ጌታ በቃሉ በመላዕክት
ዝማሬያቸው በሰማያት
በምድርም የካህናት
መአዛሽ ሳበኝ ከሩቅ
አልቻል አለኝ ካንቺ መራቅ
ከበሮ ሲመታ ሲጎሰም
ሁሉም በመቅደስ ሲከትም
ጽናጽል ሲንሿሿ ማህሌት ሲሰማ
ልቤ ሀሴትን ሲሰማ
ሕይወት ዘርቶ
መረስረስ ነው ማህሌት ሰምቶ
እጣን ሲጤስ ሃሌ ሲባል
በጣፈጠ የእግዚአብሔር ቃል
ተቀምሞ በማኀሌት
አጣፍጠውት ሊቀ ቀሳውስት
ሽብሸባቸው የዲያቆናት
በተማሩት በመላእክት
የእግዚአብሔር ቃል ይጣፍጣል
ደንዳናን ልብን ያሸንፍል
ሰይጣን ድል ይነሳል
እንግዲህ ስለዚህ ቃል
ማህሌት መላእክት ነጋሪ
እንግዲህ በስራሽ ተሰማሪ
ያልሰሙትን ዞረሽ ጥሪ
የቅዱሳን ያሬድ ቅርሳቸው
የእኛነት መለያችን
አቋቋም ዝማሜው
የመላእክት ዝማሬው
ጽናጽል ከበሯቸው
በእኛም አለ ቅዳሴአቸው
የምስጋና ትጋታቸውን።
🌹🌹🌹🌹🌹✞🌹🌹🌹🌹
✞@MENFESAWItsufoche✞
🌹🌹🌹🌹🌹✞🌹🌹🌹🌹










