1/2አምና ግንቦት ወር ላይ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የፕሮጀክት ማናጀር የነበሩት አቶ ብርሀኑ አለቃ ሲፈፅሙት የነበረውን ምዝበራ መሠረት ሚድያ ደርሶበት ጥያቄ ሲያቀርብላቸው የሚከተለውን ማስተባበያ ልከውልን ነበር፣ ዛሬ እንደሰማነው ግን ከ1.1 ቢልዮን ብር በመመዝበር ክስ ቀርቦባቸዋል።
በዚህ ገንዘብ ደግሞ ቢያንስ ስድስት ቤቶችን በ223 ሚልዮን ብር ገዝተው እንዲሁም 68 ሚልዮን ብር የሚያወጣ መኪና ሸምተው ሲንፈላሰሱ ነበር።
አይኔን ግንባር ያርገው ብለው የዛሬ አመት ለመሠረት ሚድያ የላኩት ማስተባበያ ይሄ ነበር ⤵️
በመረጃችሁ የተነሱ ሃሳቦች ላይ መረጃ ከመስጠቴ በፊት የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አዋጅ ከ30 ዓመት በላይ ሴት ልጆቻችን አረብ ሀገር ሲሄዱ፣ እንቅልፍ አጥተው ሰርተው ወደ ሀገራቸው እንደ ሌባ ተቆጥረው ሲኖሩ ጤነኛ ሆነው ሄደው አካላቸው ጎድሎ ሲመለሱ በበረሃው የፈሰሰው ደማቸው፣ በየሰው ቤት ያዩት እንባ… ብዙ… ብዙ… ስቃያቸው የሚታበስበት እና ዜጎች መብታቸው፣ ደህንነታቸው እና ጥቅማቸው ተጠብቆ እንዲሰማሩ የሚያደርግ አፅድቀናል።
እንዴት ? ምን ማለት ነው:: የሚል ጥያቄ ሊኖር ይችላል !! በ ሚዲያችሁ በተጋራው የመረጃ Frame መሰረት ሃሳቤን ላስቀምጥ!
1. ሰራተኛ ወደ ውጭ ሀገር የስራ ስምሪት የሚያሰማራ ማንኛውም ኤጀንሲ ፍቃድ ከመውሰዱ በፊት ለዜጎች ደህንነት ዋስትና የሚሆን 100,000 ዶላር በባንኮች በዝግ አካውንት እንዲንቀሳቀስ ያስቀምጣል:: የሚል ቀደም ሲል የወጣ አዋጅላይ ስለተቀመጠው አንቀጽ…
ይህ ገንዘብ ዜጎች ደሞዝ ሳይከፈላቸው… በካሳ መልስ ለመክፈል፣ ጉዳት ቢደርስባቸው… የሚገባቸውን ካሳ ለመክፈል፣ ቢታመሙ… ለማክመምና፣ ዜጎች የላካቸው ኤጀንሲ ወደ ሀገር እንዲመልሳቸው ሲጠየቅ እምቢ ቢል… ትኬት ቆርጦ ለመመለስ:: በአጠቃላይ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ትእዛዝ ይህንን ለመፈጸም የሚውል ካሽ ገንዘብ ነው::
ይህ ገንዘብ ባንክ ተቀምጧል ወይ ? ኤጀንሲዎች ከባንኮች ማናጀሮች ጋር በፈጠሩት ጥቅም ትስስር ባንኮች በዝግ አካውንት እንደተቀመጠው አድርገው ሐሰተኛ ደብዳቤ እና የባንክ ስቴትመንት ለኤጀንሲዎች በመስጠት የተቀመጠው ገንዘብ ሲጠራ ከ10% በታች ኤጀንሲ ብቻ ማስቀመጡ ተረጋግጧል::
ባንኮች ገና ለገና ኤጀንሲዎች ዜጎቻችን አረብ ሀገር ሄደው ዶላር ያመጡልናል በሚልና በገንዘብ የተደለሉ ማናጀሮች በሚሰጡት ማስረጃ የተላኩ ዜጎች በባርነት ወደ ኢራቅና ሶሪያ ቢልኳቸው ምንም የሚያስነካቸው ነገር አይኖርም:: የሚወረስ ገንዘብ የላቸውም !! ደህንነቱ ያልተጠበቀ ቦታ ልጆቻችን ቢወድቁ የሚያስፋፍራቸው ነገር የለም:: ይህ ማለት በቃይ አልፈው ለሃገራቸው የሚበቁ ዜጎችን ለመደገፍ የሚሆን በዝግ አካውንት የተቀመጠ ገንዘብ የለም ማለት ነው::
ይህንን ገንዘብ ለዜጎቻችን ዋስትና በሚሆን መልኩ ወደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አካውንት ይቀመጥ ማለት ይህንን ችግር ሙሉ ለሙሉ መቅረፍ ይቻላል ማለት ነው:: እንደምሳሌ እንኳን ብናይ በተመሳሳይ ዘርፍ እጅግ ስኬታማ የሆኑ ሃገራት የተለመደ የ አሰራር ስርዓት ነው:: ምሳሌ ፊሊፒንስ፣ ኬንያም በተወሰነ መልኩ፣ ኡጋንዳ፣ ስሪላንካ እና ሌሎችም…
ስራውን ማቆም እፈልጋለሁ የሚል ማንኛውም ኤጀንሲ ለዜጎች ዋስትና ያስያዘውን ገንዘብ በየትኛውም ጊዜ መውሰድ እንደሚችል ደግሞ ተቀምጧል::
2 የሰለጠኑ ዜጎችን ለኤጀንሲዎች የሚደረግ ምደባን በተመለከተ
አንድ ሰው ወደ ውጭ ሃገር ለስራ የሚያሰማራ ኤጀንሲ በሚልከው በእያንዳንዱ ሰው በትንሹ $900 ዶላር ያገኛል:: ኤጀንሲዎች ይህ ብር አልበቃ ብሏቸው ከደላላ ጋር በመመጣመር ወደ ውጭ ለስራ ለሚሄድ ሰው በትንሹ ከ60,000 - 80,000 ብር ይቀበላሉ:: የሚሄዱ ልጆች ብሩን ቀጥታ ለኤጀንሲው አይሰጡትም ! በደላላው በኩል ነው የሚከፈለው… ብር የከፈሉ ዜጎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ጥቅም በሚሰጡበት ጊዜ ኤጀንሲውንና ልጆቹን ቆጭ አድርገን ስንመረምር ኤጀንሲ ከመስሪያ ቤቱ በላይ "በነጻ ለሚደረግ ጉዞ ለምን ትከፍላለሽ ብሎ ልጇ ላይ በመጮህ ድራማ ይሰራሉ:: ይህ በኤጀንሲዎች የሚደረገው ህገወጥ ተግባር በአብዛኛው ኤጀንሲ የሚፈጸም ነው::
ይህ ተግባር የሚፈጸመው ለብዙ ዓመታት ደላሎችና በኤጀንሲዎች መካከል ለብዙ ዓመታት የቆየ ትስስር ስላለ ነው:: ይህ ትስስር ካልተበጠሰ ዜጎቻችንን ከብዝበዛ ማዳን አይቻልም ተብሎ ችግሩን ለመፍታት ጥረት ተደርጋል:: በዚህ መሰረት ኤጀንሲው ወደ ውጭ ሃገር መላክ በሚፈልገው መስፈርት መሰረት (ተቀባይ ሃገር የሚገኘው ፓርትነር በሚሰጠው መስፈርት መሰረት) ሰልጣነው ከተቀመጡ ዜጎች ውስጥ እንዲወስዱ ማድረግ ነው:: በዚህ መንገድ ደላላ ያላመጣበት፣ ገንዘብ አያመጣ/ጣ ማለት የማይደፍረውን ሰራተኛ ያገኛል ማለት ነው::
ብርሃኑ አለቃ
የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የፕሮጀክት ማናጀር












