምባር የቆመበት ምዕራፍ ለዚህ ለትውልዶች ለተደገሰው ጦርነት የመጨረሻው ምዕራፍ ነው፤ ለህዝቦች የአሸናፊነት ምዕራፍ።

እናም ቀጣዩ አመት በትብብር አቅም የህልውና አደጋን በመመከት ጠላትን ጨርሶ በማስወገድ እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ የምናደርግበት አመት ነው። ለዚህም የተጀመሩ መልካም የትብብር ተግባራትን በማስቀጠል፣ የጠላትን የፕሮፓጋንዳ ጥቃት ለመመከት በህዝባዊነት እንድንሰራ መልዕክታችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን። የህዝቦችን እና የብሔራዊ ሀይሎች መልካም ግንኙነት ለጠላት ትልቅ አደጋ በመሆኑ ይህን ለማፍረስ የሚሰራቸውን ተግባራት ለመቀልበስ የህዝብን አቅም በጋራ መጠቀም ይገባል። ለዚህም የትብብሩን ተስፋዎች መንከባከብ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ህዝቡ እና ሁሉም ብሔራዊ ሀይሎች በሁሉም ረገድ የጠላትን መግቢያ በሮች ለመድፈን የጋራ ርብርብ ልናደርግ ይገባል።

፬) ለአፍሪካውያንና ለመላው የዓለም ሕዝብ፦

በኢትዮጵያ ምድር እየተፈጸመ ያለውን አረመኔያዊ የሰብአዊ መብት ረገጣና የዘር ማጥፋት ወንጀል ዓለም በዝምታ ሊመለከተው አይገባም። የጭቁን ሕዝቦችን የነፃነት ድምፅና ትግል በሁሉም መስክ ሊደገፍ የሚገባዉ ነው።

​የአማራ ህዝብ የህልውና እና የፍትህ ጥያቄ ከዓለም አቀፍ ህጎች (IHL) እና ከህግ የበላይነት ጋር የተጣጣመ ነው። በምስራቅ አፍሪካ፣ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር ቀጠና ዘላቂ መረጋጋት እና የንግድ መስመር ሰላም ሊመጣ የሚችለው የህዝባችን ሰብአዊ፣ ታሪካዊ እና ፖለቲካዊ መብቶች ሲከበሩ ብቻ ነው። ያልተረጋጋች ኢትዮጵያ ለቀጠናው ስጋት ናት፤ የህዝባችንን ትግል መደገፍ ደግሞ በቀጠናው ህጋዊነትን፣ ፍትህን እና ዘላቂ ሰላምን የመትከል ብቸኛው መንገድ ነው።

በመሆኑም የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰላም እና መረጋጋትን የሚያውከውን የብልፅግና አገዛዝን ማስወገድ ለሰላማዊ የንግድ እና ፖለቲካ እንቅስቃሴ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን በማመን አገዛዙን ባለመደገፍ እና ለተጋድሏችን ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ በመስጠት የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ እንጠይቃለን።
5,7500038
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

11 de set. de 2026, 03:57

Photo
🔥#ምርኮ_ከዳውንት_ግምባር‼️

የጠላት 12ኛ ዕዝ 71ኛ ክ/ጦር ወሎ ቤተአማራ ቀጠና በገባች 24 ሰዓታት ሳይሞላት ዳውንት ግንባር ላይ እንደ በረዶ ቀልጣ በቀረችበት ተጋድሎ የተገኙ ተጨማሪ የሰውና የመሣሪያ ምርኮ ምስሎች!

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጳጉሜ 05/2018 ዓ.ም
6,9600063
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

11 de set. de 2026, 03:57

🔥#ሰበር_ቪዲዮ‼️

በአፋብን ምንሊክ 1ኛ ዕዝ መብረቃዊ ጥቃት 12ኛ ዕዝ ይኮራባትና ይተማመንባት የነበረችው 71ኛ ክ/ጦር ወሎ ቤተ አማራ ቀጠና ከገባች 24 ሰዓታት ሳይሞላት ዳውንት ግንባር ላይ እንደ በረዶ ቀልጣ ከቀረችው ክፍለ ጦር እድለኛ ሆነው #ከተማረኩ #ምርኮኞች ጋር የተደረገውን ቆይታ በንስር አማራ የዩቱዩብ ገፅ ይመልከቱ‼️

ምርኮኞችን ምን አሉ ? ለአብይ አህመድና ጓዶቹ ይድረስ‼️

ቪዲዮ ለመመልከት ማስፈንጠሪያ link ይጫኑ የንስር አማራ የዩቲዩብ ገፅ ይወዳጁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/agIy8KI2344?si=NPJPrAG483D6QBri
Video Thumbnail
9,9500056
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

11 de set. de 2026, 03:57

Photo
🔥#ኢትዮጵያ_አልነጋላትም‼️


(የአማራ ተወላጅ ከሆኑ ከማንነት፣ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች የተላለፈ መልዕክት)

እኛ የአማራ ተወላጆች የሆን፣ በማንነታችን፣ በፖለቲካ አመለካከታችን ለግፍ እስር ከተዳረግን ሦስት ዓመታት ያለፉ የሕሊና እስረኞች ከ2016 የአዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ በዓል ጀምሮ አራት የዘመን መለወጫ በዓላትን በእስር ውስጥ አሳልፈናል፡፡ ነገ የሚገባው 2019 አዲስ ዓመት የቁጥር እንጅ የፖለቲካ ለውጥ የሌለበት፣ የጦርነት እልቂት የሚቀጥልበት፣ የኢኮኖሚ ድቀቱ ወደ ከፋ ምዕራፍ የሚሻገርበት፣ የከፋ ማህበራዊ ቀውስ የሚቀጥልበት እንደሚሆን ከምንሰማቸው መረጃዎች ተረድተናል፡፡

የአዲስ ዓመት መባቻውንም #ያልጠባው_መባቻ ብለነዋል፡፡ እኛ የፖለቲካ እስረኞች በነገው ዕለት የረሃብ አድማ አድርገን አንደምንውል ለመላው የአማራ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ እናሳውቃለን፡፡

የተከበርከው የአማራ ሕዝብ ይህንን ማስታወሻ የሰደድንልህ እንደ አባቶቻችን ወግና ልማድ እንኳን አደረሰህ ልንልህ አይደለም።አዲሱ ዓመት እንደ ባለፉት አመታት አገራችን በማያበራ ጦርነት ውስጥ ተነክራ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የማይቻልበት ልጅ ወልዶ ማሳደግ፣ ዘርቶ መቃም ፈፅሞ የማይቻልበት ሆናለች።
ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ከጎረቤት አገራት ተነጥላ እና ተንቃ የቅጥረኛ ፖለቲካ በሚያካሂድ አገዛዝ የምትመራ ሆናለች። ሕዝቡ በአገዛዝ ቀንበር ስር ሆኖ 2019 ዓ.ም ልትቀበል ነው፡፡
ስልጣን የያዘው ቡድን ገንዘብ እያተመ የሕዝቡን ጥሪት የሚዘርፍባት፣ የውጭ ኃይሎች በቀጥታ እጃቸውን አስገብተው አድራጊ ፈጣሪ፣ ሿሚ ሻሪ የሆኑበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ አሁንም ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ሕዝባችን ተፈናቅሎ በካምፕ ውስጥ ይኖራል። አሁንም ወለጋና አርሲን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የዘር ፍጅት የተፈፀመበት የወገናችን ደም፣ የፍትህ ያለህ እያለ ከመቃብር በላይ ይጣራል፡፡ 

እንደ ሕዝብ የአማራ ሕዝብ ጠላታችን ነው እናጥፋው ያሉ ጠላቶቻችን ተባብረው ተሰልፈዋል፡፡ የአማራን ህዝብ ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ በሆነ ሁኔታ እንዲፈጅ ተፈርዶበታል ይህን መመከት ደግሞ ተፈጥሯዊ መብቱ ነው፡፡
መላው የአማራ ሕዝብ ታጋዮች ለትግሉ በፅናት እና በታማኝነት በመቆማችሁ በዚህ ዘመን ሊደረግ ይችላል ተብሎ በማይታሰብ ደረጃ የማንነት ድምሰሳ እና የዘር ፍጅት እየተፈፀመበት፣ ላለው ሕዝባችን የሕይወት መስዋትነት በመክፈላችሁ በርቱ ቀጥሉ እንላለን፡፡

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የሰብዓዊ መብት ተቋማት በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ የዘር ፍጅት ለማስቆም የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ እንጠይቃለን፡፡

በዚህ የሕዝባችን መከራና ስቃይ ባላባራበት እንደውም ተጠናክሮ የቀጠለበትን 2019 ዓ.ም የአዲስ ዓመት መባቻ እንደ አምናው ሁሉ ዘንድሮም "#ገና_ያልጠባው_አዲስ_ዓመት" ብለን ሰይመነዋል።

እኛ በቂሊንጦ እስር ቤት የምንገኝ  ብዙሃን የአማራ የፖለቲካ እስረኞች በብዙ ስቃይና መከራ ውስጥ እንገኛለን፡፡ በተለይ አገዛዙ በደነገጠ ቁጥር ከሰብዓዊነት ውጭ በሆነ ደረጃ ተደራራቢ የሆነ ግፍና በደል እየተፈጸመብን ይገኛል፡፡

የአገዛዙ የቁጣው ሁሉ ማረፊያ እኛ እስር ቤት ውስጥ ያለነውን የማንነት፣ የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች ቢያደርግም ከተነሳንበት ዓላማ አንፃር የሚደርስብን ሁሉ በፀጋ እንቀበላለን፡፡
የዓላማ ቁርጠኝነታችን እስከ #ቀራንዮ ድረስ ጸንቶ ይቀጥላል፡፡

ይህን የአዲስ ዓመት ጨለማ ዕለት በመከራ እና በስቃይ ውስጥ ያለውን ሕዝባችንን በማሰብ፣ በእኛ ላይ ያለውን ተደጋጋሚ ኢሰብዓዊ ጥቃት በመቃወም እና በአገራችን ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ ጥቃት ለመቃዎም ስንል #የርሀብ_አድማ አድርገን ለማሳለፍ መወሰናችንን ለሕዝባችን እንገልፃለን፡፡  በነገው ዕለት የረሃብ አድማ አድርገን ስንውል ለዓላማችን ያለንን ቁርጠኝነት፣ ለሕዝባችን ያለንን ታማኝነት ለማሳየት መሆኑን መላው የአማራ ሕዝብ፣ መላው ኢትዮጵያዊ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ አንዲያውቀው መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

©የማንነት፣ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች
ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም.

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጳጉሜ 05/2018 ዓ.ም
10,10000118
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

11 de set. de 2026, 03:57

Photo
የምኒልክ ዕዝን መብረቃዊ ምት መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ጦር ከመዋጋት ይልቅስ በሰላም እጅ መስጠትን እየመረጠ ይገኛል። በሰሜን ወሎ ዞን ደጋማ አካባቢዎች የወረዳ ከተማዎች ላይ ብቻ ተወሽቆ የሚገኘው የስርዓቱ ቀለብተኛ ወታደር የ16ኛ ኮርን ምትሃታዊ ገድል ምት መቋቋም አልቻለም።

በዚህም በዛሬው እለት አንድ ዘመናዊ የሞርተር መነፀርን ጨምሮ ጥቁር ክላሽን በመያዝ 16ኛ ኮር 163ኛ ክፍለጦርን ተቀላቅሏል።


መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

©አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ 16ኛ ኮር ቃል አቀባይ

ጷግሜ፦ 05/ 2018 ዓ/ም

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጳጉሜ 05/2018 ዓ.ም
11,1000091
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

26 de ago. de 2026, 20:43

Photo
በወሎ ቤተአማራ ቀጠና ራያ ግንባር ሦስት የመከላከያ ሠራዊት አባላት አንድ የቡድን መሳሪያ እና 1ክላሽን ኮፍ መሳሪያ በመያዝ በአፋብን 1ኛ ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።

ከጠላት የኮበለሉት የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ 250 የክላሽ ተተኳሽ እና 200 የስናይፐር ጥይት ተተኳሽ እንዲሁም አራት ኤፍ ዋን ቦንብ በመያዝ ተቀላቅለዋል።

የተቀላቀሉት የደቡብ ዕዝ 202ኛ ኮር 21ኛ ክፍለጦር 1ኛ ሻለቃ 1ኛ ሻምበል ቲም መሪ እና እስናይፐር ተኳሽ ደሳለ መልካሙ እና እሱ ያውቃል ታደሰ እንድሁም 1 ጓዳቸውን በጀሌ /ያለመሳሪያ/ በመያዝ ህዝባችንን አንወጋም በብለው ወደ ምኒልክ 1ኛ ዕዝ 102ኛ ኮር በመምጣታቸው በኮር አመራሮቹ የጀግና አቀባበል ተደርጓላቸዋል።

©አፋብን 1ኛ ምኒልክ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

20/12/2018 ዓ.ም
1,7500021
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

26 de ago. de 2026, 20:43

Photo
⚫️በሚኮላተፍ የህፃን አንደበቷ "እራበኝ፣ እራበኝ" እያለች የሲቃ ድምፅ ታሰማለች ቀናት ካስቆጠረው የእናቷ አስከሬን ጎን ተቀምጣት😭

እናቷ የተገደለችው እለተ አርብ ነሀሴ 15/2018 ዓ/ም ነው። ህፃኗ ልጅ ከእናቷ አስከሬን ጎን ተቀምጣ የተገኘችው ሰኞ ነሀሴ 18/2018 ዓ/ም አመሻሹን ነው። ወልጅ እናቷን በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ገዝግዘው የገደሏት እነዛ ጨካኞች ህፃኗን ልጅም ታፋዋ ላይ ክፉኛ አቁስለዋታል።

ከጥቃቱ በኋላ በሕይወት የተረፈ ሰው ካለ ለማገኘት አከባቢውን ሲያስሱ የነበሩ ሌሎች የአማራ ተወላጆች ወደ ልጂቱ ሲቀርቡ ...እነዛ እናቷን ያለርህራሔ የገደሉባትና እሷንም ጭኗ ላይ ያቆሰሏት አውሬያዊ ባህሪ ያላቸው ጨካኞች መስለዋት ...በፍርሀት ትንቀጠቀጥ ነበር ልጂቱ።

ከእናቷ አስከሬን ጎን እንደተቀመጠች በሚኮላተፍ የህፃን አንደበቷ "እራበኝ፣ እራበኝ" እያለች በተደጋጋሚ የሲቃ ድምፅ ታሰማለች።

የግፍ ፅዋው ሞልቶ የፈሰሰበት ምድር፣ የፍትሕና የእዝነት ሚዛን ተዛብቶ የሰው ልጅ የጭካኔ ጥግ እስከምን ድረስ እንደሆነ የታየበት ወለጋ!

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

20/12/2018 ዓ.ም
6,55000130
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

26 de ago. de 2026, 20:43

Photo
በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ልዩ ቦታው መንደር 3 ተብሎ በሚጠራው አከባቢ መከላከያ ሠራዊትና የክልሉ ልዩ ኃይል እንዲሁም ገዳ ኮማንዶና የሚኒሻ ኃይሉ በቅንጅት በከፈቱት መንግስት መር ጭፍጠፋ ንፁኋን ወገኖች በገፍ ተጨፍጭፈዋል።

በመንደሩ ጭፍጨፋው የተከፈተው ነሀሴ 18/2018 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ ሲሆን፡ በዚህም የሃይማኖች አባቶችንና አረጋውያንን ጨምሮ ከ22 በላይ የአማራ ተወላጆች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።

ንፁኋኑ የተጨፈጨፉት በመከላከያ ሠራዊቱና በገዳ ኮማንዶ ኃይል ሽፋንና እገዛ በሚሰጠው ከክላሽ ጀምሮ ሜንጫና ቆንጨራ በታጠቀ የቄሮ ቡድን መሆኑን መረብ ሚዲያ ከጥቃቱ የተረፉ እማኞችን በማነጋገር ለማረጋገጥ ችሏል።

እስካሁን የ22 ንፁኋኖች አስከሬን መገኘቱንና አሁንም በየማሣው ወድቆ የዱር አራዊትና የሰማይ አሞራ እየበላው የሚገኝ አስከሬን መኖሩን ነው መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው ከጥቃቱ የተረፉ እማኞች አክለው የገለፁት።

ከዚህ በተጨማሪ በርካታ መኖሪያ ቤቶች በእሳት የወደሙ ሲሆን፡ የቀንድ ከብቶችም ተዘርፈው በብልፅግና መከላከያ ሠራዊት ካሶኒ ተጭነው ወደ ነቀምቴ ከተማ መወሰዳቸውን ነው እማኞች ለጣቢያችን የገለፁት።

የከባድ መሣሪያ ሽፋን ከመስጠት ጀምሮ ህፃናትና አረጋውያንን ጨምሮ በሜንጫና በሌሎች ስለታማ መሣሪያዎች የሚገድሉ ወጣቶችን አደራጅቶ በወታደራዊ ኦራል ተሽከርካሪ ጭኖ ከቦታ ቦታ እስከማንቀሳቀስና እልቂቱን እስከመምራት የደረሰ ስራ የሚሠራው በሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ የሚመራው ማዕከላዊ ዕዝ እና በሜጀር ጄኔራል አማረ ባህታ የሚመራው ምዕራብ ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ነው።

ከነዚህ ፅንፈኛ ኃይሎች በተጨማሪ፡ የገዳ ኮማንዶ ኃይል፣ የክልሉ አድማ ብተና ኃይል፣ ጋቸና ሲርና፣ ረፔሎላና የሚኒሻ ኃይሉ በቅንጅት የእልቂቱ ዋና መሪ እንዲሁም ፈፃሚና አስፈፃሚ ናቸው ሲሉ ተጎጂዎች ለመረብ ሚዲያ ተናግረዋል።

©መረብ ሚዲያ

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

20/12/2018 ዓ.ም
6,9200072
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

26 de ago. de 2026, 20:43

Photo
🔥የደቡብ ወሎ ዞን የደህንነት ኃላፊ መቶ አለቃ ቢኒያም ምኒልክ 1ኛ ዕዝን በይፋ ተቀላቀሉ‼️

​የደቡብ ወሎ ዞን የደህንነት ኃላፊ መቶ አለቃ ቢኒያም ከአገዛዙ በመለየት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄን (አፋብን) ምኒልክ 1እኛ ዕዝ  በይፋ  በዛሬዉ ዕለት ማለትም በቀን 19/12/2018 ዓ.ም ተቀላቅለዋል።

ኃላፊው የምኒልክ 1ኛ ዕዝ፣ 15ኛ ኮር፣ 155ኛ ክፍለ ጦርን የተቀላቀለ ሲሆን ውሳኔውን የወሰዱትም "ገዢው የብልፅግና ስርዓት በዞኑና በሕዝቡ ላይ እየፈጸመ ነው ያሉትን ሴራና አበሳ በመቃወም እንደሆነ አስታውቀዋል"።

በተለይም የደሴ፣ ኮምቦልቻና ሐርቡ አካባቢዎችን ጨምሮ የዞኑ ቁልፍ ቦታዎችና አጠቃላይ የሕዝብ ጥቅም የወረዳዉ የብልፅግናዉ ቡድን ለሌላ አካል አሳልፈው ለመስጠት የተሄደበትን መንገድ አጋልጠዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

©የአፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ!
  ነሐሴ19/ 2018 ዓ/ም

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

19/12/2018 ዓ.ም
12,40000152
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

26 de ago. de 2026, 20:43

🔥#የታፈሱ_ወጣቶች_ወደ_ስልጠና_ጣቢያ‼️

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የታፈሱ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ወደ ተለያዩ ማሰልጠኛ ጣቢያ የተጫኑ ሲሆን ከአማራ ምድር የታፈሱ ወጣቶች #ከጎጃም_አዲስ_አበባ መስመር ከምዕራብ ወደ ምስራቅ ጎጃም የተሻገረ.. 48 ታታ ባስ ፣20 አይሱዙ ቅጥቅጥ በድምሩ #68_መኪና እንዲሁም #ከአዲስ_አበባ_ጎጃም መስመር ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ጎጃም የተሻገረ 10 ታታ ፣ 40 አይሱዙ ቅጥቅጥ በድምሩ #52_መኪና ተንቀሳቅሷል ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች አረጋግጠዋል።

ይህ ስርዓት ካልተገረሰሰ ውጊያው አማራ ክልል ቢሆንም የመላው የኢትዮጵያውያን ልጆች እየታፈሱ ወደ ጦር ግምባር መግባታቸው አይቀሬ ነውና ከአማራ ጎን በመሰለፍ ይህንን ስርዓት እንገርስስ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን‼️

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

19/12/2018 ዓ.ም
13,0000094
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

26 de ago. de 2026, 20:43

⚫️#አሳዛኝ_የወለጋ_አማራ_የንፁኋን_ስቃይ‼️
      (#የዘር_ማጥፋት_ዘመቻ )

   ነሐሴ18/2018ዓም

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ተጠናክሮ የቀጠለው የአማራን ተወላጅ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ያለ ማቋረጥ ለ7ዓመት በተከታታይ ሲገሉ እና ሲፈናቅሉ መቆየታቸው ይታወቃል።

በዘንድሮው አመት በተለይም አድማሱን አስፋፍቶ የቀጠለው የንጽኋን ግዲያ ፣የንብረት ዘረፋ እና የቤት ቃጠሎ በሁለቱ ዞኖች የአገዛዙ ሰራዊት መከላከያ እና የክልሉ ጥምር ጦር አገዛዙ በጫካ ያሰማራው ሸኔ ያ ፍላጎታቸው አልሳካ ሲል ወደ ጉያው ያስገባው  ጥሬ ስጋ ሲቀልበው የነበረው የስም ቅያሬ ያደረገለት ገዳ ኮማዶ ፣አድማ ብተና ፣ልዩሃይል፣ጋቸናሲርና ፣ኤርፔሎላ፣ሚኒሻ እና ቄሮ የሚፈጽሙት እኩይ ተግባራቸውን በጋሀድ እየተገበሩት ይገኛሉ ።በተለይም ሰሞኑን በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና ወረዳ  ያለማቋረጥ ለሁለት ሳምንት አፀያፊ ስራዎችን በመፈፀም ፈንደቃን እና አዶዴ ዴቾን በማቃጠል እድሁም የሃይማኖት ተቋም ቤተክርስቲያንን ጨምሮ በማውደም ከወለጋ ምድር ላይ አማራን እናጠፋለን በሚል እብሪተኝነት የአገዛዙ ሰራዊት እና የክልሉ ጥምር ሃይል ሲያካሂዱ የነበረውን ነገር በተደጋጋሚ ስንገልፅ ነበር ።

ይህ በእድህ እዳለ ነሐሴ13ቀን 2018ዓም በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ከተማን ሙሉ በሙሉ በማውደምና ቤተክርስትያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በመግባት በማስቀደስ እና በቅዳሴ ላየ ያሉ ካህናቶች እድሁም ከእናት አስክሬን ጎን የአራት አመት ህፃን በህይወት እደተገኘ እድሁም የሀይማኖት አባቶችን ካህናት ፣አይነ ሰውራንንና መለኮሳትን በግፍ ተረሽነው ለማየት ችለናል።በአሰቃቂ ሁኔታ በግፍ ከተረሸኑት በጥቂቱ
የስም ዝርዝራቸውም፦
➾የአዶዴ ስላሴ ቤተክርስቲያን 
      ዋና አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ታደሰ
➾ቄስ አድስ አየለ
       እድሁም አስክሬናቸው ያልተገኙ ካህናትና መነኮሳት በርካታ እንዳለ ሁኖ፤

ትናት ደግሞ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ይህ የክልሉ ገዳይ ጥምር ጦር እንዲሁም መከላከያ ማዕከላዊ ዕዝ 101ኛ ኮር 33ኛ ክፍለጦር ከፊት እደኬላ በማስቀመጥ ይህ የክልሉ ጥምር ሀይል መንደር ሶስት፣መንደር 22 ሙሉ በሙሉ ሲያቃጥሉ እና ተጨማሪ "በጭበጭ" የሚባል ሰፈርን የሃይማኖት ተቋም የጊዮርጊስ ቤተክርስትያንን ጨምሮ አቃጥለዋል።

በነዚህ መደሮችም በርካታ ንጹኋንን በጂምላ የአማራ ተወላጆችን ከመኗሪያ ቤታቸው አፈናቅሏል ፣ንጹሐን ደካሞች እና ህጻናት በግፍ እረሽነዋል ፣የቤት ንብረታቸውን እና የቀንድ ከብቶችን ከ450 በላይ በግፍ ተዘርፈዋል ።አሁን በዚህ ስዓት የተገደሉት ንጹሃን 67 ደርሰዋል የተቃጠለው የማህበረሰቡ ቤት በሺዎች እደተቆጠሩ ምንጮች ያሳያሉ ።ይህ የብልጽግና ስርዓት የፋኖን ብርቱ ክንድ መቋቋም ሲያአቅተው ባልተያዙ ቀጠናዎች ይሀንን መጥፎ ተግባሩን ሲፈጽም ውሏል ።

የህዝቡ ስቃይ ከቤቱ ያስወጣው የአንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ  አንገር ጉተን ክፍለ ጦር ትናንት ጧት ደፈጣ በመጣል ኬላ ዘርግቶ ለክልሉ ጥምር ጦር ሽፋን ሲሰጥ የነበረው መከላከያ ሲያዘርፍ ፣ ቤቶችን ሲቃጠሉ ፣የቀድ ከብቶች ሲያዘርፍ፣ ንፁኋንን በግፍ ሲያስረሺን ከዋለ ቦኋላ  እቅስቃሴዎችን ሲያደርግ ድቾ ተራራ ለይ በደፈጣ እንደለመደው ታሪክን በክንዳቸው ጽፈዋል።

ግፍ የወለደን:ግፈኞችን የምቀጣ የአንሻ ሰይድ ወድሞች ነን!!!

©አፋብን አንሻ ሰይድ 4ኛ እዝ ህ/ግንኙነት መምሪያ!

19/12/2018 ዓ.ም
12,90000103
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

26 de ago. de 2026, 20:43

Photo
ቀን 19/12/2018 ዓ.ም
🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙
እንኳን ለ1501ኛው የመውሊድ (የነቢዩ ሙሐመድ የልደት) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ለሕዝባቸው ክብር፣ ፍትሕና ሰላም ሲሉ ለሚታገሉት ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መሪዎችና አባላት እንዲሁም ለተከበረው ሙስሊም ማህበረሰባችን በሙሉ እንኳን ለታላቁ ነብይ ነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

የመውሊድ በዓል የሰላም፣ የርኅራኄ፣ የፍቅርና የሕብረት ታላቅ ተስፋ የሚታደስበት ወቅት ነው።

ነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ለዓለም ያስተማሩት የመቻቻል፣ የታማኝነት፣ የወንድማማችነት እና ለበደለኞች አለመበርከክ እሴቶች ለሁላችንም ትልቅ የሞራልና የጽናት ምንጭ ናቸው።

ታላቁ ነቢይ ያስተማሩት የእውነትና የፍትሕ መንገድ ለሕዝባችን አንድነት፣ ለሰራዊታችን ጥንካሬና ብርታት ለጋራ ዓላማችን መሳካት ትልቅ ብርሃን ነው።

የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት፣የአማራን ሕዝብ ሕልውና፣ ታሪካዊ ክብርንና ፍትሕን ለማስከበር እየተካሄደ ያለው መራራ ትግል በላቀ ድልና በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ  ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል።

ለሕዝባቸው ህልውናና ደህንነት ሲሉ በየግንባሩ ለሚታገሉት የሰራዊታችን አባላት በሙሉ የሚደረገው የፍትሕና የእውነት ጉዞ በሕዝባችን ደጋፊነትና ጥበቃ ታጅቦ የሕዝባችንን የተነጠቀ መብት፣ ደህንነትና ታሪካዊ ክብር የማስከበር ጉዞ ወደ ኋላ በማይመለስ ጽናት ወደ ፊት ይገሰግሳል።

በየመንገዱ የሚገጥሙ ፈተናዎችን ሁሉ በመሻገር ለተበደሉት ፍትሕን፣ ለተፈናቀሉት ወገኖቻችን ደግሞ ዘላቂ መረጋጋትና እፎይታን የሚያመጣ ድል ይረጋገጣል።

እስከ አሁን የተከፈለውን ግዙፍ መስዋዕትነት ወደ ተጨባጭ ድል ለመቀየር ሕዝባችን በጋራ ዓላማና አንድነት ሊቆም ይገባል።
‎
‎ በዓሉ የፍቅር፣ የደስታ፣ የጽናትና የድል ይሁንላችሁ!
‎ድል ለሕዝባችን! ፍትሕና ሰላም ለሀገራችን!
መልካም የመውሊድ በዓል!!
©የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ /አፋብን/
ነሃሴ19/12/2018  ዓ.ም

19/12/2018 ዓ.ም
13,6000099
️ ንስር አማራ🦅 logo
️ ንስር አማራ🦅

23 de jul. de 2026, 03:21

Photo
🔥#ሰበር...‼️

በምኒልክ ዕዝ ቀጠና በዛሬው ዕለት ከመካነሰላም ከተማ ወጣ ብሎ በተወሰነ ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኘው የአባይ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ላይ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞ ገዳሙንና ገዳማውያን ላይ ጉዳት መድረሱ መዘገባችን ይታወሳል።

ለሌላ ውድመት በዚሁ ቀጠና ለቅኝት ስትንቀሳቀስ የነበረችው ቱርክ ሰራሿ የአገዛዙ ድሮን #በማውደም ምኒሊክ ዕዝ የህልውና ትግሉን ምዕራፍ ወደተሻለ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ ያሸጋገረ አንፀባራቂ ድል መቀዳጀቱን ንስር አማራ ከአይን አማኞችና ከአናብስቶች የምኒልክ ልጆች አረጋግጣለች።

ስለ ድሮኑ መከስከስ እና እንዴት ተከሰከሰች የሚለውን ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሁም የተከሰከሰችዋን የድሮን ምስል በሚመለከተው የአፋብን ምኒልክ ዕዝ ባለድርሻ አካል በኩል ፈቃድ ሲሰጥ ይዘን የምንመለስ ይሆናል‼️

#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

15/11/2018 ዓ.ም
2490012

Showing 30 of 62 posts

Avaliação

Login necessário

Frequently Asked Questions

Sobre o que é o canal Telegram ️ ንስር አማራ🦅?+

️ ንስር አማራ🦅 (@nisireamhra) é um canal Telegram listado em Memes no tgdio. Ranking, avaliações, reviews e posts recentes para decidir antes de assinar. Atualmente lista cerca de 68.237 inscritos no tgdio.

Como entrar em ️ ንስር አማራ🦅 (@nisireamhra) no Telegram?+

Abra o perfil no tgdio e use Join / Open in Telegram para assinar @nisireamhra de graça.

️ ንስር አማራ🦅 é um bom canal de Memes?+

No tgdio você pode ver avaliação, reviews, ranking e posts de ️ ንስር አማራ🦅 antes de entrar. Atualmente lista cerca de 68.237 inscritos no tgdio. Compare com canais similares de Memes.

Onde ver estatísticas e posts de ️ ንስር አማራ🦅?+

No tgdio, abra @nisireamhra para stats de inscritos, ranking, avaliações e posts. Use Stats para gráficos.