1/2በብዙዎች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው "የቅን ልቦች 2018 የበጎ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ" የአሸናፊዎች አሸናፊ (Champions of Champions) የምሽቱ ታላላቅ አሸናፊዎች በይፋ ታውቀዋል።
በዚህ ድንቅ እና ታሪካዊ የምሽቱ መርሃ ግብር ላይ በበጎ አርዓያነታቸው፣ በቅንነታቸው እና በማህበረሰቡ ላይ ባሳደሩት አዎንታዊ ተፅዕኖ አሸናፊ መሆን የቻሉት፦
1ኛ ደረጃ (የአሸናፊዎች አሸናፊ)፦ አቲስነማ ቻሪቲ —
የ100 ግራም ወርቅ ታላቅ ሽልማት ባለቤት በመሆን የመጀመሪያውን ደረጃ ተጎናጽፏል!
2ኛ ደረጃ፦ አዶናይ — የ50 ግራም ወርቅ ተሸላሚ በመሆን የሁለተኛ ደረጃን ክብር ጨብጧል!
3ኛ ደረጃ፦ አወንታ በርሲሳ — የሦስተኛ ደረጃ አሸናፊ በመሆን የኮከብነት ማዕረጉን ተቀናጅቷል!
ለማህበረሰባችን የብርሃን እና የተስፋ ምንጭ በመሆን ላሳያችሁት ድንቅ በጎ አርዓያነት፣ አርአያዊ ተግባር እና ለወገናችሁ ላላችሁ ወሰን የለሽ ፍቅር እጅግ በጣም እናመሰግናለን!
ለመላው አሸናፊዎቻችን እንኳን ደስላችሁ እንላለን፤ የበጎነት፣ የቅንነት እና የድል ጉዟችሁ ከፍ ብሎ ይቀጥል!
©️ቅንልቦች
ጉርሻ Page
🌴🌴🌴








