🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻 Telegram channel photo

🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

@menfesawitsufochePublic Channel

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ትምህርታዊ ጹሑፎችን፣ ብሂለ አበው፣ ከመጽሐፍት ዓለም እና ሌሎችም ''መንፍሳዊ ሥነ-ጹሑፎችን'' ያገኛሉ። . . . ሃሳብ አስተያየታቹን ወይም ቻናሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ-ጹሑፎች ለመደገፍ @kal002 ላይ አድርሱን።

IPLportuguêsBrasil

133

Last views

31k (30,952 subscribers)
Membros
—
Rating
67
Total Posts
Oct 21, 2026, 3:03 AM
Atualizado
Apr 1, 2026
Created
Stats

Você está vendo conteúdo em português. Para ver conteúdo em outros idiomas, mude o idioma do site.

Channel Information

Channel Information
Channel Name🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻
Username@menfesawitsufoche
CategoryIPL
Languageportuguês
CountryBrasil
Membros30,952
Channel TypePublic Channel
Created1 de abr. de 2026
Last Updated21 de out. de 2026 • anteontem
StatusActive

Classificação

Classificação Global
#138729+229
Classificação por Idioma
#2919+19
Classificação por Categoria
#947-1

Crescimento de Participantes

Total: 31.0K30 Days growth: +1990.6%
09/2109/2610/0110/0610/1110/1610/20
Crescimento de Participantes - 30 Days
DateSubscribers
21:09:202630,753
22:09:202630,753
23:09:202630,753
24:09:202630,753
25:09:202630,753
26:09:202630,753
27:09:202630,753
28:09:202630,753
29:09:202630,753
30:09:202630,753
01:10:202630,753
02:10:202630,753
03:10:202630,753
04:10:202630,753
05:10:202630,753
06:10:202630,753
07:10:202630,753
08:10:202630,753
09:10:202630,753
10:10:202630,753
11:10:202630,753
12:10:202630,753
13:10:202630,894
14:10:202630,894
15:10:202630,894
16:10:202630,894
17:10:202630,894
18:10:202630,894
19:10:202630,894
20:10:202630,952
Crescimento de Participantes - Weekly
DateSubscribers
Week of 30:03:202630,645
Week of 06:04:202630,702
Week of 13:04:202630,675
Week of 20:04:202630,602
Week of 27:04:202630,602
Week of 04:05:202630,602
Week of 11:05:202630,482
Week of 18:05:202630,482
Week of 25:05:202630,482
Week of 01:06:202630,197
Week of 08:06:202630,197
Week of 15:06:202630,197
Week of 22:06:202630,089
Week of 29:06:202630,089
Week of 06:07:202630,089
Week of 13:07:202630,222
Week of 20:07:202630,222
Week of 27:07:202630,283
Week of 03:08:202630,400
Week of 10:08:202630,400
Week of 17:08:202630,612
Week of 24:08:202630,677
Week of 31:08:202630,677
Week of 07:09:202630,725
Week of 14:09:202630,753
Week of 21:09:202630,753
Week of 28:09:202630,753
Week of 05:10:202630,753
Week of 12:10:202630,894
Week of 19:10:202630,952
Crescimento de Participantes - Monthly
DateSubscribers
April 202630,602
May 202630,482
June 202630,089
July 202630,283
August 202630,677
September 202630,753
October 202630,952
Crescimento de Participantes - Yearly
DateSubscribers
202630,952

Últimos Posts

[📌 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?

📌 ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
እና የሌሎችንም ...........](https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk)

የዘማሪዎችው መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት 🔻🔻🔻
                   👇👇👇

https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
133000
📕✞ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከሐዋርያቱ ጋር የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና በሰርግ ቤት ተገኝቶ ውሃውን ወይን ጠጅ ያደረገበት የሰርግ ደግሶ የነበረው  ማን ነበር ?
204000
♥♥ስደቷ ፍቅር ነው♥♥
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ከአረጋዊው ዮሴፍ ጋር _ ኤልሻዳይን አዝላ
ሰሎሜም ሳትቀር_ወጡ ከገሊላ
የአስራአምስት ዓመቷ_ድንግል ማርያም
በግብፁ በረሀ_ ገጠማት ድካም።
ዐፈሩ ረመጥ ነው_ እጅግ የሚያቃጥል
አሸዋ ድንጋዩ_ እንደ ብረት የሚግል
አየር እንፋሎቱ_ ልብን የሚሰውር
የነበረው ስቃይ_እንደምን ይዘርዘር?
ያስጨንቃል በጣም_የመከራሽ ነገር።
በትንቢተ ሆሴዕ _የተጻፈውን
ምስጢራዊ ትንቢት_ ሄደ ሊከውን
የድንግል ማርያም ልጅ_ ኢየሱስ መድኽን
እፁብ ድንቅ ያሰኛል_ የእግዚአብሔር ማዳን።
በፈጣን ደመና _ ወደ ግብጽ በረረ
በማለት ኢሳይያስ_ እውነት ተናገረ
ፈጣኗ ደመና _ ወለተ ኢያቄም
ማኅደረ መለኮት_ ነጻነቱ የአዳም።
ከሦስቱ አካል አንዱ_ ኢየሱስ ክርስቶስ
ተወልዷል በበረት_ ሞትን ሊደመስስ
በገባው ቃል ኪዳን_ በቀጠሮ መጣ
ከሲዖል ቁራኛ_ ነፍሳትን ሊያወጣ።
በከብቶቹ በረት_ ቢታይ በትሕትና
የሕይወት እንጀራ _ የሰማዩ መና
የዳዊት የሙሴ_የነቢያቱ ዜና
ተፈፅሞ ስናይ_ ዘመርን በበገና።
እረኞች በቦታው _ ከመላእክት ጋራ
ሥብሐት ለሥላሴ_ብለዋል በጋራ
ንጉሥ ተወለደ_ በዳዊት ከተማ
አስይ የምሥራች_ በዓለም ይሰማ
ነበር የዚያን ጊዜ_የደስታቸው ዓርማ።
መወለዱን የሰማው_ ሄሮድስ በውሸት ተነስቶ
ብዙ ሕጻናትን _ ቦታው አስጠርቶ
እርዳታ ልሰጥ ነው_ በሚለው ትዕዛዙ
የዋሓን እናቶች_ የሆዳቸውን ፍሬ ወደ እሱ አጋዙ።
ገስግሰው ሲደርሱ_ የሆነው ሌላ ነው
ለጨካኝ ሰራዊቱ_ ደም ለጠማቸው
የሕጻናቱን አንገት_ ቆራርጡት አላቸው
ለወንበር ለሥልጣን_ ስለ ተማረከ
የሥላሴን ፍጥፈት_ በሰይፉ አወከ።
የሰባ ሰገሎቹ_ ጥበብ ስላልገባው
የተወለዱትን _ በሙሉ አስጠራቸው
የተባለው ትንቢት_እንቅልፍ ስለ ነሳው
የነገሥታት ንጉሥን_አስቦ ሊያገኘው
ከዚህ ድንቁርና _ ሰውረን ማለት ነው።
የነፍሳቱ ደም_ ወረደ እንደ ጎርፍ
በዚያች ከተማ _ ቤተልሔም ደጃፍ
በከንቱ ሰዋቸው_ በመሰለው ነገር
ሕፃኑ ግን ሸሽቷል_ ወደ ሌላ ሀገር
የሥላሴ ጥበብ _ ከቶ አይመረመር።
ዛሬም በዚህ ዘመን_ አሉ ብዙ ሞኞች
በአለማዊ ጥበብ_ በባዶ ተሟጋች
ማመን አለማመን_የነሱ ድርሻቸው
እውነትን መመስከር_የልጅ ግዴታ ነው
ሂዱና አሰተምሩ_ መልሱ ነው የሚለው።
ስለኛ ተሰዳ _ተስፋን ለሰጠችን
በልጇ ቸርነት_ ስለተጎበኘን
እንደ ቅዱሳኑ_ ነይ ነይ እንላለን።
በአፀድ በቅጽሯ_ ጽዮንን ከበናል
የአባ ጽጌ ድንግል_ በረከት ደርሶናል
በሰማያዊው ስልት_ማኅሌት ቆመናል
አቤት ያለው ደስታ_ዓለምን ያስረሳል።
ዶግማ የማይሻር_ ከቶ የማይታደስ
ሕጉ አምላካዊ_በፍፁም የማይፈርስ
ቀኖና ፍትሐዊ_ጭንቀት የሚበጥስ
ትውፊት ታሪካዊ_ ለልጅ ልጅ የሚደርስ
የእውነት ቅብብሎሽ_አንዱም አይፋለስ
ከዚህ ውጪ የሆነ_ ልቡ እንዲመለስ
በዋሻ ገደሉ _ጤዛውን በመላስ
ተግተው ይቆማሉ_ እንዳለው ጳውሎስ።
በምድራችን ሰላም_እንዲሆን ደስታ
ትውልዱ እንዲጠግብ_ በአጋፔው ገበታ
በንሰሐ ታጥቦ_ ልቡ እንዲበረታ
ድንግል ሆይ አሳስቢ_ ለታቀፍሽው ጌታ ።
የቤሌሖር ልጁ_ ወድቆ እንዲሰበር
ዳጎናዊው መንገድ_በእውነት እንዲታጠር
የዲያቢሎስ ውጊያ_በቃልህ እንዲሞት
አስነሳልን አምላክ_ የበረታ አባት
ለመንጋው እራርቶ_የሚያፀና በእምነት።
ነኽምያን ላከው_ ያንጽ ቤተመቅደስ
የአምልኮ ሥፍራ_ለሁሉ እንዲዳረስ
ሳሙኤልን ስጠን_ ወንጌልን ሰባኪ
በፀጋው በጥበብ_ራዕይን አሳኪ።
አባታችን ሙሴ_ የማርያም ወንድም
ስማን አሳስብልን_ ለመድኃኒአለም
በኑፋቄ ባሕር_ ገብተን እንዳንሰጥም
ክፈልና አሻግረን_ ተጨንቀናል በጣም
በተሰጠን ፍቅ_ ለመኖር አልቻልንም።
ከውብ ዜማው ጋራ_ ቅዱስ ያሬድ ይምጣ
ምስጢር በማፋለስ_ ከሕግ እንዳንወጣ
እናንብብ እንጠይቅ_ እንማር ከአበው
ከእውነተኛው መምህር_ለኛ ከሚገደው
አምላክ ይሰውረን_ አሁን ከምንሰመው።
እመቤታችን ሆይ አዘክሪልን!
💝🪔💝➴💝🪔💝➴💝🪔
@MENFESAWItsufoche
🪔🪔🪔🪔🪔🪔🪔🪔🪔🪔
1,6000014
፨ማኅሌት፨
ጌታ በቃሉ በመላዕክት
ዝማሬያቸው በሰማያት
በምድርም የካህናት
መአዛሽ ሳበኝ ከሩቅ
አልቻል አለኝ ካንቺ መራቅ
ከበሮ ሲመታ ሲጎሰም
ሁሉም በመቅደስ ሲከትም
ጽናጽል ሲንሿሿ ማህሌት ሲሰማ
ልቤ ሀሴትን ሲሰማ
ሕይወት ዘርቶ
መረስረስ ነው ማህሌት ሰምቶ
እጣን ሲጤስ ሃሌ ሲባል
በጣፈጠ የእግዚአብሔር ቃል
ተቀምሞ በማኀሌት
አጣፍጠውት ሊቀ ቀሳውስት
ሽብሸባቸው የዲያቆናት
በተማሩት በመላእክት
የእግዚአብሔር ቃል ይጣፍጣል
ደንዳናን ልብን ያሸንፍል
ሰይጣን ድል ይነሳል
እንግዲህ ስለዚህ ቃል
ማህሌት መላእክት ነጋሪ
እንግዲህ በስራሽ ተሰማሪ
ያልሰሙትን ዞረሽ ጥሪ
የቅዱሳን ያሬድ ቅርሳቸው
የእኛነት መለያችን
አቋቋም ዝማሜው
የመላእክት ዝማሬው
ጽናጽል ከበሯቸው
በእኛም አለ ቅዳሴአቸው
የምስጋና ትጋታቸውን።

🌹🌹🌹🌹🌹✞🌹🌹🌹🌹
✞@MENFESAWItsufoche✞
🌹🌹🌹🌹🌹✞🌹🌹🌹🌹
1,7800013
ደረሰ ሰዓቱ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ደረሰ ሰዓቱ_እንገስግስ መቅደሱ
ሊዘረጋልን ነው_ቅኔ መወድሱ
የአባ ጽጌ ድንግል_የምስጋናው ሻማ
ሊበራ ሊነድ ነው_ለነፍስ የሚስማማ።

የተመረጠቱ _ እንደየ ፀጋቸው
መቋሚያ ጽናጽል_ ከበሮውን ይዘው
የድንግልን ስደት_ በዜማ እያዋዙ
በአንደምታው ምስጢር_ በረከትን ገዙ።

ተጠርተው በፍቅሩ_ የሄዱት ምዕመናን
መስቀልያ አጣፍተው_ተውብው በብርሃን
ሐሴት ተጎናፅፈው_በቅድስቷ ድንኳን
ሲታይ በረከቱ_ መዓዛ ወ ዕጣን
ይወስዳል በሀሳብ_ ወደ ሰማይ ዙፋን።

የአምላክን ምሕረት_ፈቅዶ መሰደዱን
ከከበረው ዙፋን_ ስለኛ መውረዱን
የላከው ወደ ግብጽ_ ሙሴን ያናገረው
እሱ ነው ጌታችን_ በማርያም ያደረው።

የቅዱሳን አበው _ የነ ኢሳይያስ
የአማልእክት አምላክ_ የሁሉም ንጉስ
አዶናይ መሆኑን_የጽድቃችን ልብስ
የማኅሌት ሲሳይ_ ለኛ ሲዳረስ
ዕጹብ ድንቅ ያሰኛል_ ፍቅሩ የኢየሱስ።

የቅዱሱን መጽሐፍ_ ተርጉመው ሊቃውንት
አልቀው አርቅቀው_ ፈጽመው ሰማዕታት
ግራ እንዳይገባን_ ቀምረው ስርዓት
በደም አጥንታቸው_ለኛ አስቀመጡት
ምስጋና ይግባቸው_ በቀን በሌሊት።

የኪዳን የሳዓታት_ የቅዳሴን ትርጉም
ያስተማረን ጌታ_ ቸሩ መድኃኒአለም
ከመምህሩ ሰምተው_ ከተቡት በእምነት
በክፉዎች ሴራ_ እንዳይፋቅ እውነት።

ዛሬ የምናየው _ ኹከት ልብሱ የሆነው
በሐሰት ኑፋቄ_ ትውልድ የሚያውከው
የበግ ለምድ ለብሶ_ የዋሕ የሚያስተው
ቀድሞ ይታወቃል_ አሁን ወቅቱ እኮ ነው።

ይልቅ ይሄ ሲያይል_ ክኽደት ሲበረታ
ፈርቶ ተደናግጦ_ በመጨነቅ ፈንታ
የጸኑት ያሉትን_ የጻፉትን እንይ
ቃሉን ከሸቀጡት_ በፍጥነት እንለይ
ወርደን እንዳንጣል_ በትጋት እንጸልይ።

የተዘጋች ደጃፍ_ሕዝቅኤል የሚላት
የእሰይ ልጅ ዳዊት_ የሚያመሰግናት
ሰሎሞንም ብሏል _ የታተመች ገነት
ነቢዩ ኢሳይያስ_ የመሰከረላት
ልዑል ለማደሪያው _ አንዴ የቀደሳት
ከተሰጣት ክብር_ ማን ነው የሚያወርዳት?
ይልቅ የታደለው_ስሟን እየጠራት
በፍቅሯ ይኖራል_ ብጽዕይት እያላት።

ጊዜ የማይሽረው_ በዐለት የተጻፈ
ከሰማይ ከምድር_ እጅግ የገዘፈ
ቃሉ የማይሻር_ በዘመን እርዝማኔ
መርጧታል ኢየሱስ_ ምስክር ነኝ እኔ።

የስደቷን ነገር_ መከራዋን አይቶ
ከአለማመን መንፈስ_ ፈቅዶ ተለይቶ
የክርስቶስ ፍቅር_ እውነቱ ሲገባው
ጣቶቹን አንስቶ_ ማሕሌቷን ጻፈው
አባ ጽጌ ድንግል_ የእውነት አበባ ነው።

በብዙ ምሳሌ _ እያመሳጠረ
ለትውልደ ትውልድ_ ቅኔን አስተማረ
ኋላ የተጠራው_ ቀድሞ ተከበረ
ወድቆ መነሳቱን_ ቆሞ መሰከረ
እናት ተዋሕዶ_ምስጢርሽ ደመረ።

            ድንግል ሆይ
በስደትሽ ስደታችንን _ባርኪልን
ከልጅሽ ቸርነት _ ለምኚልን
ፍቅር አንድነትን_ ደራርቢልን
ከክፉ መናፍስት_ በኪዳንሽ ጠብቂን
መስሏቸው ከበረቱ_ ክደው የወጡትን
በአማላጅነትሽ_ መልሽልን
አሜን አሜን አሜን
                   ከእህተ ማርያም
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
@MENFESAWItsufoche
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
4,1300039
Photo1/2
እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን ከመድሃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለተሰደደችበት መታሰቢያ ለሆነው ፆመ ፅጌ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
ይህ ፆም በፍቃድ የሚፆም ሲሆን ከመስከርም 26 እስከ ህዳር 6 ይፆማል።
መልካም ፆም ይሁንልን!
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
@MENFESAWItsufoche
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
3,150007
የተዋህዶ ልጆች እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!!!
ይህ ክብረ በዓል በግሸን ደብረ ከርቤ በልዩ ሁኔታ ይከበራል።
የእናታችን ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን!!!
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
@MENFESAWItsufoche
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
3,700007
መስቀል ኃይላችን ነው
✨✨✨✞✨✨✨
የነገር መስቀሉን መነሻ
የታሪኩን መዳርሻ
መርምራ ለማወቅ ብትሻ
እመቆስጠንጢኖስ ንግስት እሌኒ
ተደብቋት መቼ ቀረ
ምስጢር ሆኖ እንደተቀበር፡፡
በባዕድ ሃገር በኢየሩሳሌም
ሐይማኖቷን ደብቃ
ለእውነት ተነስታ ፀንታ ታጥቃ
ተራ ሰው መስላ ራሷን ንቃ
መስቀሉን አስቀድማ
ስታስፈልግ በገጠር በከተማ
ኪራኮስ እስራኤላዊው
በአምላክ ቃል እያፅናናት
የመስቀሉን ቦታ እየመራት
ደመራውን ደምራ
የዕጣኑ ጢስ ምልክት ሆኖ
መስቀሉ ተገኘ ተቆፍሮ
ምቀኞችን አሳፍሮ፡፡
ደውያንን እየፈወሰ
አንካሶችን እየረታ
ጎባጣዎችን እያነፃ
ዕውራንን እያበራ
ሙታንን እያስነሳ
ዜናው ተሰማ በዓለም ዙርያ፡፡
ጥበበኞች ነን ባዮቹ
የአይሁድ ካህናት ግብዞቹ
መጎብኘታቸውን ያላወቁ
ሰላማቸውን የናቁ
መዳኛቸውን የርሱ
በስራቸው የረከሱ
መስቀሉን ቢቀብሩትም
አልቻሉም ሊሰውሩት
ከእሌኒ ንግስት ሊሸሽጉት
ዝናውን ከቁስጠንጥንያ
ከዚያም አልፎ በኢትዮጵያ
እየተባለ ሃሌ ሉያ፡፡
እስኪ እኛም ይመርብን
የመስቀሉን ቃል እንዲያድርብን
በአዲስ ምስጋና በዝማሬ
ደመራውን እንደምር
ተሰባስበን በመስቀሉ ዙርያ
መስቀል ኃይላችን ነው
መስቀል ፅንአችን ነው
መስቀል ቤዛችን ነው
መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው
እየተባለ እያሰተጋባ
እየተበተነ አደይ አበባ፡፡
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
@MENFESAWItsufoche
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
5,6200014
መስቀል ሃይላችን ነው ፣መስቀል መፅናኛችን ነው ፣ መስቀል የነፍሳችን መድሃኒት ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው ።አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን ያመነውም እኛ በመስቀሉ እንድናለን ድነንማል።
የተወደዳቹ የቻናላችን ቤተሰቦች
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
🪔✨🪔✨🪔✝✨🪔✨🪔✨🪔
   @MENFESAWItsufoche
✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨
5,620009
ዘመን እንደዋዛ
✨✨✨✨
ሰከንድ ደቂቃውን ደቂቃ ሰዓቱን
እያደገ ሲሄድ ሰይገታ ጉዞውን
በዚህ ሳያበቃ ሰዓት ቀንን ወልዶ
ቀኑም ሳምንት ሲሆን ተሻግሮ ተራምዶ
ሳምንትም በተራው ወራትን ሲተካ
የተቦካው ሲያልቅ ተፈጭቶ ሲቦካ
ወራት ወደ አመታት በአንዴ ሲቀየሩ
እረፋት የለሽ ሰዓት ሲዞር መዝወሩን
እድሜዬ አብሮ ሮጠ አለፈ ዘመኔ
ጆሮዬ እየሰማ እያየኹት በዓይኔ።
ብልጭ ድርግም ስትል ያቺ ፈጣን ሰኮንድ
በእጄ ላይ አስርያት ተቀምጣ በእኔ ክንድ
እኔ ስስቅባት ፍጥነቷን እያየሁ
ምንድን አስቸኮለሽ አጣደፈሽ እያልሁ
ለካስ ምስጢር አላት ዘመን ትቆጥራለች
በእድሜ መቀለዴን ነጋሪ ኖራለች።
እኔ መች ተረዳሁ ምስጢሩ መች ገባኝ
እብድነች እላለሁ ለካስ እብዱ እኔ ነኝ።
ዛሬ ባስታውሰው ያለፈ ዘመኔን
የሰኮንድ ደቂቃ የሰዓት ምስጢሩን
የሳምንት የወራት የዓመታት ድምሩን
ለካ ሄዶብኛል
ዘመን አልቆብኛል
በራሴ ላይ ሆኖ ሞት ይስቅብኛል።
ልጠይቅ እራሴን ምን ሰራሁ በእድሜዬ❔
በኖርኩበት ዘመን በዚህ ቆይታዬ
አንድ ነገር ቀረቶኛል
ጭንቀት ይሰማኛል
ኑሮ እንዴት እንደሆነ ማሰብ ተስኖኛል
የእኔነቴ መሰረት አምላክ ከእኔ ርቋል።
አዎ❕አሁን ገባኝ ሁሉ የእድሜ አቆጣጠሩ
የሳምንት የወራት የዓመታት ምስጢሩ
ያለ ቅጽበት ዕረፍት በፍጥነት መብረሩ
ሰዓት በእርሷ ስስቅ ለካ ትስቃለች
እግሬን ወደ ጉድጓድ ይዛ ትሮጣለች።
እኔማ መች ገባኝ ቁም ነገር መሥራቷ
በሕይወቴ ዙርያ በእድሜ መጫወቷ።
ከአምላክ መለየቴ መች ተገለጸልኝ
እርቃኔን መቆሜን ማን አይቶ አለበሰኝ።
ውሃና ሳሙና ተቀምጦ በፊቴ
አድፌን ሳላስወግድ ድረስ ሰዓቴ
አይ ዘመን❕
አምላክ ለእኔ አስቦ ተጨንቆ ተጠበበ
ለንስሐ ብሎ ጊዜዬን ቆጥቦ
ምህረት ቢለግስኝ ወደ እረሱ እንድመለስ
እኔ ግን ዘነጋሁት መስቀሉን ማስታወስ።
እስኪ አንተም ንገረኝ
በይ አንቺም ንገረኝ
ዘመንህ እንዴት ነው❔
ዘመንሽ እንዴት ነው❔
የአጠቃቀም ስልቱ ዘዴው እንደምን ነው❔
በሃሜት በወሬ ወይስ በለቅሶ ነው❔
በወሬም ይቆጥራል
በሃሜት ይበራል
በፀሎትም ያልቃል
ከእንባ ጋር ይወርዳል
ጊዜማ መብረሩን መች አቁም ያውቃል።
ግን ቁጥሩ አንድ ቢሆንም ጥቅሙ ይለያያል።
እናም የእናቴ ልጅ ዘመንህን ተመልከት
ሃሜቱን ተውና ንስሐ ግባበት
ሃሜቱን ተይና ንስሐ ግቢበት
ኮንትራትህ ሲያልቅ ቁም ነገር ሥራበት
በላይ በሰማያት ስንቅን አስቀምጭበት።
በሉ አሁን ተነሱ ያለፈው ይብቃና
እኔም አንተም አንቺም ንስሐ እንግባና
ከአምላክ እንታረቅ
መንገዱን እንወቅ
ቀሪ ዘመናችን ከእርሱ ጋራ ትዝለቅ።
ስብሐት ለእግዚአብሔር
✍ገጣሚ መምህር አለምቀረ ሙሉ

🌻🕊️🌻✨🕊️🌻✨🕊️🌻✨🕊️🌻
@MENFESAWItsufoche
🌻🕊️🌻✨🕊️🌻✨🕊️🌻✨🕊️🌻
8,1100053
ይህን ያወቁ ኖራል?
✨✨✨✨✨✨✨
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ  ስፍረ ሰዓት/ሰዓት አቆጣጠር/
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

  የመስከረም ወር   ቀኑ 12 ሰአት ለሊቱ 12 ሰኣት ነዉ፡፡

  የጥቅምት ወር     ቀኑ 11 ሰኣት ለሊቱ 13 ሰኣት ነዉ፡፡

  የህዳር   ወር      ቀኑ 10 ሰኣት ለሊቱ 14 ሰኣት ነዉ፡፡

  የታህሳስ  ወር      ቀኑ 9 ሰኣት ለሊቱ 15 ሰኣት ነዉ፡፡

  የጥር   ወር           ቀኑ10 ሰኣት ለሊቱ 14 ሰኣት ነዉ፡፡

  የየካቲት  ወር      ቀኑ 11 ሰኣት ለሊቱ 13 ሰኣት ነዉ፡፡

  የመጋቢት ወር      ቀኑ 12 ሰኣት ለሊቱ  12 ሰኣት ነዉ፡፡

  የሚያዝያ  ወር      ቀኑ 13 ሰኣት ለሊቱ 11 ሰኣት ነዉ፡፡

  የግንቦት   ወር   ቀኑ 14 ሰኣት ለሊቱ 10 ሰአት ነዉ፡፡

  የሰኔ    ወር    ቀኑ 15 ሰኣት ለሊቱ 9 ሰኣት ነዉ፡፡

  የሀምሌ  ቀኑ 14 ሰኣት ለሊቱ 10 ሰአት ነዉ፡፡

  የነሃሴ እና ጳጉሜ  ቀኑ 13 ሰኣት ለሊቱ 11 ሰኣት ነዉ፡፡
   ፨ምንጭ ኣቡሻክር እና ስንክሳር
እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰለም አሸጋገርዎ
ወስብሃት ለእግዚአብሔር

🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🌼@MENFESAWItsufoche🌼
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼
6,2000022
አዲስ ዓመት 2019 ዓ.ም
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ውድ የተዋህዶ ልጆች እና የቻናላችን ተከታታዮች እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገራቹ አሸጋገረን!
እግዚአብሔር አምላክ ዘመኑን የሰላም ፣ የበረከት፣ የደስታ እና የምህረት ያድርግልን! መልካም በዓል !
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
@MENFESAWItsufoche
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
5,690000
Photo
የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረገት ነሐሴ 16 ቀን
ረድኤት በረከቷ ምልጃ እና ፍቅሯ አይለየን አሜን!!!
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
5,5100017
ደብረ ታቦር
.
.
ብርሃነ መለኮት ከተገለፀበት፤
መልኩ ተለዉጦ ፀዳል በሆነበት፤

አብም ስለ ልጁ እርሱን ስሙት ብሎ ከመሰከረበት፤
የጌታ አምላክነት የሥላሴ ምስጢር ከተሰበከበት፤

ልብን ከሚመስጥ ከዚህ ድንቅ ስፍራ፤
መንፈስ ከሚያድስ ከታቦር ተራራ፤

በዚህ መኖር ለእኛ .......
እጅጉን መልካም ነዉ ከጌታችን ጋራ።

✨እንኳን አደረሳችሁ✨

በዔደን ታደሰ
🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨

🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨
5,9700023
በደብረ ታቦር
🌿🌿🌿🌿
መለኮት ተገለጠ በደማቅ ብርሃን አበራ
በተቀደሰው የታቦር ተራራ።
የአብ አባትነት የወልድ ልጅነት
በግልጽ ታወቀ ተነገረ በእውነት
ዮሐንስ ጴጥሮስን ያዕቆብን ጠርቶ
ሙሴን ከመቃብር ከሙታን አንሥቶ
ከብሔረ ሕያዋን ኤልያስን አምጥቶ
በአምላክነቱ ፍጹም አንጸባርቆ
በሕያው መለኮቱ በብርሃን ደምቆ
አብም ተገለጠ በብሩህ ደመና
የምወደው ልጄ ክርስቶስ ነውና።
እርሱን ብቻ ሰሙት እስከ ዘለዓለም
ሕይወት በእርሱ ነው ያለርሱ አትድኑም።
ብሎ ስለልጁ በግለጽ መሰከረ
አምላክነቱንም በተግባር ነገረ።

➴ከሀብታሙ ገበያው
➴🍁➴🍁➴🍁➴🍁➴🍁➴

👆👆👆👆👆👆👆👆👆
5,2000015
፨ፍልሰታ፨
🍁🍁🍁🍁
ትፈራው ነበረ ያን መልአከሞት
የልጅሽን ፅዋ ቅመሽው አላት
ይጠፋል ኩነኔ ይጠፋል አበሳ
እንደ ፈጣሪያችን ማርያም ስትነሳ
እየባረከቻት ኢትዮጵያን በእጆቿ
በይባቤ አረገች እሷም እንደ ልጇ
ከሰው የተለየች መሆኗን ሲያበስር
ሞት በጥር ሆነ ነሃሴ መቃብር
አይሁዳዊው ቀንቶ ሲሰርቅ ሥጋዋን
የመለኮቱ ሰይፍ ቆርጠው እጁን
ብዙው ይጾመዋል የፍልሰታን ፆም
ከእህል ተከልክሎ ከሥጋ ከደም
ሐዋርያው ፊሊጶስ ትንሣኤዋን ሲሻ
ከወንድሞቹ ጋር ዕርገቷንም ሲሻ
በስሟ ተነሱ ሊፆሙ በጋራ።

የበረከት ፆም ያድርግልን!

➴🍁➴🍁➴🍁➴🍁➴🍁➴

👆👆👆👆👆👆👆👆
8,4100038
Photo
እንኳን ለፆመ ማርያም የፍልሰታ ፆም በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!
በዚህ ፆም ሱባኤ የእመቤታችን ፍቅሯን የሚያበዛልን፣ ለሃገራችን ፍፁም ሰለምና መረጋጋትን፣ ለህዝባችን ፍቅርን እና መተሳሰብን ፣ለቤተክርስቲያናችን ሰላምን ምናገኝበት ያድርግልን አሜን!!!
✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯

✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯
7,7800018
Photo
የንጉስ ጭካኔ ፥ ክንዱ ቢበረታ፤
ለጣዖት ሳንሰግድ፥ እኛ ሳንረታ፡፡
የምናምነው አምላክ፥ ሊያድነን ወደደ፤
ገብርኤል መጣና፥ እሳቱ በረደ፡፡
፤
ፍላፃና ሠይፉን፥ አጠፈው መላኩ፤
ሰላም ይዞ መጣ፥ ባለም ለታወኩ፡፡
አትጠራጠሩ፥ ምልጃው ያስምረናል፤
የሚነደው እሳት፥ ሳይነካን ወተናል፡፡
፤
የሰልስቱ ደቂቅ፥ የእየሉጣ ብርታት፤
የድንግል አብሳሪ፥ የቂርቆስ ረዳት፡፡
በሚመጣው አለም፥ እንዳይበላኝ እሳት፤
አማልደኝ ከጌታ፥ ነፍሴን እንዲምራት፡፡
፤
የነገርኩህ ሁሉ፥ በቀኑ ደረሰ ፤
በዘብር ገብርኤል፥ እንባዬ ታበሰ፡፡
ና ልጄ ስትለኝ፥ አልልህም እንቢ፤
ስለቴን ተቀበል፥ አባቴ ቁልቢ፡፡
፤
የልቤን ነግሬህ፥ የቁልቢው ገብርኤል፤
ሳትረሳ ፈፀምከው፥ ስለቴን ተቀበል፡፡
ለንግስ እንመጣለን፥ አንተ አትረሳምና፤
ደሞ የዛሬ አመት፥ አድርሰን በደህና፡፡
+++++++

እንኳን ለሃያሉ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!!

🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔

🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔
8,2800030
Photo
እንኳን ለአጋዕስተ ዓለም ለቅድስት ስላሴ ዓመታዊ በዓለ ክብር በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!!!
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
10,7000037
መነባንብ
፨፨፨፨፨፨
ክፍል፬

@MENFESAWItsufoche
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔

ዘራፍ!2🔔 ፍቅርን ታጥቄ ፍቅርን ለብሼ
በንስሐ እንባ ውስጤን አድሼ
የጌታን ስጋ ደሙን ጠጥቼ
በቤትሽ ኖሬ ደጅሽ ፀንቼ
አሁንም ልኑር ጡትሽን ጠብቼ
ዘራፍ!2🔔ማነው የሚነካሽ የታለወንዱ
ቢፈራገጥም አምላኩ ሆዱ
መሠረትሽን ከቶ አይንዱ
ዘራፍ!2🔔የቄርሎስ ምላሽ ጥንተ ሃይማኖት
የአባ ጊዮርጊስ ፀሎት ደረሰቱ
የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል ስብከት
የአግናጢዎስ የአንበሳ ራቱ
የአባ እንጦስ ብርታት ፅናቱ
የቅዱስ መቃርስ ምናኔ ቤቱ
የቅዱስ ያሬድ ዜማ ስርዓቱ
የአትናቴዎስ ብርታት ስደቱ
የአረጋዊ ወዳጅ እናቱ።
ዛሬም ይስማል ስዓታት ቅኔሽ ዚቅ ማህሌቱ
ይከበራል ነገም ገና ከፍ ይላል መስቀል ፅላቱ
እማ ተዋህዶ መቼም አትጠፋም ይሰማ ፍጥረቱ2
አትጠፋም... አትጠፋም
አትጠፋም.... እማ ተዋህዶ❕

#ስብሐትለእግዚአብሔር
#ለአለምወለአለምአሜን!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

/ተፈፀመ ዝንቱ መነባንብ\
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

➴💝➴💝➴💝➴💝➴💝➴
@MENFESAWItsufoche
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
6,1100019
።።ቅኔና--ውዳሴሽ።።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ቅኔና ውዳሴሽ ምግብ መጠጣችን
ማር የሆነው ስምሽ የመንገድ ስንቃችን
ፍቅርሽ እንደ ዕሳት__ ይነዳል ውስጣችን
ንኢ ንኢ ስንል ባርኪን እናታችን።

ልቡ ያዘነውን አዳምን ሊያፅናና
ትካዜውን ሊቀብር__የሞቱን ጎዳና
ማደሪያው አድርጎሽ__የሰማዩ መና
አዳነው ክርስቶስ__ ይድረሰው ምስጋና
ከወጣበት ገነት___ ተመልሷልና።

ካንቺ ተወለደ__ ያለ ወንድ ዘር
የሔዋን እርግማን__ወድቆ ሊሰበር
ያሳታት ዲያቢሎስ__ሲዖል ሊታሰር
ሥጋ ለብሶ ታየ__ ወልደ እግዚአብሔር።

ሰው የሆነና በኛ ያደረ ቃል
ኢየሱስ ክርስቶስቅዱስ አማኑኤል
መሆኑን ነገረን__ነበዩ ኢሳይያስ
አየነው ተጽፎ__ በመጽሐፍ ቅዱስ።

ሰው ሆይ ደስ ይበልህ__ተነስ ለምስጋና
እግዚአብሔር ዓለሙን__እንዲሁ ወዷልና
በአንድ ልጁ እንድናምን
ልዑል ክንዱን ሰደደልን።

የነበረው የሚኖረው__የማያልፈው ለዘለአለም
ከላይ ወርዶ ሰጠን ሰላም
በሥራው ሁሉ አልተለየም
ወልደ እግዚአብሔር__ ወልደ ማርያም።

ቅድስት ሆይ ለምኝልን
በበደልነው እንዳይቀጣን
ለንሰሀ ዕድሜን ይስጠን
በኪዳንሽ ተማፀንን።

የእግዚአብሔር ቃል መለኮት
የለበትም ሦስትነት
አንድ ብቻ__ነው እውነት
የሥላሴ__ቸርነት።

እንደ አበው__ ባንበቃ
ስምሽ ሆኖን__ ዋስ ጠበቃ
ደስታችን ሆኖ__ሲቃ
ልመናችን ሰምሮ ባንቺ
አማለደሽን ሳትሰለቺ።

ተሰበሰብን ልንጠራሸ
ማርየም ሆይ ቆምን ደጅሽ
የዘለአለም ዓንባችን ነሽ
ዕርስታችን የወረስንሽ።

እመቤታችን ሆይ የቅዱስ ኤፍሬምን በረከት አሳድሪብን Amen
ኢትዮጵያን ሰላም አድርጊልን
ልመናችንን አሳ ርጊልን።

➴ ከእህተ ማርያም
➴💝➴💝➴💝➴💝➴💝➴

👆👆👆👆👆👆👆👆👆
12,8000063

Showing 30 of 67 posts

Avaliação

Login necessário

Frequently Asked Questions

Sobre o que é o canal Telegram 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻?+

🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻 (@menfesawitsufoche) é um canal Telegram listado em IPL no tgdio. Ranking, avaliações, reviews e posts recentes para decidir antes de assinar. Atualmente lista cerca de 30.952 inscritos no tgdio.

Como entrar em 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻 (@menfesawitsufoche) no Telegram?+

Abra o perfil no tgdio e use Join / Open in Telegram para assinar @menfesawitsufoche de graça.

🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻 é um bom canal de IPL?+

No tgdio você pode ver avaliação, reviews, ranking e posts de 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻 antes de entrar. Atualmente lista cerca de 30.952 inscritos no tgdio. Compare com canais similares de IPL.

Onde ver estatísticas e posts de 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻?+

No tgdio, abra @menfesawitsufoche para stats de inscritos, ranking, avaliações e posts. Use Stats para gráficos.