Ethiopia Check Telegram channel photo

Ethiopia Check

@ethiopiacheckPublic Channel

ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።

3.3k

Last views

24.8k (24,814 subscribers)
Membros
—
Rating
52
Total Posts
Oct 20, 2026, 9:25 PM
Atualizado
Mar 31, 2026
Created
Stats

Você está vendo conteúdo em português. Para ver conteúdo em outros idiomas, mude o idioma do site.

Channel Information

Channel Information
Channel NameEthiopia Check
Username@ethiopiacheck
CategoryExames Públicos
Languageportuguês
CountryBrasil
Membros24,814
Channel TypePublic Channel
Created31 de mar. de 2026
Last Updated20 de out. de 2026 • há 3 dias
StatusActive

Classificação

Classificação Global
#208036+210
Classificação por Idioma
#4589+4
Classificação por Categoria
#677+8

Crescimento de Participantes

Total: 24.8K30 Days growth: -420.2%
09/2109/2610/0110/0610/1110/1610/20
Crescimento de Participantes - 30 Days
DateSubscribers
21:09:202624,856
22:09:202624,856
23:09:202624,856
24:09:202624,856
25:09:202624,856
26:09:202624,856
27:09:202624,856
28:09:202624,856
29:09:202624,856
30:09:202624,856
01:10:202624,856
02:10:202624,856
03:10:202624,856
04:10:202624,856
05:10:202624,856
06:10:202624,856
07:10:202624,856
08:10:202624,856
09:10:202624,856
10:10:202624,856
11:10:202624,856
12:10:202624,856
13:10:202624,866
14:10:202624,866
15:10:202624,866
16:10:202624,866
17:10:202624,866
18:10:202624,866
19:10:202624,866
20:10:202624,814
Crescimento de Participantes - Weekly
DateSubscribers
Week of 30:03:202624,974
Week of 06:04:202624,952
Week of 13:04:202624,988
Week of 20:04:202624,997
Week of 27:04:202624,997
Week of 04:05:202624,997
Week of 11:05:202624,961
Week of 18:05:202624,961
Week of 25:05:202624,961
Week of 01:06:202624,883
Week of 08:06:202624,883
Week of 15:06:202624,859
Week of 22:06:202624,869
Week of 29:06:202624,869
Week of 06:07:202624,869
Week of 13:07:202624,894
Week of 20:07:202624,889
Week of 27:07:202624,886
Week of 03:08:202624,886
Week of 10:08:202624,886
Week of 17:08:202624,896
Week of 24:08:202624,868
Week of 31:08:202624,874
Week of 07:09:202624,874
Week of 14:09:202624,856
Week of 21:09:202624,856
Week of 28:09:202624,856
Week of 05:10:202624,856
Week of 12:10:202624,866
Week of 19:10:202624,814
Crescimento de Participantes - Monthly
DateSubscribers
March 202624,998
April 202624,997
May 202624,961
June 202624,869
July 202624,889
August 202624,868
September 202624,856
October 202624,814
Crescimento de Participantes - Yearly
DateSubscribers
202624,814

Top 10 posts

Most viewed posts from this channel

By views
  1. #1#FactCheck የገቢዎች ሚኒስቴር ዴኤታዋ "በዚህ አመት ከእገታ አምስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል" ብለዋል 15.7K
  2. #2#FactCheck ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አይ ኤም ኤፍ (IMF) ስለ ኢትዮጵያ የ2026 የኢኮኖሚ እድገ15.3K
  3. #3#Monitoring በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ስደተኞች ላይ ያነጣጠሩ ሀሰተኛ መረጃዎች ጉዳይ እንዳሳሳበዉ የተባበሩ15.0K
  4. #4#FactCheck ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው እንደተሾሙ በመግለፅ የተሰራጨ14.7K
  5. #5#FactCheck ራያ ቆቦ አካባቢ እየተደረገ ያለ ውጊያ ያሳያል በሚል የተሰራጩት ምስሎች የቆዩ ናቸው14.2K
  6. #6#FactCheck በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 'የሞሐመድ ጋዳፊ የልጅ ልጅ' ተብለው የቀረቡት ግሰብ የቀድሞው የሊቢ14.2K
  7. #7#FactCheck ይህ ምስል በቅርቡ ደቡባዊ ትግራይ ላይ ተጠምዶ የሚታይ መድፍን አያሳይም14.0K
  8. #8#FactCheck ሰሞኑን በአማራ ክልል ዋድላ ወረዳ የተገለበጠ የመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪን ያሳያል በሚል እ14.0K
  9. #9#FactCheck በሸረሪና የተማረኩ 'የህወሓት ኃይሎች እና ጦር መሳሪያዎች' በሚል እየተሰራጩ የሚገኙት ምስሎች14.0K
  10. #10#FactCheck የአርሰናል ደጋፊዎች ‘የዶ/ር ዐቢይ ታማኝ ደጋፊ ነን’ የሚል መልዕክት የያዘ ባነር ይዘዉ የተ13.8K

Últimos Posts

Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

19 de out. de 2026, 05:08

#FactCheck ኢትዮጵያ በ2026 ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ‘ከፍተኛ የተባለውን’ የኢኮኖሚ እድገት እንደምታስመዘግብ IMF አስታውቋል?

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እኤአ የ2026 እና 2027 ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ እድገት ትንበያን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በርካታ ሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ። በዚህ ዙርያ ያደረግነውን ማጣራት ያንብቡ ⤵️
https://ethiopiacheck.org/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%89%a02026-%e1%8a%a8%e1%88%b0%e1%88%83%e1%88%ab-%e1%89%a0%e1%89%b3%e1%89%bd-%e1%8a%ab%e1%88%89-ethiopia/

ኢትዮጵያ ቼክ

ኢትዮጵያ በ2026 ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ‘ከፍተኛ የተባለውን’ የኢኮኖሚ እድገት እንደምታስመዘግብ IMF አስታውቋል? - ኢትዮጵያ ቼክ

ከነዚህ መካከልም “IMF ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት መካከል ኢትዮጵያ ከፍተኛ የተባለውን 9.2% የኢኮኖሚ ዕድገት እንደምታስመዘግብ አስታውቋል” የሚል ይገኝበታል። ይህ መረጃ ‘ኮፒ እና ፔስት’ በተደረገ መልኩ በበርካታ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ እንደሚገኝም ተመልክተናል።

3,270004
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

29 de set. de 2026, 06:01

Photo
#FactCheck ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከቦታቸው እንደተነሱ የሚጠቅስና በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ የሚገኘው ደብዳቤ ፌዝ አዘል እና ሀሰተኛ ነው

በኢንስቲትዩት ኦፍ ኮመንዌልዝ ተማራማሪ የሆኑትና በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ትንታኔ በመስጠት የሚታወቁት ማርቲን ፕላውት ደብዳቤውን ካጋሩ በኋላ “ሀሰተኛ እንደሆነ ተነግሮኛል፣ አጥፍቸዋለሁ፣ ይቅርታ” በማለት ከገጻቸው አንስተውታል

ሙሉ መረጃውን ያንብቡ:
https://ethiopiacheck.org/%e1%8d%8a%e1%88%8d%e1%8b%b5-%e1%88%9b%e1%88%ad%e1%88%bb%e1%88%8d-%e1%89%a5%e1%88%ad%e1%88%80%e1%8a%91-%e1%8c%81%e1%88%8b-%e1%8a%a8%e1%89%a6%e1%89%b3%e1%89%b8%e1%8b%8d-birhanu/
7,9800015
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

28 de set. de 2026, 03:14

#FactCheck እነዚህ ምስሎች ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ሰሞኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ ያረጉትን ንግግር እና የተመድ ዋና ፀሐፊ ምላሽ አያሳይም

/ኢትዮጵያ ቼክ/ -- ባለፉት ጥቂት ቀናት ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ኒው ዮርክ፣ አሜሪካ እየተካሄደ ባለው የ81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተሰናባቹ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር አደረጉ የተባለው ቃላት ምልልስ ቪዲዮ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።

ይህ ቪዲዮ በዚህ ሳምንት በርካታ ተከታዮች ባላቸው የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እየተጋራ እና በርከት ያሉ መስተጋብሮችን እያስተናገደ ይገኛል።

ይህን ቪዲዮ መረጃ ካጋሩ መካከል Umut Cagri Sari የተባለ ኤክስ ላይ ከ10 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ገፅ ይገኛል: https://x.com/umutcagrisariii/status/2104160684313383191 በዚህ አካውንት የተጋራውን ልጥፍ ወደ 91 የሚሆኑ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 14 የሚሆኑት መልስ ሰጥተውበታል።

በተመሳሳይ 1991 የተባለ ከ 1,700 በላይ ተከታዮች ያሉት የኤክስ ገፅ መረጃውን ያጋራ ሲሆን 198 የሚሆኑ የኤክስ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 32 የሚሆኑት መልስ ሰጥተውበታል። https://x.com/Meconneno/status/2104085168596070750

በተጨማሪም በርካታ የኤርትራ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች እንደሆኑ የሚጠቁሙ አካውንቶች መልዕክቱን በስፋት አሰራጭተዋል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በቪዲዮ ምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ከሰሞኑ የተደረገ ምልልስ እንዳልሆነ አረጋግጧል።

ምስልን በምልሰት በመፈለግ ባደረግነው ማጣራት ቪዲዮው ፕሬዝደንት ታዬ በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእከተኛ በነበሩበት ጊዜ መስከረም 26 2014 የተደረገ የቃላት ምልልስ መሆኑን አረጋግጧል: https://youtu.be/Sy3zq422Gj4?si=adIWo17TibZQlq_d

በዚህ ሰሞን ፕሬዝዳንት ታዬ አስቀስላሴ ኒው ዮርክ ያደረጉትን ንግግር ቪዲዮ በተለያዩ ተቋማት ገፅ ላይ ማግኘት ይቻላል: https://youtu.be/d0ekOP-ts_Y?si=wDwm2xg84qslLGMs

በዚህም መሰረት ስለዚህ እነዚህ ቪዲዮች ከአውድ ውጭ የተጋሩ እና አሳሳች መሆናቸውን አረጋግጠናል።

በተለይ በግጭት ወቅት ከአውድ ውጭ እና አሳሳች በሆነ መልኩ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታችን እንዲሁም ከማመናችን በፊት ተገቢውን ጥንቃቄ እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
Video Thumbnail
7,8000028
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

23 de set. de 2026, 19:02

Photo
#FactCheck አንድ የወደቀን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ድሮን ያሳያል በሚል እየተጋራ የሚገኝ ምስል በሰው-ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- አንድ የወደቀን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ድሮን ያሳያል የተባል ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ እንደሚገኝ ተመልክተናል። በምስሉ ‘የኢትዮጵያ አየር ኃይል ETHIOPIAN AIR FORCE’ የሚል ጽሁፍ ያለበት ድሮን ኮረብታማ አካባቢ ወድቆ ይታያል።

ከበስተኋላው ደግሞ ሚሊተሪ እና ሲቪል ልብስ የለበሱ ግለሰቦች እየጨሰ ወደሚገኘው ድሮን ሲራመዱ ይታያሉ።

ይህን ምስል ካጋሩ የፌስቡክ ገጾች መካከል ‘Zelalem Hailu (One Amhara fano)’ የሚል ስም እና ከ20 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ገጽ ይገኝበታል።

ገጹ “አንድ በሉ!….” ከሚል ጽሁፍ ጋር ምስሉን ያጋራ ሲሆን ልጥፉ በርከት ያሉ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሉ በሰው-ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ መሆኑን አረጋግጧል።

የጉግል ምርት የሆነውንና በሰው-ሰራሽ አስተውሎት የተሰሩ ምስሎች፤ ቪዲዮ እና ድምጾችን ለመለየት የሚረዳው ሲንት አይዲ ዲቴክተርን በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሉ በከፍተኛ እርግጠኛነት (very high confidence) በሰው-ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ መሆኑን ተመልክተናል።

በሰው-ሰራሽ አስተውሎት ተፈብርከው ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በስፋት እየታዩ ሲሆን በርካቶችን ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሲዳርጉም ይስተዋላል።

በመሆኑም በማህመራዊ ትስስር ገጾች የሚጋሩ አጠራጣሪ የሆኑና ትክክለኛነታቸው ያልተረጋገጠ ምስሎችን ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
8,8500040
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

10 de set. de 2026, 18:09

#MediaMonitoring ጄነራል ታደሰ ወረደ ታገቱ በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ ተናገሩ

/ኢትዮጵያ ቼክ/- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት የነበሩት ጄነራል ታደሰ ወረደ መታገታቸውን ወይም የቁም እስረኛ መደረጋቸውን አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል።

ይህ መረጃ ባለፉት ጥቂት ቀናት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ባፈሩ የፌስቡክ ገጾች እና ግለሰቦች አማካኝነት በከፍተኛ ሁኔታ ሲጋራ ቆይቷል።

ከመረጃው ዋነኛ አሰራጮች መካከል ወደ 480 ሺህ የሚጠጉ ተከታዮች ያሉት "አንዳፍታ" የተሰኘው የፌስቡክ ገጽ እና ከ507 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት "አባይ ሚዲያ" የፌስቡክ ገጽ ይገኙበታል። በተጨማሪም ከ161 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት "ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ" የተባለው ግለሰብ የፌስቡክ ገጽ ጄነራል ታደሰ የቁም እስረኛ እንደሆኑ የሚገልጽ ተመሳሳይ ዘገባ ከሌላ ገፅ ወስዶ አጋርቷል።

ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ እውነተኝነቱን ለማረጋገጥ በቀጥታ ከጄነራል ታደሰ ወረደ ጋር በስልክ ተገናኝቶ የጠየቀ ሲሆን በማጣራቱም ጄነራሉ እንዳልታገቱና የቁም እስረኛም እንዳልተደረጉ ምላሽ ሰጥተዋል።

በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ለዘገባቸው ዋቢ ያደረጉት «አፍሪካ ኢንተለጀንስ» (Africa Intelligence) የተሰኘው የዜና ተቋም መሆኑን ቢጠቅሱም ተቋሙ ባወጣው ዘገባ ላይ እሳቸው ስለመታገታቸውም ሆነ የቁም እስረኛ ስለመሆናቸው የጠቀሰው ነገር እንደሌለ አብራርተዋል፣ ይህንን ኢትዮጵያ ቼክም አረጋግጧል።

ጄነራል ታደሰ ወረደ ለኢትዮጵያ ቼክ በሰጡት የቀጥታ ምላሽ "ታግተሃል አልያም የቁም እስረኛ ሆነሃል ለሚለው አሁን እያናገርከኝ ነው፤ እኔ አልታገትኩም፣ የቁም እስረኛም አልተደረግኩም፤ የAfrica Intelligence ያወጣው ዘገባ ላይም እኔ እንደታገትኩም አልያም የቁም እስረኛ እንደሆንኩ አልገለጸም" ብለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የታዋቂ ሰዎችን እና የፖለቲካ መሪዎችን ስም በመጠቀም ያልተናገሩትን እንደተናገሩ፣ ያልሆኑትን እንደሆኑ አድርጎ ማሰራጨት የተለመደ የሀሰተኛ መረጃ ስልት መሆኑ ይታወቃል።

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መሰል አጠራጣሪ እና የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸውን መረጃዎች ሲያነቡ መረጃው የወጣበትን ድረ-ገጽ ታማኝነት እንዲያረጋግጡ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራት እንዲቆጠቡ እንመክራለን።

ኢትዮጵያ ቼክ!
13,5000032
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

10 de set. de 2026, 18:09

#FactCheck፡ ዶ/ር አርከበ እቁባይ 'African Pulse' ለተባለ ሚዲያ ሰጡት ተብሎ በስፋት የተሰራጨው ጽሑፍ እና ቃለ-ምልልስ በሀሰት የተፈበረከ መሆኑ ተረጋገጠ

/ኢትዮጵያ ቼክ/ -- የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ የነበሩት ዶ/ር አርከበ እቁባይ “አፍሪካን ፐልስ” (African Pulse) ለተባለ ድረ-ገጽ ሰጡት የተባለው እና በማህበራዊ ሚዲያ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ያለው ፖለቲካዊ ትንታኔ እና አስተያየት ከእሳቸው ያልወጣ እና በሀሰት የተፈበረከ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል።

'African Pulse' በተሰኘው ድረ-ገጽ ላይ “ስትራቴጂካዊ ራስን ማጥፋት - ዶ/ር አርከበ እቁባይ የህወሓትን አመራር አምርረው ተቹ” በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሑፍ በዛሬው ዕለት ወጥቷል። ይህ የፈጠራ ጽሑፍ ዶ/ር አርከበን በማስመሰል በርካታ ከባድ የፖለቲካ ትችቶችን የቀድሞ ድርጅታቸው ህወሓት ላይ እንደሰነዘሩ አድርጎ ያቀርባል።

ጽሑፉን ይበልጥ እውነተኛ ለማስመሰልም ዶ/ር አርከበ ስለ ጦርነቱ አጀማመር፣ ስለ ፖለቲካዊ ስህተቶች እና ስለ ድርጅቱ መጻኢ ዕጣ ፈንታ ተናግረዋል ያላቸውን የሀሰት ሀሳቦች አካቷል። በዚህም የቀድሞ የትግል ጓዶቻቸው በስትራቴጂካዊ ድክመት እና በፖለቲካዊ እልህ ውስጥ ወድቀው የትግራይን ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ እንደጣሉ እና ጦርነቱ የተጀመረው በስሜት እንጂ በፖለቲካዊ ስሌት እና በበቂ ዝግጅት እንዳልነበረ በጽሑፉ ላይ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም አመራሩ የፌደራል መንግስቱን እና የሌሎች ኃይሎችን ጥምረት መገመት አለመቻሉን እንደተቹ፣ እንዲሁም የድርጅቱ አመራሮች ለለውጥ ዝግጁ እንዳልሆኑ እና አሁን ባለበት የዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ውድቀት ውስጥ ሆኖ ዳግም ስለ ጦርነት ማሰብ የድርጅቱን ህልውና ሙሉ በሙሉ የሚያጠፋ እንደሆነ አድርጎ አስነብቧል።

ይህ ዶ/ር አርከበ ሰጡት የተባለው የፈጠራ ጽሑፍ በዋናነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተከታዮች ባፈሩ የፌስቡክ ገጾች እና ግለሰቦች አማካኝነት በስፋት ተጋርቷል። ከእነዚህም መካከል ወደ 186 ሺህ የሚጠጉ ተከታዮች ያሉት ጄዚራ አፍሪካ የተባለ ገፅ ይህንኑ ሀሰተኛ መረጃ አጋርቷል።

በተመሳሳይ ከ91 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ቬነስ ዜና የተሰኘ የፌስቡክ ገፅ ጽሑፉን ያሰራጨ ሲሆን ከ33 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት Nebyat Alemu የተባለ ገፅም ይህንኑ መረጃ ተቀብሎ ለተከታዮቹ አጋርቷል።

እነዚህ ገጾች በአጠቃላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሏቸው በመሆኑ ይህ ሀሰተኛ መረጃ ብዙሃን ዘንድ እንዲደርስ እና በአንባቢዎች ዘንድ ከፍተኛ ብዥታ እንዲፈጥር ምክንያት ሆኗል።

ኢትዮጵያ ቼክ ይህ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ የጉዳዩን እውነተኛነት ለማረጋገጥ በቀጥታ ዶ/ር አርከበ እቁባይን ጠይቋል። በማጣራቱም ዶ/ር አርከበ 'African http://Pulse.org/' ለሚባለው ድረ-ገጽ ምንም ዓይነት ቃለ-ምልልስም ሆነ የጽሑፍ አስተያየት አለመስጠታቸውን አረጋግጠዋል።

ዶ/ር አርከበ ለኢትዮጵያ ቼክ በላኩት ቀጥተኛ ምላሽ ላይ ለ http://Pulse.org/ ቃለ-ምልልስ ሰጥተው እንደሆነ ተጠይቀው እንደነበር ገልጸው ምንም አይነት ቃለ-ምልልስ አለመስጠታቸውን አስረግጠው ተናግረዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ታዋቂ ሰዎችን እና የፖለቲካ ሰዎችን ስም በመጠቀም ያልተናገሩትን እንደተናገሩ አድርጎ ማሰራጨት የተለመደ የሀሰተኛ መረጃ ስልት ነው።

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንደዚህ አይነት አጠራጣሪ እና የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸውን መረጃዎች ሲያነቡ መረጃው የወጣበትን ድረ-ገጽ ታማኝነት እንዲያረጋግጡ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራት እንዲቆጠቡ እንመክራለን።

ኢትዮጵያ ቼክ!
13,4000023
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

04 de set. de 2026, 00:43

Photo
#FactCheck እነዚህ ምስሎች ሰሞኑን በምስራቅ ወለጋ ዞን በፋኖ ታጣቂዎች የወደመ የአርሶ አደር ቡና ማሳን አያሳዩም

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ በመንግስት ጸጥታ አካላት እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት መከሰቱ ሲዘገብ ሰንብቷል፣ በግጭቱ ምክንያትም በርካታ ነዋሪዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸው እንዲሁ።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዞኑ በፋኖ ታጣቂዎች የወደመን የአርሶ አደር ቡና ማሳ ያሳያሉ የተባሉ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ይገኛሉ።

እነዚህ ከትላንት ረቡዕ ነሀሴ 27፣ 2018 ጀምሮ እየተዘዋወሩ የሚገኙ ምስሎች በርካታ ተከታዮች ባላቸው የፌስቡክ አካውንቶች እና ገጾች ጭምር እየተጋሩ አና በርከት ያሉ መስተጋብሮችን እያስተናገዱ ይገኛሉ።

ይህን መረጃ ካጋሩ መካከል ‘Alex Taye’ የሚል ስምና ከ300 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት አካውንት አንዱ ሲሆን “ይህ የፋኖ ጽንፈኞች ያወደሙት የወለጋ አርሶ አደር ቡና ነው” ከሚል ፍሁፍ ጋር ምስሎቹን አጋርቷል።

በዚህ አካውንት የተጋራውን ልጥፍ ከ300 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን ከ700 በላይ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ከሰሞኑ የተነሱ እንዳልሆኑ አረጋግጧል።

ምስልን በምልሰት በመፈለግ (Reverese image search) ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ ከአመት በፊት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጋርተው የነበሩ እንደሆኑ ተመልክተናል።

በወቅቱ ምስሎቹን ያጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾችም ምስሎቹ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ውስጥ የተነሱ እንደሆኑ በመጥቀስ ነበር ምስሎቹን ያጋሩት፡ https://www.facebook.com/share/p/18N8Jj6eDj/?mibextid=wwXIfr

የቆዩና ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ
12,2000057
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

02 de set. de 2026, 15:57

Photo
#FactCheck የሳውዲው 'Al Riyadh' ጋዜጣ ያወጣው ነው በሚል ተቀናብሮ የተሰራጨው ፅሁፍ እና ምስል ሀሰተኛ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- የሳውዲው Al Riyadh ጋዜጣ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድን እግር ሲስሙ ያሳያል የሚል ዜና ሰርቷል በሚል አንድ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ ነው።

ምስሉንና አርእስተ ዜናውን ካጋሩት መሀል ፋሲል የኔአለም 'Fasil Yenealem' የተባለ በፌስቡክ ላይ ከ269 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ግለሰብ ይገኛል። በተጨማሪም ኤክስ ላይ ወደ 23ሺህ የሚጠጋ ተከታዮች ያሉት @Joe የሚባል የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ መረጃውን አጋርቷል።

ይሁንና ኢትዮጽያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ምስሉም፣ ዜናውም Al Riyadh ጋዜጣ ላይ እንዳልወጣ አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ ቼክ Google Lens የተባለ የድህረ ገፅ መረጃ ማጣሪያ በመጠቀም ባረገው ማጣረት የ Al Riyadh አርእስተ ዜና ርእስ የሚጠቀማቸው የአረብኛ ቃላቶች ልዩ ደማቅ ጥቁር የአረብኛ ፅሁፍ ጥበብ እንደሚጠቀም እና አረንጓዴ ቀለም ያለው የቴምር ዛፍ መለያው እንደሆነ አረጋግጧል: https://www.alriyadh.com/

በተጨማሪም Al Riyadh ጋዜጣ አመተ ምህረቱን የሚያስገባው ከአርእስቱ በታች በግልፅ በአውሮፓውያን አመተ ምህረት አቆጣጠር ተጠቅሞ በአግድም መልክ እንደሚያስቀምጥ ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል።

በተቃራኒው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድን ያሳያል የተባለው ምስል የAl Riyadh ጋዜጣ መለያ የሆነውን አረንጓዴ የቴምር ዛፍ ሳይሆን የተባበሩት አረብ ኤምሬቴስ መለያ የሆነውን
የወርቅ ቀለም ያለው መለያ ምስል በጉልህ ይታያል።

በተጨማሪም የAl Riyadh ጋዜጣ ሌላ መለያው የሆነውን አመተ ምህረት አገባብ፣ ፊደልና የአውሮፓውያን አመት አቆጣጠር አያሳይም።

የሰው-ሰራሽ አስተውሎት በመጠቀም የሚፈበረኩ እና ከአውድ ወጭ የሚጋሩ ምስል እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ
9,3200041
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

27 de ago. de 2026, 06:26

Photo
#FactCheck ሰሞኑን በሻምቡ ከተማ ‘ለመንግስት እጃቸውን የሰጡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላትን ያሳያሉ’ በሚል እየተሰራጩ ያሉ ምስሎች የቆዩ ናቸው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ከሰሞኑ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ ለመንግስት እጃቸውን የሰጡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላትን ያሳያሉ በሚል በርከት ያሉ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ይህን መረጃ በሰበር ዜና መልኩ ካሰራጩ የፌስቡክ ገጾች መካከል ‘Ethiopian Green Legacy’ የሚል ስም እና ከ27 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ገጽ ይገኝበታል።

ገጹ “የጠላት ካምፕ መፍረሱን ቀጥሏል። በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ የኦነግ ሼኔ (WBO) አባላት በጃል ያዴሳ የሚመሩት ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ በሰላማዊ መንገድ ለወታደራዊ መንግስት እጃቸውን ሰጥተዋል” የሚል ጽሁፍም ከምስሎቹ ጋር አጋርቷል።

በተመሳሳይ መልኩ ሌሎች በርከት ያሉ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶችም ይህን መረጃ ያጋሩ ሲሆን አንዳንዶቹ እጃቸውን የሰጡ የታጣቂ ቡድኑ አባላት ቁጥር 200 እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ ምስሎቹን በምልሰት በመፈለግ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ሰሞኑን የተነሱ እንዳልሆኑ አረጋግጧል።

በዚሁ መሰረት ምስሎቹ የዛሬ ዓመት አከባቢ (እኤአ መስከረም 29፣ 2025) በማህበራዊ ትስስር ገጾች የተጋሩ ሲሆኑ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጃርደጃ ጃርቴ ወረዳ “በሰላም የገቡ” የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላትን እንደሚያሳዩ ተዘግቦ ነበር።

በወቅቱ በጉዳዩ ላይ ዘገባ ከሰሩ መገናኛ ብዙሃን መካከል EBC አንዱ ሲሆን 73 የታጣቂ ቡድኑ አባላት “እጅ ሰጥተዋል” ሲል ዘግቦ ነበር፡ https://www.facebook.com/share/1Hiz34qqM7/?mibextid=wwXIfr

የቆዩና ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ
9,9100029
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

26 de ago. de 2026, 12:01

Photo
#EthiopiaCheck "በወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለቀረበ ጥያቄ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠ መልስ እንደሆነ በመጥቀስ እየተጋራ የሚገኝ ደብዳቤ ሀሰተኛ ነው" —አቶ አገኘሁ ተሻገር

/ኢትዮጵያ ቼክ/- የፌዴሬሽን ምክር ቤት በወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠዉን መልስ የያዘ እንደሆነ የተገለጸ ደብዳቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ይገኛል።

ይህ ደብዳቤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ስም የሰፈረበት ሲሆን ግንቦት 12፣ 2018 ወጪ የተደረገ እንደሆነም በደብዳቤዉ ተጠቅሷል።

የደብዳቤዉ ዋና ይዘት ደግሞ ‘በወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የቀረበዉ የማንነትና ራስ ገዝነት አስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ ተቀባይነት የሌለዉ እና ሙሉ በሙሉ ውድቅ የተደረገ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጥብቅ ያሳውቃል” የሚል ነው።

ይህን ደብዳቤ ካጋሩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘ደጀን ግራካሕሱ ሚዲያ ኔትዎርክ’ እና ‘ቤት ፅሕፈት ህወሓት ከተማ ኮረም’ የሚሉ የፌስቡክ ገጾች ይገኙበታል።

ይሁን እንጂ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በተረጋገጠ የፌስቡክ ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ ደብዳቤው ሀሰተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

አፈ ጉባዔው “የፌዴሬሽን ምክር ቤት በወልቃይት ጉዳይ ያወጣው መግለጫ በሚል በማኀበራዊ ሚዲያ የሚዟዟረው ደብዳቤ ፍጹም ሐሰትና በቅንብር ፎቶ የተሰራ መሆኑን እየገለፅኩ ይህን የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩት እነማን እንደሆኑ አጣርተን ለህግ የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን” ብለዋል።

አፈ ጉባዔው በፌስቡክ ገጻቸው ያጋሩት መረጃ በዚህ ማስፈንጠሪያ ይገኛል፡ https://www.facebook.com/share/p/14h6RpnEwNE/?mibextid=wwXIfr

ኢትዮጵያ ቼክ
12,8000025
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

26 de ago. de 2026, 12:01

#FakeAccountAlert በሸዊት ውዳሴ ስም የተከፈቱ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፆች ማሳሰቢያ

/ኢትዮጵያ ቼክ/- በመምህር እና የፖለቲካ ተንታኝ ሸዊት ውዳሴ ስም እና ምስል የተከፈቱ በርካታ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጾች መኖራቸውን ደርሰንበታል። እነዚህ ገጾች የግለሰቡን ማንነት በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን እያጋሩ የሚገኙ ሲሆን አንዳንዶቹም ህዝብን የሚያሳስቱ ይዘቶች እንዳሏቸው ተመልክተናል።

መምህር ሸዊት በሀገራዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው ትንታኔዎች እና በትምህርት ዘርፍ ባለው ተሳትፎ የሚታወቅ ግለሰብ ነው።
ሸዊት ውዳሴ ለኢትዮጵያ ቼክ እንዳረጋገጠው የእሱ ብቸኛው እና ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/share/18iYLyc8Yu/ ነው። ይህ ገጽ በአሁኑ ወቅት ከ72 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን ግለሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችን እና የራሱን ሐሳቦች የሚያጋራበት ዋነኛ መድረክ ነው።

ከዚህ ትክክለኛ ገጽ በተጨማሪ ከ5 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት እንዲሁም ሌላ ከ2 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ተመሳሳይ ስም እና ምስል የሚጠቀሙ ገጾች ተለይተዋል። እነዚህ ገጾች የሸዊት ውዳሴ እንዳልሆኑ ተረጋግጧል።

የታዋቂ ግለሰቦችን፣ የመንግስት ባለስልጣናትን ወይም የተቋማትን ስም እና አርማ በመጠቀም የሚከፈቱ ገጾች አሳሳች መረጃዎችን በማሰራጨት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጫና ሲፈጥሩ ይታያል።
ስለሆነም ማንኛውንም መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ከመጋራታችን ወይም ከመቀበላችን በፊት የገጹን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ተገቢ ነው።

ሀሰተኛ እና ተመሳስለው የሚከፈቱ አካውንቶችን፣ ገጾችን እና ቻናሎችን በቀላሉ ለመለየት የሚረዱን ጠቋሚ ምልክቶችን ለማወቅ ኢትዮጵያ ቼክ ያዘጋጀውን አጭር እና አስተማሪ ቪዲዮ በዚህ ሊንክ መመልከት ትችላላችሁ፦


ኢትዮጵያ ቼክ
12,1000019
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

25 de ago. de 2026, 04:37

Photo
#FactCheck አልጀዚራ ስለ ምክክር ጠቅላላ ጉባኤ ሰራው በሚል በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ተቀናብሮ የተሰራጨው ሀሰተኛ ዘገባ

/ኢትዮጵያ ቼክ/- አልጀዚራ የዜና ወኪል ስለ ኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤ ሰራው የተባለ ሀሰተኛ ዘገባ በጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃዎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተጋራ ይገኛል።

ይህ የተሰራጨው የጽሁፍ እና ቪዲዮ መረጃ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያከናወነችው የጠቅላላ ምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያ የውስጥ አለመግባባቶችን በጠመንጃ ግጭት ሳይሆን በውስጣዊ ውይይት ማስተናገድ እንደምትችል ያሳያል በሚል ተዘግቧል ይላል።

ይህ የተሰራጨው የጽሁፍና የቪዲዮ መረጃ የምክክር ጠቅላላው ጉባኤው ውጤቶች ኢትዮጵያን ለሰላምና አካታች ልማት አቅጣጫ ሊመራት ይችላል ይላል።

ይህን የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ በስፋት ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ''Hermen Gashaw'' የተባለ ወደ 21 ሺህ ተከታዮች ያሉበት ገፅ ይገኛል። በገጹ የተጋራዉን ይኸንን የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ ወደ 208 የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ለሌሎች ያጋሩት ሲሆን 51 የሚሆኑ አስተያየቶች ሰጥተውበታል።

ይህንን ጉዳይ ተከትሎ ኢትዮጵያ ቼክ መረጃውን ለማረጋገጥ ባደረገው ጥልቅ ምርመራ ቪዲዮው እውነተኛ እንዳልሆነ አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ ቼክ የጉግል ምርት የሆነዉን ‘ሲንዝ አይዲ ዲቴክተር’ (SynthID Detector) የተባለውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መተግበሪያ በመጠቀም በቪዲዮው ላይ ባደረገዉ ማጣራት የተሰራጨው ፅሁፍ ትክክለኛ የዜና አቅራቢም፣ ዘገባም እንደማያሳይ ደርሶበታል።

በዚሁ የምርመራ ውጤት መሰረት በቪዲዮው ውስጥ የሚታየው ምስልም ሆነ የሚሰማው ድምጽ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ የተቀነባበረ የፈጠራ ውጤት መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።

በቪዲዮው ላይ የ'ዜና አቅራቢው' ቪዲዮ የሚታየው የከንፈር እንቅስቃሴ፣ የፊት ገጽታ እና የድምጽ ቅንብር አንድን ትክክለኛ ሰው አስመስሎ በኮምፒውተር ፕሮግራም የተሰራ እንጂ በገሃዱ ዓለም የተፈጠረን ዘገባ ክስተትን የሚያንጸባርቅ አይደለም።

በተጨማሪ ቪዲዮው Hermen Gashaw በተባለ የፌስቡክ ገፅ የተጫነ እንጂ በተረጋገጡ አልጀዚራ እንግሊዘኛ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ የሌለ መሆኑን አረጋግጠናል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚፈበረኩ መሰል የዲፕፌክ (Deepfake) ቪዲዮዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ በጣም እየተበራከቱ እና በርካታ ሰዎችን ለተሳሳተ መረጃ እያጋለጡ ይገኛሉ።

አሳሳች መረጃ አሰራጪ አካላት እነዚህን እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመጠቀም እውነተኛ የሚመስሉ ነገር ግን ፈጽሞ ያልተፈጠሩ ክስተቶችን በመፍጠር ህብረተሰቡን በማሳሳት ላይ ይገኛሉ።

ይህ አይነቱ ቴክኖሎጂ የፖለቲካ ውዥንብር ለመፍጠር፣ የተሳሳቱ ትርክቶችን ለማራመድ፣ እና የሰዎችን ስነልቦና ለመጉዳት ሆን ተብሎ የሚሰራጭ አደገኛ የሀሰተኛ መረጃ (Disinformation) መሳሪያ ሆኗል።

በተለይም አሁን ባለንበት ወቅት የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ግለሰቦች ያልተናገሩትን እንደተናገሩ አድርጎ በማቅረብ ህብረተሰቡ የተዛባ መረጃን አምኖ እንዲቀበል ማድረግ የተለመደ የማጭበርበር ስልት ሆኖ ብቅ ብሏል።

ሰዎች እውነተኛ ቪዲዮ እየተመለከቱ እንደሆነ በማሰብ እንዲታለሉ እና የተዛባ መረጃን ለሌሎች በማጋራት በማህበረሰቡ ውስጥ አለመተማመንን መፍጠር የዚህ አይነቱ ተግባር ዋና አላማ ነው።

ስለሆነም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ይህንን እያደገ የመጣውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት አደጋ በሚገባ ተገንዝበው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንመክራለን።

ማንኛውም አጠራጣሪ እና ተአማኒ ባልሆኑ የመረጃ ምንጮች ወይም ግለሰቦች የሚጋሩ የምስል እና የቪዲዮ መረጃዎችን ልክ እንዳዩት ከማመናችን እና መልሰን ለሌሎች ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት ማድረግ አለብን።

ቪዲዮዎች ያልተለመደ የዓይን ብልጭታ፣ ከድምጽ ጋር የማይሄድ የከንፈር እንቅስቃሴ ወይም ኢተፈጥሮአዊ የሆነ የቆዳ ገጽታ ካላቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ በጥሞና መመርመር ያስፈልጋል።

ኢትዮጵያ ቼክ!
9,9900038
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

20 de ago. de 2026, 03:46

Photo
#FakeAccountAlert በመአረግ አማረ ስም ስለተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ የወጣ ማሳሰቢያ

/ኢትዮጵያ ቼክ- በማህበራዊ ሚዲያ ተሳትፎው በሚታወቀው በመአረግ አማረ ስም እና ምስል የተከፈተ አንድ የፌስቡክ ገፅ የተለያዩ መረጃዎችን እያጋራ መሆኑን ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ላይ ባደረገው ማጣራት ከ15 ሺህ በላይ ተከታታዮች ያሉት ገፁ ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል። መአረግ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፁ ከ152 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ይህ አካውንት ብቻ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ ያረጋገጠ ሲሆን ገፁንም በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል፡ https://www.facebook.com/share/1D91gjpkCL/

በታዋቂ ግለሰቦች እና ተቋማት ስም የሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች በህብረተሰቡ ላይ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ። እነዚህ አካውንቶች የሰዎችን አሳሳች መረጃ የማሰራጨት፣ የማጭበርበር እና የስም የማጥፋት ድርጊቶችን በቀላሉ ለመፈፀም ስለሚጠቀሙባቸው ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል።

ብዙ ጊዜ እነዚህ ገፆች የህዝብን ትኩረት እና እምነት ለማግኘት የታዋቂ ሰዎችን ማንነት በመስረቅ ያልተረጋገጡ የፖለቲካ እና የብሄር ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎችን ያሰራጫሉ። በተጨማሪም ከባድ የፋይናንስ ማጭበርበሮችን በማካሄድ የውሸት የእርዳታ ጥሪዎችን በማቅረብ እና ሰዎችን የገንዘብ ወጥመድ ውስጥ በመክተት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ያደርሳሉ።

ይህ ድርጊት የእውነተኛ አካውንት ባለቤቶችን መልካም ስምና ዝና ከማበላሸቱ ባሻገር ተከታዮች እውነተኛውን ከሀሰተኛው ለይተው ለማወቅ እንዲቸገሩ በማድረግ በማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎች ላይ ያለውን እምነት ያጠፋል። ስለሆነም የታዋቂ ግለሰቦችን እና ተቋማትን ስም እንዲሁም ምስል በመጠቀም የሚከፈቱ ሀሰተኛ ገፆች ለእንደነዚህ አይነት አሳሳች አደጋዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ሁልጊዜ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል።

ተጠቃሚዎች ማንኛውንም መረጃ ከማመናቸው እና ከማሰራጨታቸው በፊት የገፁን የሰማያዊ ምልክት (Verification Badge)፣ የተከፈተበትን ጊዜ፣ የፖስቶች ይዘት እና የተከታዮች ብዛት በጥንቃቄ መመርመር አለባቸው።

በተጨማሪም ሀሰተኛ እና ተመሳስለው የሚከፈቱ አካውንቶችን፣ ገፆችን እና ቻናሎችን ለመለየት የሚረዱ ጠቋሚ ምልክቶችን ለመመልከት በኢትዮጵያ ቼክ የተዘጋጀውን ይህን አጭር ቪዲዮ መመልከት ትችላላችሁ፡ https://t.me/ethiopiacheck/1344

ኢትዮጵያ ቼክ!
10,4000017
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

14 de ago. de 2026, 00:31

#FactCheck በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ ወደቀ ስለተባለው ጄት እየተሰራጩ ያሉ ትክክለኛ እና አሳሳች መረጃዎች

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ ጎራ ለመን ቀበሌ ወደቀ ስለተባለ የጦር ጄት የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ቆይተዋል።

የጄቱ ስብርባሪ አካል ብቻውን እንዲሁም የታጠቁ ሰዎች በስብርባሪው ላይ ቆመው የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዮዎችም እየተጋሩ ይገኛሉ።

አንዳንዶች የጦር ጄቱ በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) ታጣቂዎች ተመቶ መውደቁን በመጥቀስ ምስሎቹን ያጋሩ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ምስሎቹ እና ቪዲዮዎቹ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ እንደሆኑ የጻፉም አሉ።

በተጨማሪም ምስሉ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጄትን እንደማያሳይ በመጥቀስ መረጃው ሀሰተኛ እንደሆነ የጻፉም አሉ። ከነዚህ መካከልም ‘Demeke Negassa Kube’ የሚል ስም እና ከ500 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል።

ገጹ “የወያኔ ቋሚ ተላላኪዎች እያሰራጩ ያለው ዜና በፍጹም ውሸት ነው ።ጀግናው አየር ኃይላችን እንደዚህ ጨጨባ (ስብርባሪ) ጄት የለውም።ይህንን ስብርባሪ ለራሣችሁ አውሉት።በመንደር ሽፍታ ቀርቶ በሌላም በቀላሉ የሚመታ ጄት የለውም” ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ስለሚገኙ ምስሎች እና ቪዲዮ ጽፏል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ እና ቪዲዮ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹም ሆነ ቪዲዮ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዲሁም በቅንብር የተሰሩ እንዳልሆኑ አረጋግጧል። በተጨማሪም ምስሎቹ እና ቪዲዮ ከዚህ በፊት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጋርተው እንደማያውቁም ተመልክቷል።

የጦር ጄቱም ኤሮ L-39 አልባትሮስ (Aero L-39 Albatros) በመባል የሚታወቅ ሲሆን የቼክ ሪፐብሊክ ስሪት ነው። ይህ ጄት በስፋት ለስልጠና አገልግሎት የሚውል ሲሆን ለአየር ላይ ውጊያ፤ የመሬት ላይ ኢላማዎችን ለማጥቃት እንዲሁም ለስለላ አገልግሎትም መዋል ይችላል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይልም ይህን ጄት ለስልጠና እንደሚጠቀም ከዚህ በፊት የተጠቀሰ ሲሆን ጄቱ የዛሬ ስድስት ወር ገደማ በተከበረው የአየር ኃይል 90ኛ አመት ክብረ በዓል ላይ ትርዒት ካሳዩ ጄቶች መካከል አንዱ ነበር።

በእለቱም የተወሰኑ የአየር ኃይሉ L-39 አልባትሮስ ጄቶች ትርዒት ያሳዩ ሲሆን የጄቶቹ ትርዒት EBC በእለቱ ባሰራጨው ቀጥታ ስርጭት ቪዲዮ 1፡03፡00 ጀምሮ ይታያል፡ https://www.youtube.com/live/Ib4t9boBZxg?si=uqGOCD92DKVMGo30

በዚህ የEBC ቪዲዮ ውስጥ 5፡30 ደቂቃ ላይ ደግሞ ጄቶቹ በረድፍ ቆመው ይታያሉ፡ https://youtu.be/969VaWBL9EY?si=cJFbiSKI6zBvBFBg

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ቼክ የተከሰከሰውን ጄት ስብርባሪና በክብረ በዓሉ ላይ ትርዒት ያሳዩ L-39 አልባትሮስ ጄቶችን በማነጻጸርም ተመልክቷል። በዚሁ መሰረት የተከሰከሰው እና በትርዒቱ ላይ የተሳተፉት ጄቶች ተመሳሳይ የቀለም ስብጥር እንዳላቸው አረጋግጧል።

ከነዚህ መካከልም ጄቶቹ ሆድ ስር የሚገኘው ሰማያዊ ቀለም፤ ክንፎቹ ጫፍ ላይ ያሉት ቀይ እና ቢጫ ቀለማት እንዲሁም የጄቶቹ ጅራት ጫፍ ላይ የሚገኘው ቢጫ ቀለም ቅብ ይገኙበታል።

ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች እንዲሁም በጄቱ ስብርባሪ ምስል ላይ የሚታየውና ጄቱ እንደወደቀ የተገለጸበት ስፍራ መሬት አቀማመጥ መመሳሰል ጄቱ ከጥርጣሬ በላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል መሆኑን የሚያመላክቱ ናቸው።

ይሁን እንጂ ጄቱ ተመቶ ወይስ በቴክኒክ ችግር ምክንያት ነው የወደቀው የሚለው ጥያቄ በማስረጃ ያልተመለሰ ሲሆን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስትም ስለ ጉዳዩ በግልጽ ያሉት ነገር የለም።

ኢትዮጵያ ቼክ
Video Thumbnail
12,0000057
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

03 de ago. de 2026, 21:45

Photo
#FactCheck በሸረሪና የተማረኩ 'የህወሓት ኃይሎች እና ጦር መሳሪያዎች' በሚል እየተሰራጩ የሚገኙት ምስሎች የቆዩ ናቸው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ሰሞኑን በፌደራል ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ሸረሪና አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል። ይህን ግጭት መነሻ በማድረግም በፌደራል ሠራዊት የተማረኩ ‘የትግራይ ኃይሎች’ አባላት እና ጦር መሳሪያዎችን ያሳያሉ በሚል በርከት ያሉ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ይገኛሉ።

እነዚህን ምስሎች ካጋሩ የፌስቡክ ገጾች መካከልም ‘አውደ ሀገር’ የሚል ስም እና ከ107 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል።

በዚህ ገጽ የተጋራውን የምስል እና ጽሁፍ መረጃ 19 የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ሲያጋሩት በርከት ያሉ አስተያየቶችም ተሰጥቶበታል።

በተጨማሪም ‘Mimi Jarso’ የሚል ስም እና ከ170 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ተመሳሳይ መረጃን አጋርቷል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ሰሞኑን ሸረሪና አከባቢ በተከሰተው ግጭት የተማረኩ የትግራይ ኃይሎች አባላትን እና ጦር መሳሪያዎችን እንደማያሳዩ አረጋግጧል።

ምስልን በምልሰት መፈለጊያ ድረ-ገጾችን በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ ከወራት በፊት በአማራ ክልል ውስጥ የተነሱ መሆናቸውን አረጋግጠናል።

በዚሁ መሰረት ምስሎቹ እኤአ ታህሳስ 15፣ 2025 “በምስራቅ ደምቢያ እና በቆላድባ ከተማ አካባቢ ታጥቀዉ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂ ሃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለዉ ገቡ” በሚል ርዕስ በአማራ ክልል ፕሬዘዳንት ጽ/ቤት የተረጋገጠ የፌስቡክ ገጽ የተጋሩ ናቸው፡ https://www.facebook.com/share/14hssp5abfn/?mibextid=wwXIfr

ስለዚህም ምስሎቹ ከአውድ ውጭ የተጋሩ እና አሳሳች መሆናቸውን አረጋግጠናል።

በተለይ በግጭት ወቅት ከአውድ ውጭ እና አሳሳች በሆነ መልኩ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታን እንዲሁም ከማመናችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ
14,0000038
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

30 de jul. de 2026, 20:23

Photo
#FactCheck የአሜሪካው ፕሬዚዳንት አማካሪ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ላይ አቋም ወስደዋል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት የመካከለኛው ምሥራቅ፣ የአረብ አገራት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ አገራቸው በፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ላይ የጠነከረ እርምጃ ትወስዳለች ብለው ተናግረዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ መሠረት የሌለውና ሐሰተኛ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት አረጋግጧል።

ከ193 ሺህ በላይ ተከተዮች ያሉት «ጌትነት አልማው ጥሩነህ» የተባለው የፌስቡክ ገፅ ይህ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግሥት ኃላፊ «ፀረ-ኢትዮጵያ አደረጃጀቶች ላይ አሜሪካ እርምጃ እንደምትወስድ ተናግረዋል» በሚል የተሳሳተ መረጃ አጋርቷል።

ይህ የፌስቡክ ገፅ ያሰራጨው መረጃ አሳሳች መሆኑ ሳይታወቅ በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መልሶ እንዲሰራጭ እና የህዝብን ትኩረት እንዲስብ ተደርጓል።

ኢትዮጵያ ቼክ ያደረገው ጥልቅ ማጣራት እንደሚያሳየው ማሳድ ቡሎስ በይፋዊ የኤክስ (X) ገፃቸው ላይ ባጋሩት መግለጫ አሜሪካ የተባለውን ዓይነት እርምጃ ትወስዳለች የሚል ንግግር አላደረጉም።

ማሳድ ቡሎስ በሰጡት ቀጥተኛ ማብራሪያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያተኮረው የአሜሪካ ዲፕሎማሲ «ፀረ-ኢትዮጵያ ጥምረትን ለማጠናከር እየሞከረ ነው» ተብለው በየቦታው የቀረቡት ዘገባዎች ሙሉ በሙሉ ውሸት አሳሳችና ህዝብን የሚያሳስቱ መሆናቸውን በግልጽ አስረድተዋል።
በተጨማሪም አሜሪካ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከሌሎች የአፍሪካ ቀንድና የሰፊው ቀይ ባሕር ቀጣና አገሮች ጋር በጋራ የልማት፣ የሰላምና የደህንነት ጉዳዮች ላይ በቅርበትና በትብብር እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል።

የአሜሪካ ዲፕሎማሲ ዋነኛ አላማ ተፎካካሪ ጎራዎችን መፍጠር ወይም የቀጣናውን ቅራኔዎች ማጥበቅ ሳይሆን ግጭቶችን በማስቀረት ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ እንደሆነ አብራርተዋል።

በሌላ በኩል መቀመጫውን ፓሪስ ያደረገው «አፍሪካ ሪፖርት» (The Africa Report) የተባለው የዜና ምንጭ በቅርቡ ባወጣው የትንታኔ ዘገባ የአሜሪካ ዲፕሎማሲ በግብፅ-ሶማሊያ-ኤርትራ ምህዋር በኩል እና በኢትዮጵያ-ሶማሊላንድ-እስራኤል ምህዋር በኩል ባለው አህጉራዊ ፖለቲካዊ ውጥረት መካከል ሊወጠር እንደሚችል አመላክቷል።

ይህ የትንታኔ ዘገባ የቀጣናውን ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚያስረዳ እንጂ ማሳድ ቡሎስ እርምጃ እወስዳለሁ ብለው የተናገሩትን የሚያረጋግጥ አይደለም።

በፖለቲከኞች፣ በዲፕሎማቶች እና በታዋቂ ሰዎች ስም ያልተናገሩትን ንግግር እንደተናገሩ አስመስሎ ማሰራጨት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰፊ ተቀባይነት ለማግኘት የሚደረግ የተለመደ የሐሰተኛ መረጃ (Disinformation) ስልት ነው።

ስለሆነም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንደዚህ ያሉ አጠራጣሪና የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸውን መረጃዎች በሚያነቡበት ጊዜ፣ መረጃው የወጣበትን ድረ-ገፅ ታማኝነትና ትክክለኛነት አስቀድመው እንዲያረጋግጡ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራት እንዲቆጠቡ ይመከራል።

ኢትዮጵያ ቼክ!
14,0000016
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

29 de jul. de 2026, 02:45

Photo
#FactCheck በአሜሪካ የአማራ ማህበር ስም የተሰራጨው መግለጫ ሐሰተኛ መሆኑን ተቋሙ አስታወቀ

/ኢትዮጵያ ቼክ/- በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ከሰሞኑ በስፋት ሲሰራጭ የነበረውንና በአሜሪካ አማራ ማህበርን (AAA) የደብዳቤ ቅርፅ እና አርማ የያዘውን መግለጫ አስመልክቶ ማህበሩ በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ አጋርቷል።

በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚል ቀን የተጻፈበትና የአሜሪካ አማራ ማህበርን ህጋዊ አርማ የያዘ የአቋም መግለጫ በሰፊው ሲያሰራጩ ቆይተዋል። ይህ በስፋት የተሰራጨው መግለጫ ስለ አማራ ሕዝብ የትግል አቅጣጫና የወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታዎች ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ሀሳቦችን ያካተተ ነው ተብሎ ነበር።

ነገር ግን መረጃው በስፋት መሰራጨቱን ተከትሎ የአሜሪካ አማራ ማህበር በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ይፋዊ ማብራሪያና ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ማህበሩ በላከው መግለጫ መሰረት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለው ሰነድ በማህበሩ ያልተዘጋጀና ሙሉ በሙሉ የተፈበረከ ሐሰተኛ መረጃ መሆኑን ጠቁሟል።

ድርጅቱ ምስሉ ላይ ትልቅ የቀይ “FAKE” (ሐሰተኛ) የሚል ማህተም በማስቀመጥ ደጋፊዎቹ እና የሕዝብ አባላት በተሳሳተ መረጃ እንዳይደናገሩ አሳስቧል።

እንደ ማህበሩ ገለጻ ከሆነ ይህ የተቀናበረ ሐሰተኛ መግለጫ የመነጨውና መጀመሪያ የተሰራጨው ከመንግስት ጋር ግንኙነት ካላቸው አካላት ወይም "የገዥው አካል አፈቀላጤዎች ገጽ ላይ ነው" ብሏል።

በተጨማሪም በአሜሪካ የአማራ ማህበር ማንኛውም አይነት ይፋዊ መግለጫ፣ መረጃና አቋም የሚለቀቀው በድርጅቱ ህጋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች እና በኦፊሴላዊ ድረ-ገጹ ላይ ብቻ መሆኑን አብራርቷል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ የነበረውና የማህበሩ አርማ ያለበት መግለጫ ሙሉ በሙሉ የተፈበረከ መሆኑን ድርጅቱ በመግለፁ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡና መረጃዎችን ከተቋማቱ ህጋዊ ገጾች ብቻ እንዲከታተሉ ይመከራል።

ኢትዮጵያ ቼክ!
12,2000031
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

22 de jul. de 2026, 17:47

#FactCheck የኢትዮጵያ የስንዴ ምርት መረጃ እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ሪፖርቶች ንጽጽር

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ሰሉልታ አካባቢ የሚገኝ የስንዴ ማሳን በጎበኙበት ወቅት ኢትዮጵያ በዘንድሮው የምርት ዘመን ያስመዘገበችውን ውጤት በተመለከተ የሰጡት መግለጫ አነጋጋሪ ሆኗል።

በመግለጫቸውም ሀገሪቱ በዚህ በጀት ዓመት ከ330 ሚሊዮን ኩንታል (33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን) በላይ ስንዴ ማምረት መቻሏንና ይህም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚዋ ስንዴ አምራች ሀገር እንደሚያደርጋት ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ይህ በመንግስት በኩል የቀረበው አሀዝ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የግብርና እና የኢኮኖሚ መረጃ ተንታኝ ተቋማት ሪፖርቶች ጋር ሲነጻጸር እጅግ ከፍተኛ ልዩነት ይታይበታል።

የአሜሪካ የእርሻ ዲፓርትመንት (USDA) የውጭ እርሻ አገልግሎት (FAS) እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2024 እና በሜይ 2025 ባወጣቸው ተከታታይ ሪፖርቶች መሰረት የኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ምርት በ6.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን አካባቢ እንደሚገኝ ተገምቷል።

ምንም እንኳን ተቋሙ በኢትዮጵያ የመስኖ ስንዴ ልማት እና የክላስተር ግብርና ምርታማነትን እየጨመረ መሆኑን ቢገልጽም የተመዘገበው ጭማሪ በመንግስት ከተጠቀሰው 33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ጋር ሲነጻጸር በአምስት እጥፍ ገደማ ያነሰ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ የሳተላይት ምስሎችን እና የመሬት ላይ መረጃዎችን መሰረት ያደረጉ የUSDA ትንታኔዎች እንደሚጠቁሙት በኢትዮጵያ ለእርሻ የዋለው መሬት ስፋት እና የተገኘው ምርት መጠን መንግስት እንደሚለው "በአራት እጥፍ" አድጓል የሚለውን መረጃ አያረጋግጡም።

በተመሳሳይ እንደ FAO (የዓለም የምግብ እና ግብርና ድርጅት) ያሉ ተቋማት መረጃዎችም የኢትዮጵያን ምርት ከ7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ አያደርሱትም።

ኢትዮጵያ "ግብፅን በሶስት እጥፍ በመብለጥ ከአፍሪካ አንደኛ ሆናለች" የሚለውን መግለጫ በተመለከተ ዓለም አቀፍ የንግድ እና የግብርና መረጃዎች የተለየ ምስል ያሳያሉ።

የUSDA እና የኢንዴክስ ቦክስ (IndexBox) የ2024/25 ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ግብፅ በ9.2 እስከ 9.7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዓመታዊ ምርት አሁንም ከአፍሪካ ቀዳሚነቱን እንደያዘች ነው። ኢትዮጵያ በ6.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምርቷ ከግብፅ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

መንግስት ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ ጀምራለች ቢልም የዓለም አቀፍ የንግድ መረጃዎች (እንደ OEC ያሉ) ግን ኢትዮጵያ አሁንም ከፍተኛ መጠን ያለው ስንዴ ከውጭ እንደምታስገባ ያሳያሉ።

ለምሳሌ እ.ኤ.አ በ2024 እና 2025 መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያ ከኬንያ፣ ሮማኒያ እና ቱርክ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያወጣ ስንዴ ገዝታለች። በተቃራኒው ወደ ውጭ የተላከው የምርት መጠን እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ተመዝግቧል።

እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና በዓለም ባንክ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፤ በሀገር ውስጥ ገበያ ላይ የታየው የስንዴ ዋጋ ንረት (በአንድ ዓመት ውስጥ የ28% ጭማሪ) እና በምግብ እርዳታ ላይ የሚገኙ ዜጎች ቁጥር አለመቀነስ፣ ሀገሪቱ "ትርፍ ምርት አምርታለች" ከሚለው መግለጫ ጋር የሚጋጩ ተጨባጭ እውነታዎች ናቸው።

በአጠቃላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው የ33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የምርት ሪፖርት ከገለልተኛ ዓለም አቀፍ ተቋማት ግምቶች (ከ5.5 - 7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን) ጋር እጅግ ሰፊ ልዩነት ያለው ሲሆን የሀገሪቱ የገቢ ንግድ መረጃ እና የገበያ ዋጋም የቀረበውን "ትርፍ ምርት" አያረጋግጡም።

ኢትዮጵያ ቼክ
12,70000101
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

21 de jul. de 2026, 00:01

Photo
#FactCheck በጮቄ ሰንሰላታማ ተራራ የተማረኩ ጦር መሳሪያዎች በሚል በሰበር መልኩ እየተጋሩ ያሉ ምስሎች በሰው-ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ ናቸው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ‘በጮቄ ሰንሰላታማ ተራራ የተማረኩ የጦር መሳሪያዎችን ያሳያሉ’ የተባሉ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ይገኛሉ።

በምስሎቹ በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል መሀመድ ተሰማ ከሌሎች ሁለት ግለሰቦች ጋር ቆመው ከፊታቸው ደግሞ በርከት ያሉ የጦር መሳሪያዎች ተደርድረው ይታያሉ።

ምስሎቹን “ሰበር መረጃ” በማለት ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ’ የሚል ስም ያለው የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል።

ይህ ገጽ “ከጮቄ ሰንሰለታማ ተራራ ዛሬ ብቻ 75 ክላሽ 1ዲሽቃ 2 ብሬን ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተረክቧል” የሚል ጽሁፍም ከምስሎቹ ጋር አጋርቷል።

በተመሳሳይ መልኩ 'ሀገሬ ሚዲያ’ የሚል ስም ያለው የፌስቡክ ገጽም ምስሎቹን እና የጽሁፍ መረጃውን ያጋራ ሲሆን 35 የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በገጹ የተጋራዉን መረጃ መልሰው አጋርተዉታል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ የጉግል ምርት የሆነውና በሰው-ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ ምስሎች፣ ቪዲዮ እና ድምጾችን ለማጣራት በሚረዳው ‘SynthID Detector’ በመጠቀም ምስሎቹን መርምሯል።

በዚሁ መሰረት ምስሎቹ ጉግል ኤአይ (Google AI) በመጠቀም የተፈበረኩ መሆኑን ተመልክተናል።

በተጨማሪም ምስሎቹን በምልሰት በመፈለግ (reverse image search) ባደረግነው ማጣራት አንዳንዶቹ ምስሎች ትክክለኛ የሌተናል ጀነራል መሀመድ ተሰማ ምስልን ይዘት በመቀየር የተሰሩ መሆናቸዉን አረጋግጠናል።

ትክክለኛው የጀነራሉ ምስል በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ትክክለኛና የተረጋገጠ የፌስቡክ ገጽ ከሁለት ቀናት በፊት የተጋራ ሲሆን በአማራ ክልል የተደረገን ኦፕሬሽን በማስመልከት የተጋራም ነበር፡ https://www.facebook.com/share/p/1BuimH7V2p/?mibextid=wwXIfr

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከምስሉ ጋር ባጋራው የጽሁፍ 'ምስራቅ ዕዝ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጣናዎች ባደረገው ፀረ-ሽምቅ ስምሪት ፈረስ ቤት ፣ ዋሸራ ፣ ጫት ዋርካ ፣ ሐሙስ ገበያ ፣ ሰከላ እና ሌሎች ቀጣናዎች የነበረው ፅንፈኛ ተደምስሷል’ ብሏል።

የሰው-ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የሚፈበረኩ እና ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስል እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ
12,9000049
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

19 de jul. de 2026, 08:21

#Explainer ድምጽ ማቸገን (voice cloning) ምንድ ነው? ጉዳቱስ? እንዴት መከላከል እንችላለን?

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎች ፈጣንና የማያቋርጥ እድገት ለሰው ልጆች በርከት ያሉ ዕድሎችን ይዘው ስለመምጣታቸው በተደጋጋሚ ሰምተናል፣ በአንጻሩ ቀላል የማይባሉ ጉዳቶችን እያስከተሉ ስለመሆናቸውም አድምጠናል።

ለምሳሌም በእነዚህ ቴክኖሎጂዎች የሚፈበረኩ ምስሎች፣ ቪዲዮዎች እና ጽሁፎች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን በማባባስ ረገድ በመጫዎት ላይ ያሉትን አሉታዊ ሚና መጥቀስ ይቻላል።

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopiacheck.org/home/disinformation-threats-posed-by-voice-clones-and-how-to-combat-them/

ኢትዮጵያ ቼክ

ድምጽ ማቸገን (voice cloning) ምንድ ነው? ጉዳቱስ? እንዴት መከላከል እንችላለን? - ኢትዮጵያ ቼክ

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅዎች ፈጣንና የማያቋርጥ እድገት ለሰው ልጆች በርከት ያሉ ዕድሎችን ይዘው ስለመምጣታቸው በተደጋጋሚ ሰምተናል። በአንጻሩ ቀላል የማይባሉ ጉዳቶችን እያስከተሉ ስለመሆናቸውም አድምጠናል። ለምሳሌም በእነዚህ ቴክኖሎጅዎች የሚፈበረኩ ምስሎች፣ ቪዲዮዎች እና ጽሁፎች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን በማባባስ ረገድ በመጫዎት ላይ ያሉትን አሉታዊ ሚና መጥቀስ ይቻላል። አሁን አሁን ደግሞ በሰው…

11,800009
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

09 de jun. de 2026, 08:40

#FactCheck የገቢዎች ሚኒስቴር ዴኤታዋ "በዚህ አመት ከእገታ አምስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል" ብለዋል በሚል ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በርካታ ተከታዮች ባሏቸው ገጾች እና ግለሰቦች ዘንድ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው "በዚህ አመት ከእገታ አምስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል" ብለዋል የሚል ጽሁፍ (Caption) የተለጠፈበት ምስል በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።

ይህ እየተሰራጨ ያለው ምስል የፎቶ ማቀናበሪያ መተግበሪያዎችን በመጠቀም የተቀነባበረ እና ሀሰተኛ መረጃን ለማስተላለፍ ሆን ተብሎ የተሰራ መሆኑን አረጋግጠናል።

ትክክለኛው እና ያልተቆረጠው ምስል የተወሰደው የገቢዎች ሚኒስቴር ሚያዚያ 01 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ካጋራው መረጃ ላይ ነው።

ዋናው መረጃ የሚያወራው የዩናይትድ ኪንግደም የግብር፣ የክፍያ እና የጉምሩክ ባለሥልጣን (HMRC) በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሲያካሂደው የነበረውን የታክስ ትራንፎርሜሽን ፕሮግራም ድጋፍ (Tax Transformation Program) ማጠናቀቁን በሚመለከት ነው (ሊንክ: https://www.facebook.com/share/p/1A2mhcT8s1/)

በዚህ መድረክ ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ ተገኝተው ውይይት ያደረጉ ሲሆን የተሰራጨው ሀሰተኛ ምስል ከዚሁ እውነተኛ የፎቶ ስብስብ ላይ ተቆርጦ የተወሰደ ነው።

ቅንብሩን የሰሩት አካላይ ይህንን ትክክለኛ ምስል በመውሰድ፣ የቴሌቪዥን ዜና እይታውን ትክክለኛ በማስመሰል እና ከስሩ "በዚህ አመት ከእገታ አምስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል" የሚል የሀሰት የሆነ ጽሁፍ በማስገባት አሰራጭተውታል።

ማህበረሰቡ ይህ ምስል የተጭበረበረ እና ከእውነተኛ መረጃ ላይ ተቆርጦ የተወሰደ መሆኑን ተገንዝቦ እንዲህ አይነቱን ሀሰተኛ መረጃ ከማመን እና ከማጋራት እንዲቆጠብ ኢትዮጵያ ቼክ ይመክራል።

ኢትዮጵያ ቼክ!

@EthiopiaCheck
15,7000051
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

09 de jun. de 2026, 08:09

#FactCheck የአርሰናል ደጋፊዎች ‘የዶ/ር ዐቢይ ታማኝ ደጋፊ ነን’ የሚል መልዕክት የያዘ ባነር ይዘዉ የተነሱት ፎቶ በሚል እየተጋራ የሚገኝ ምስል በቅንብር የተሰራ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ባለፉት ቀናት አርሰናል የ2025/2026 ውድድር ዘመን የእንግሊዙ አርሰናል የእግር ኳስ ክለብ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆኑን በማስመልከት የተለያዩ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂደዋል።

በዝግጅቶቹም የክለቡ የቀድሞ ተጫዋች ኢማኑኤል ኢቦዬን ጨምሮ የAFTV ሚዲያ አባላት ከክለቡ ደጋፊዎች ጋር ተገናኝተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንድ በቤተመንግስት ሙዝየም ውስጥ የተነሳ ምስል የበርካቶችን ቀልብ የሳበ ሲሆን መነጋገሪያም ሆኗል።

ይህ ምስል ኢማኑኤል ኢቦዬን፤ የAFTV ሚዲያ አባላት እና ሌሎች ግለሰቦች/ የቡድኑ ደጋፊዎች “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይና ለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ባነር ጀርባ ቆመዉ ይታያል።

ምስሉን ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘Wollo Addis’ የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ የሚገኝ ሲሆን ገጹ ያጋራውን ምስል ከ50 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰዉ አጋርተዉታል፣ ከ2 ሸህ በላይ አስተያቶችም ተሰጥተዉበታል።

ኢትዮጵያ ቼክ የዚህን ምስል ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የተለያዩ መገልገያዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም በምስሉ ላይ ጥልቅ ምልከታ እና የማመሳከር ስራ ሰርቷል።

በቅድሚያ የተነካኩና ይዘታቸው የተቀየረ ምስሎችን ለመመርመር የሚረዳዉን ፎቶ ፎረንሲክስ ድረ-ገጽ በመጠቀም ባደረግነዉ ማጣራት በምስሉ ዉስጥ የሚገኘውና “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይና ለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ጽሁፍ የያዘው ባነር በቅንብር የተካተተ መሆኑን የሚያሳይ ትንተና አግኝተናል።

በተጨማሪ ‘illuminarty.ai’ የተሰኘዉን ድረ-ገጽ በመጠቀም በባነሩ ላይ ባደረግነዉ ምርመራ ባነሩ በሰው-ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ መሆኑን (88%) የሚያሳይ መረጃ አግኝተናል።

በሌላ በኩል ምስሉን በማግዘፍ ባደረግነው ጥልቅ ምርመራ ባነሩን ይዘው የሚታዩ እጆች ቅርጻቸው የተዛባ እና ትክክለኛ ያልሆኑ መሆናቸውን ተመልክተናል። በተጨማሪም በምስሉ በስተቀኝ ዳር ላይ የቆመ ግለሰብ የእጅ ጌጥ ምስሉ በመነካካቱ ይዘቱ የተቀየረ መሆኑን ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ በእለቱ የተነሱ እና የተቀረጹ ምስሎች እና ቪዲዮችን በመመልከትም የማመሳከር ስራ ሰርቷል።

በቤተመንግስት ሙዝየም የተነሳውና ትክክለኛ ፎቶ ላይ በስተግራ ጥግ የሚገኝ ግለሰብ የታችኛው የእግር ክፍል ‘I love Addis Ababa’ በሚለው የፎቶ ፍሬም የተደበቀ ነው።

ነገር ግን “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይና ለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ጽሁፍ የያዘው ባነር ላይ ግለሰቡ ጥቁር ቆዳ መሳይ ጫማ ተጫምቶ ይታያል።

ኢትዮጵያ ቼክ የግለሰቡን የእለቱን እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች የተመለከተ ሲሆን ግለሰቡ በእለቱ የተለያዩ ቀለማት ያለው ስኒከር ጫማ ተጫምቶ እንደነበር ተመልክቷል።

ይህም ባነሩ ያለበት ምስል ከትክክለኛው ምስል ላይ ‘I love Addis Ababa’ ሚለውን የፎቶ ፍሬም በማጥፋት በምትኩ የግለሰቡ የታችኛው የእግር ክፍል ላይ በሰው-ሰራሽ ክህሎት ሀሰተኛ ጫማ የተካተተ መሆኑን አረጋግጠናል።

በዚሁ መሰረት ከላይ የተዘረሩትን ቴክኖሎጂን እና የባለሙያ ምልከታን በመጠቀም ባደረግነዉ ማጣራት “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይና ለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ጽሁፍ የያዘው ባነር ትክክለኛ ያለሆነ እና በቅንብር የተካተተ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።

ትክክለኛ ምስሎች ላይ የተፈበረኩ ይዘቶችን በመጨመር የሚጋሩ መልዕክቶች ለሀሰተኛ እና የተሳሳተ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
13,8000032
Ethiopia Check logo
Ethiopia Check

08 de jun. de 2026, 04:01

#FactCheck በረቀቀ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቅንብር ተሰርቶ ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተጋራ የሚገኘው ቪዲዮ ምንነት

/ኢትዮጵያ ቼክ/- አንድ የፋኖ አባል ለመንግስት እጅ እንደሰጠ የሚጠቁም የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተጋራ ይገኛል። ይህ የተሰራጨው የጽሁፍ መረጃ “የዘመነ ካሴ አብሮ አደግ እና የዘመነ ካሴ ቀኝ እጅ ቴዎድሮስ የደሜ የሚመራውን ታጣቂ አሰልፎ ወደ ሰላም መጥቷል” የሚል መልዕክት ያዘለ ነው።

በተጨማሪም በቪዲዮው ላይ የሚታየዉ ግለሰብ “እኔና ጓደኞቼ ከመንግስት ጋር በመስማማት እጃችንን የሰጠን ሲሆን ከሻብያ ተላላኪዉ ዘመነ ካሴ ጋር የነበረን ግንኙነት በዚ አብቅቷል” ሲል በግልጽ ይደመጣል።

ይህን የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ በስፋት ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘የፍቅር መንገድ’ እና ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ’ የሚባሉ የፌስቡክ ገጾች በዋነኝነት ይገኙበታል።

በተለይም ‘የፍቅር መንገድ’ በተሰኘዉ ገጽ የተጋራዉን ይኸንን የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ ከመቶ አርባ በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ለሌሎች ያጋሩት ሲሆን በርካታ አስተያየቶችም ተሰጥተዉበታል።

ይህንን ጉዳይ ተከትሎ ኢትዮጵያ ቼክ መረጃውን ለማረጋገጥ ባደረገው ጥልቅ ምርመራ ቪዲዮው ፈጽሞ እውነተኛ እንዳልሆነ አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ ቼክ የጉግል ምርት የሆነዉን ‘ሲንዝ አይዲ ዲቴክተር’ (SynthID Detector) የተባለውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መተግበሪያ በመጠቀም በቪዲዮው ላይ ባደረገዉ ማጣራት የተሰራጨው ምስል ትክክለኛ ሰውን እንደማያሳይ ደርሶበታል።

በዚሁ የምርመራ ውጤት መሰረት በቪዲዮው ውስጥ የሚታየው ምስልም ሆነ የሚሰማው ድምጽ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ የተቀነባበረ የፈጠራ ውጤት መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።

በቪዲዮው ላይ የሚታየው የከንፈር እንቅስቃሴ፣ የፊት ገጽታ እና የድምጽ ቅንብር አንድን ትክክለኛ ሰው አስመስሎ በኮምፒውተር ፕሮግራም የተሰራ እንጂ በገሃዱ ዓለም የተፈጠረን ክስተት የሚያንጸባርቅ አይደለም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚፈበረኩ መሰል የዲፕፌክ (Deepfake) ቪዲዮዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ በጣም እየተበራከቱ እና በርካታ ሰዎችን ለተሳሳተ መረጃ እያጋለጡ ይገኛሉ።

አጥፊ እና አሳሳች መረጃ አሰራጪ አካላት እነዚህን እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመጠቀም እውነተኛ የሚመስሉ ነገር ግን ፈጽሞ ያልተፈጠሩ ክስተቶችን በመፍጠር ህብረተሰቡን በማሳሳት ላይ ይገኛሉ።

ይህ አይነቱ ቴክኖሎጂ የፖለቲካ ውዥንብር ለመፍጠር፣ የተሳሳቱ ትርክቶችን ለማራመድ፣ እና የሰዎችን ስነልቦና ለመጉዳት ሆን ተብሎ የሚሰራጭ አደገኛ የሀሰተኛ መረጃ (Disinformation) መሳሪያ ሆኗል።

በተለይም አሁን ባለንበት ወቅት የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ግለሰቦች ያልተናገሩትን እንደተናገሩ አድርጎ በማቅረብ ህብረተሰቡ የተዛባ መረጃን አምኖ እንዲቀበል ማድረግ የተለመደ የማጭበርበር ስልት ሆኖ ብቅ ብሏል።

ሰዎች እውነተኛ ቪዲዮ እየተመለከቱ እንደሆነ በማሰብ እንዲታለሉ እና የተዛባ መረጃን ለሌሎች በማጋራት በማህበረሰቡ ውስጥ አለመተማመንን መፍጠር የዚህ አይነቱ ተግባር ዋና አላማ ነው።

ስለሆነም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ይህንን እያደገ የመጣውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት አደጋ በሚገባ ተገንዝበው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንመክራለን።

ማንኛውም አጠራጣሪ እና ተአማኒ ባልሆኑ የመረጃ ምንጮች ወይም ግለሰቦች የሚጋሩ የምስል እና የቪዲዮ መረጃዎችን ልክ እንዳዩት ከማመናችን እና መልሰን ለሌሎች ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት ማድረግ አለብን።

ቪዲዮዎች ያልተለመደ የዓይን ብልጭታ፣ ከድምጽ ጋር የማይሄድ የከንፈር እንቅስቃሴ ወይም ኢተፈጥሮአዊ የሆነ የቆዳ ገጽታ ካላቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ በጥሞና መመርመር ያስፈልጋል።

ኢትዮጵያ ቼክ!

@EthiopiaCheck
13,4000071

Showing 30 of 52 posts

Avaliação

Login necessário

Frequently Asked Questions

Sobre o que é o canal Telegram Ethiopia Check?+

Ethiopia Check (@ethiopiacheck) é um canal Telegram listado em Exames Públicos no tgdio. Ranking, avaliações, reviews e posts recentes para decidir antes de assinar. Atualmente lista cerca de 24.814 inscritos no tgdio.

Como entrar em Ethiopia Check (@ethiopiacheck) no Telegram?+

Abra o perfil no tgdio e use Join / Open in Telegram para assinar @ethiopiacheck de graça.

Ethiopia Check é um bom canal de Exames Públicos?+

No tgdio você pode ver avaliação, reviews, ranking e posts de Ethiopia Check antes de entrar. Atualmente lista cerca de 24.814 inscritos no tgdio. Compare com canais similares de Exames Públicos.

Onde ver estatísticas e posts de Ethiopia Check?+

No tgdio, abra @ethiopiacheck para stats de inscritos, ranking, avaliações e posts. Use Stats para gráficos.