ኢትዮ መረጃ - NEWS Telegram channel photo

ኢትዮ መረጃ - NEWS

@ethio_mereja_newsPublic Channel

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት ማክበር ባትችል አታዋርዳት ማራመድ ባትችል አታዘግያት መጠበቅ ባትችል አትበትናት። ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም። ለአስታየት @ethio_merjabot @B_promotor

3k

Last views

45.8k (45,817 subscribers)
Membros
—
Rating
100
Total Posts
Oct 20, 2026, 10:12 PM
Atualizado
Mar 31, 2026
Created
Stats

Você está vendo conteúdo em português. Para ver conteúdo em outros idiomas, mude o idioma do site.

Channel Information

Channel Information
Channel Nameኢትዮ መረጃ - NEWS
Username@ethio_mereja_news
CategoryNotícias e Jornais
Languageportuguês
CountryBrasil
Membros45,817
Channel TypePublic Channel
Created31 de mar. de 2026
Last Updated20 de out. de 2026 • anteontem
StatusActive

Classificação

Classificação Global
#106949+253
Classificação por Idioma
#2219+14
Classificação por Categoria
#1005+4

Crescimento de Participantes

Total: 45.8K30 Days growth: +6871.5%
09/2109/2610/0110/0610/1110/1610/20
Crescimento de Participantes - 30 Days
DateSubscribers
21:09:202645,130
22:09:202645,130
23:09:202645,130
24:09:202645,130
25:09:202645,130
26:09:202645,130
27:09:202645,130
28:09:202645,130
29:09:202645,130
30:09:202645,130
01:10:202645,130
02:10:202645,130
03:10:202645,130
04:10:202645,130
05:10:202645,130
06:10:202645,130
07:10:202645,130
08:10:202645,130
09:10:202645,130
10:10:202645,130
11:10:202645,130
12:10:202645,130
13:10:202646,068
14:10:202646,068
15:10:202646,068
16:10:202646,068
17:10:202646,068
18:10:202646,068
19:10:202646,068
20:10:202645,817
Crescimento de Participantes - Weekly
DateSubscribers
Week of 30:03:202649,202
Week of 06:04:202649,102
Week of 13:04:202648,889
Week of 20:04:202648,643
Week of 27:04:202648,643
Week of 04:05:202648,643
Week of 11:05:202648,113
Week of 18:05:202648,113
Week of 25:05:202648,113
Week of 01:06:202647,276
Week of 08:06:202647,276
Week of 15:06:202646,988
Week of 22:06:202646,741
Week of 29:06:202646,741
Week of 06:07:202646,741
Week of 13:07:202646,327
Week of 20:07:202646,127
Week of 27:07:202645,979
Week of 03:08:202645,979
Week of 10:08:202645,979
Week of 17:08:202645,665
Week of 24:08:202645,476
Week of 31:08:202645,296
Week of 07:09:202645,296
Week of 14:09:202645,130
Week of 21:09:202645,130
Week of 28:09:202645,130
Week of 05:10:202645,130
Week of 12:10:202646,068
Week of 19:10:202645,817
Crescimento de Participantes - Monthly
DateSubscribers
March 202649,312
April 202648,643
May 202648,113
June 202646,741
July 202646,127
August 202645,476
September 202645,130
October 202645,817
Crescimento de Participantes - Yearly
DateSubscribers
202645,817

Top 10 posts

Most viewed posts from this channel

By views
  1. #1ማልሁልሽ ቃል ኪዳንም ገባሁልሽ አላት🙏7.2K
  2. #2በኢራንና እስራኤል መካከል ያለው ውጥረት አይሏል‼7.2K
  3. #3የተሳፈሩበት ዶልፊን ተሽከርካሪ ነዳጅ በመጨረሱ ምክንያት ሴኖትራክ ላይ የተሳፈሩ 8 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወ7.2K
  4. #4አለምን ጨለማ አደርጋለሁ-ኢራን‼️7.1K
  5. #5ሽሮ ሜዳ በፖሊስ የተገደለው ወጣት‼️6.9K
  6. #6Post #245256.8K
  7. #7ኢማኑኤል ማክሮን ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ሊመጡ ነው6.8K
  8. #8እንኳን ለልደታ ማርያም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!6.8K
  9. #9ፓኪስታን በኢራን ጦርነት ዙሪያ የሳዑዲ፣ የቱርክ እና የግብፅ ከፍተኛ ዲፕሎማቶችን ለስብሰባ ጠርታለች6.8K
  10. #10ሰበር‼️6.5K

Últimos Posts

ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 de out. de 2026, 19:29

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት (ኦቻ) ለኢትዮጵያ ከ669 ሚሊዮን የዶላር በላይ ለሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ የሚውል ገንዘብ ማሰባሰቡን ገለጸ፡፡

የተሰበሰበው ድጋፍ በአብዛኛው ለአደጋ ጊዜ ምላሽ፣ ለጊዜያዊ መጠለያ እና ለጤና አገልግሎቶች መዋሉንም ኦቻ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡

ከተሰበሰበው አጠቃላይ ድጋፍ ውስጥ 6 ነጥብ 5 በመቶው በተቀናጁ ዕቅዶች አማካኝነት የተገኘ ሲሆን፣ ቀሪው 93 ነጥብ 5 በመቶው ደግሞ በሌሎች የድጋፍ መንገዶች የተገኘ መሆኑን ያመለከተው ኦቻ በተቋማት ደረጃ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከአጠቃላይ ድጋፉ 33 ነጥብ 5 በመቶ ያህሉን በመሸፈን ከፍተኛውን ድርሻ  ይዟል።

በኦቻ መረጃ መሠረት አሜሪካ፣ ስዊድንና ኔዘርላንድስ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብዓዊ እርዳታ ካደረጉ አገራት መካከል የመጀመሪያዎቹን ደረጃዎችን ይዘዋል።
ከአገራት በተጨማሪም የአውሮፓ ኮሚሽንና ማዕከላዊ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ፈንድ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ድጋፍ ካደረጉ ተቋማዊ መካከል መሆናቸውም ተጠቁሟል።
2,970009
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 de out. de 2026, 19:28

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏

የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን!!!

በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ ትጸንሻለሽ፤ አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል” አላት። ሴቲቱም ለባልዋ የሆነውን ሁሉ ነገረችው፡፡ ማኑሄም የተላከው ሰው ዳግመኛ ወደኛ ይምጣ፤ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም።

ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ባልዋንም ጠራችው። ማኑሄም “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? አለው። መልአኩም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው፡፡ መልአኩ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” ብሎ መለሰለት። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው።

መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም በግምባራቸው በምድር ተደፉ። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ሶምሶን ከተወለደ በኋላም የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። ይህ ሶምሶንና ወላጆቹን የረዳው ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

ታላቁ አለቃ ቅዱስ  ሚካኤል ዛሬም ገዳማውያንን በተጋድሏቸው ሁሉ እየተራዳ አብሯቸው ይኖራል፡፡ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ትተው ወጥተዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
2,9000017
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 de out. de 2026, 10:03

አርሰናል ከባየር ሙኒክ ሜዳ ላይ ነጥብ ይዞ ወጣ

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ መርሃ ግብር ተጠባቂ ጨዋታ በጀርመን አሊያንዝ አሬና ተካሄዷል።

አርሰናል ከአስተናጋጁ ባየር ሙኒክ ጋር አቻ በመለያየት ጠቃሚ ነጥብ ይዞ መመለስ ችሏል።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ አርሰናሎች በኤቤሬቺ ኢዜ ጎል ቀዳሚ መሆን ችለው ነበር።

ይሁን እንጂ ዴቪስ ባስቆጠራት ግብ ባየር ሙኒክ አቻ መሆን ችሏል።

በሁለተኛው አጋማሽ አስተናጋጆቹ በሃሪ ኬን የፍጹም ቅጣት ምት መሪነቱን ቢረከቡም፣ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ደቂቃዎች ሲቀረው ዲክላን ራይስ ያስቆጠራት ድንቅ ግብ የአርሰናልን አቻ ውጤት አረጋግጣለች።

በዚህም መሰረት ጨዋታው ባለበት 2 አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ሁለቱም ክለቦች ነጥብ ተጋርተዋል።
4,4200021
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 de out. de 2026, 09:59

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏 የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን!!!

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል፡፡ ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አምነው ለሚጠሩት ረዳት ነው፡፡ በመዝሙር 33÷7 እደተጻፈው ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፡፡ እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል እንደተናገረው ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው፡፡ ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ ይህንን ድንቅ ተአምር መስከረም ዘጠኝ ቀን መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን ትመሰክራለች፡፡ በቀድሞው የሮም ግዛት 'ሩፍምያ' የምትባል ከተማ ነበረች፡፡

ይህች ከተማ በእምነታቸው ጠንካሮች የሆኑ ጥቂት ክርስቲያኖችና በርካታ ኢአማንያን ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት፡፡ በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ፍጹም የእምነት ሰው ነበር፡፡ በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረግ ስለነበር ተበለጥን የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ “ዮናናውያን”ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ፡፡ በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን መከሩና ወሰኑ፡፡ በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ አለ፡፡ በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር፡፡ ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን መንገድ ዘግተው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት ከቀናት በኋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ፡፡
ወንዙ ትልቅ ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ፡፡ በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ ቤተ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በስተቀር ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ሲወጣ ወንዙ እየደነፋ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው፡፡ ከደቂቃዎች በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ እንደሚሆን የተረዳው መጋቢ በታላቅ ድንግጤ ውስጥ ወደቀ፡፡ እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ በመላዕክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ምስለ ስዕል ፊት ወድቆ ተማጸነ፡፡ ታላቁ ወንዝ ቤተ ክርስቲያኑን ጠርጎ የሚወወስደው ከሆነም የሚሆነውን ነገር ለመቀበልና ከዚያም ላለመውጣትም ወሰነ፡፡ ትንሽ ቆይቶ በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ፡፡ በዚህ ጊዜ የመላዕክት ሁሉ አለቃቸው ለጠራውም ፈጥኖ የሚደርሰው ቅዱስ ሚካኤል በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ፡፡

መጋቢውንም "ጽና አትፍራ፣ እኔ ካንተ ጋር ነኝና" ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት፡፡ በዚያች ቅጽበትም ትልቅ ሸለቆ ተፈጠረ፡፡ በአስፈሪ ሁኔታ ሲመጣ የነበረው ወንዝም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ፡፡ የሚገርመው ነገር የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሸለቆው የተፈጠረው ከቤተ ክርስቲያኑ በታች መሆኑ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ ግን ጸንቶ ቆመ፡፡ መጋቢውም እግዚአብሔርንና ቅዱስ ሚካኤልን አመሰገነ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ፡፡ በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው፣ መልአኩንም አከበሩት፣ አሕዛብ ግን አፈሩ፡፡

ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያስገዙ ገዳማውያንና ቅዱሳን ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
4,2700021
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

21 de out. de 2026, 19:28

የሕወሓት መሪዎች ኤርትራ ይገኛሉ ሲሉ ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ ተናገሩ

የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) መሪዎች ኤርትራ ውስጥ ይገኛሉ ሲሉ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ተባብሮ የሚሠራው የትግራይ ሰላም ኃይል አዛዥ ተናገሩ ። በትግራይ ክልል ባለ አደራ አስተዳደር፦ የፀጥታና ሰላም ዋና አስፈጻሚ ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ ይህንኑ ለፈረንሣይ ዜና አገልግሎት (AFP) ተናግረዋል ።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንሥትር የማነ ገ/መስቀል የጄኔራሉን አባባል ውድቅ አድርገዋል ። መሪዎቹ ኤርትራ ውስጥ ይገኛሉ ስለመባሉ AFP ወዲያውኑ ማረጋገጫ ኣለማግኘቱን አክሎ ዘግቧል ።

ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ ትናንት ማክሰኞ፤ ጥቅምት 10 ቀን፣ 2019 ዓ.ም መቐለ ከተማ ውስጥ ለነዋሪዎች ባሰሙት ንግግር፦ «የሕወሓት መሪዎች ወደ ኤርትራ ድንበር ተሻግረዋል» ማለታቸውን የዜና ምንጩ ጠቅሷል ። አያይዘውም፦ «ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሣሪያ ቁሳቁስ እና መድኃኒቶችንም» መሪዎቹ መውሰዳቸውን ተናግረዋል ።

ከፌዴራል መንግሥት በሚሰጠው አቅጣጫና መመሪያ መሠረት ትግራይ ክልልን ለሚቀጥሉት 6 ወራት እንዲያስተዳድር ከተቋቋመው ባለአደራ አስተዳደር አባላት አንዱ ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር ያሰሙትን ንግግር ኤርትራም ሕወሓትም አጣጥለዋል ። የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር አማኑኤል አሠፋ፦ የሕወሓት «አመራር ትግራይ ውስጥ እየሠራ ነው» ሲሉ ለዜና ምንጩ ተናግረዋል ።
5,2000016
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

21 de out. de 2026, 19:16

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ምልጃው እና ረድኤቱም አይለየን🙏

ድርሳነ ሩፋኤል ላይ ተጽፎ እደምናገኘው 7 ሊቃነ መላዕክት ሲኖሩ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፤ የስሙ ትርጓሜም “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ነው። ከእግዚአብሔር ዙፋን ስር ትዕዛዝ በወጣ ግዜ ኪሩቤል ተቀብለው ለሱራፌል ያስተላልፋሉ፤ ሱራፌልም ለሚካኤልና ለገብርኤል ለሩፋኤልም ያደርሳሉ፡፡ ሚካኤል ለፍጥረቱ በጎም ይሁን ክፉ ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ መላዕክትን ያዛቸዋል፤ ኪሩቤልና ሱራፌል መላዕክቱም ሁሉ አቤቱ የእጅህን ስራ አታጥፋ እያሉ ቀንና ከማታ ይለምናሉ። የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያቢሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ እግዚአብሔር ይገስፅህ አለው እንጂ የስድብን ቃል አልተናገረውም ሲባል ሰምተናል፡፡ ሊቀ ነብያት ሙሴ እጅግ ታዛዥና የዋህ ስለነበርና ከንዓንን ለማየት ወደ ናባው ተራራ ሲወጣ 2 መላዕክት በአረጋውያን ተመስለው መቃብር ሲቆፍሩ ቢያይ ላግዛቹ ብሎ መቆፈሪያውን ተቀበላቸው፡፡

በመጨረሻ “ሰውየው በአንተ ልክ ነውና እስቲ ገብተህ ለካልን” አሉት፡፡ እሱም በየዋህነቱ ጉድጓዱ ውስጥ ገብቶ እንደተኛ እንደ እንቅልፍ አሸልቦት በዚያው ዐረፈ፤ መላዕክቱም ቀበሩት። እስራኤላዊያን ሙሴን እጅግ ስለሚወዱት የሙሴን መቃብር እንደ ጣዖት እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን መቃብር ሰወረው፤ ነገር ግን ጠላት ዲያቢሎስ ሊያሳያቸው በመነሳቱ ቅዱስ ሚካኤል ተቃወመው፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ሚካኤል ዲያቢሎስን እግዚአብሔር ይገስጽህ ብሎ ከእርሱም ሰወረበት። በሐዋርያው ይሁዳ መልዕክት ቁጥር 8 የሚገኘው ቃል የቅዱስ ሚካኤልን ትዕግስት ያሳያል፡፡ ዳግመኛም አይሁድ ጌታን ሲሰቅሉት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በቁጣ ሰይፉን አወጣ፤ ቅዱስ ሚካኤል ግን በአይሁድ ስራ አዝኖ ፈጣሪን ፍጡራን ሰቀሉት እያለ በአርምሞና በትዕግስት አያቸው ይላል ድርሳኑ።

ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33÷7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” ይለናል፡፡ በትንቢተ ዳንኤል 10÷13 እና 10÷21 ደግሞ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ዳኛዬ ነው የተባለው ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም ስለ ቅቅዱስ ሚካኤል እንዲህ ሲናገር ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፣ በተዘጋ ጉድጓድ ሲያጽናናው ደግሞ “ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም” አለ፡፡ በዓለም ፍፃሜም ስለህዝቡ የሚቆመው ሚካኤል ይነሳል። በማለትረ በምዕራፍ 12÷1 ጽፎልናል፡፡ በራዕይ 8÷3 “የቅዱሳኑ ፀሎት ከዕጣኑ ጢስ ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ወጣ” ተብሎ እንደተጻፈውም መላዕክት የቅዱሳኑን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርጋሉ፡፡ ገዳማውያን የሚያደርጉት ጸሎትና የሚያቀርቡት መስዋዕት በእርሱ ምልጃ ያርጋልና ገዳማቸውን እየረዳን በዓታቸውን እያጠናን የበረከታቸው ተካፋይ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
4,9800024
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

21 de out. de 2026, 10:07

መሳሪያው የሚመጣው ከግብፅ ነው-ጄኔራል ገብረ አድሃና‼️
የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሜጀር ጀኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን የጦርነት መንገድ በመቃወም ወደ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።
ሜ/ጄኔራል ገበረ አድሃና ከ ኤንቢሲ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ንግግር ህወሃት የታጠቃቸው መሳሪያዎች መነሻቸው ግብጽ መሆኑን ተናግረዋል።
መሳሪያዎቹ የሚገቡት ከግብፅ በቀጥታ የገቡ አሉ፣እንደገና ከግብፅ በኤርትራ እና በሱዳን በኩልም የገቡ አሉ ብለዋል።
ህወሓት እነዚህን መሳሪያዎች ተርክቦ ድሮን ጭምር ለሌሎች ታጣቂዎች ሲያከፋፍል እንደነበር አውቃለሁ ብለዋል።
5,4300022
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

21 de out. de 2026, 10:06

የአቡነ ሀብተ ማርያም ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏

በምጽዋትና በስገድት የምትጋደለው እናቱ ዮስቴና ሀብቷን ሁሉ ለድሆች ሰጥታ ለምናኔ ወደ በረኃ ሄደች።

በዚያ ያገኘችው ባሕታዊም በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ከእርሷ ቅዱስ ፍሬ እንደሚወጣ ነግሮ ወደ ዓለም እንድትመለስ አዘዛት። እርሷም “እግዚአብሔር የወደደው ይሁን” ብላ እያመሰገነች ተመልሰች፡፡ የአባቱ የትውልድ ሀገር የራውዕይ በምትባል ሀገር ሲሆን ከዚህች የተባረከች ሴት ጋር ተጋባ። እርሷም በበጎ ምግባርና ሥራ የተጌጠች፣ በሕግ ተወስና በጾም፣ በጸሎት፣ የምትተጋ ነበረች።

ከጥቂት ጊዜያት በኋላም ወንድ ልጅ ወለደች። እንደ ሥርዓቱም ሲጠመቅ የመጽሐፍ ስሙን “ሀብተ ማርያም” አሉት። በሕገ እግዚአብሔር አንጸው አሳደጉት። ወደ ቤተ ክርስቲያንም ሲወስዱት “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ” የሚለውን ጸሎት ቢሰማ እጅጉን ወደዳት። እርሷንም ይዞ ከቤቱ ሌሊቱን የሚጸልይና የሚጋደል ሆነ።   

አንድ ቀን የአባቱ በጎቹን ሲጠብቅ የበግ ጠባቂዎቹን “ዛሬ ዝናም ይዘንማልና እንግባ” አላቸው። እነርሱም “ምን ደመና አለ፤ ቀኑ ብራ ነው” አሉት። እርሱ ግን በጎቹን ይዞ ወደ ቤቱ እንደገባ ኃይለኛ፣ ነፋስና መብረቅ የቀላቀለ ዝናም ዘነመ። በሌላም ጊዜ እንዲሁ አንድ እረኛ የሀብተ ማርያምን በትሩን በጉልበት ነጠቀው። “መልስልኝ” ብሎ በስመ እግዚአብሔር ቢያምለውም እምቢ አለው። በተወው ጊዜ እግዚአብሔር ያን እረኛ በአየር ላይ ሠቅሎ አዋለው። እረኞቹም ሀብተ ማርያምን ሲለምኑት፣ እግዚአብሔር ነውና ስለ ስሙ ብሎ የቀጣው መሐሪው እርሱ ከወደደ ይማረው ሲል ያ እረኛ ተፈታና ወረደ። መጥቶም ከአባታችን እግር ስር ወደቀ፡፡ በኋላም ስሟ እለ አድባር ወደምትባል ገዳም ገብቶ ከአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሶ ታላቅ ተጋድሎ ይጋደል ጀመር። በባሕር መካከልም በመቆም መዝሙረ ዳዊትን ይደግምና ግንባሩም የባሕሩን አሸዋ እስኪነካ 500 ጊዜ ይሰግዳል።

እህልም መቅመስን ትቶ የዱር ቅጠል የሚመገብ ሆነ። ዐርባ ዐርባ፣ ሰማንያ ሰማንያ ቀንም ያከፍላል። በሌሊትም ቁሞ በማደር በቀንም አራቱን ወንጌላት ዘወትር ይጸልያል። ተጋድሎውንም ያየ አምላካችን ተገለጠለት። አባ ሀብተ ማርያምም ከግርማው የተነሣ ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ። ጌታችንም እፍ ብሉ አጽናንቶ አሥነሳውና ጽኑዕ ተጋድሎው በሰማያት መጻፉን ነገረው፡፡ ስለ ድንግልናው፣ ስለ ምናኔው፣ ስለ ፍጹም ምንኲስናው፣ አራቱን ወንጌላት አዘውትሮ በማንበቡ፣ ረኃብና ጥምን በመታገሡ፣ በልቡ ቂምንና በቀልን ባለማኖሩ፣ ስለ ንጹሕ የክህነት አገልግሎቱና በንጽሕና ስለሚያሣርገው መሥዋዕቱ ሰባት እጅግ የሚያስደንቁ አክሊላትንም አቀዳጀው። የቅዱስ ማቴዎስንና የቅዱስ ማርቆስን ወንጌል ሲያነብ ከሌሎች ሥውራን አበው ጋር የሚገናኝበትን የብርሃን ሠረገላ ሰጠው፡፡

የቅዱስ ሉቃስንና የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል ሲያነብም ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድበትን የእሳት ሠረገላ ሰጠውና ቃል ኪዳን ገባለት። መታሰቢያውን ለሚያደርጉና በስሙ ለሚዘክሩ፣ ከእነርሱ ጋር የሚኖርበትን አምስት መቶ የወርቅ አምዶች ያሏትን ቦታ ሰጠሁህ አለው። ቅዱሳን መላእክት ሁሉ እየተደሰቱ አባታችን አቡነ ሐብተ ማርያምን “ወንድማችን ወደማያልቀው ሰማያዊ ደስታ ልንወስድህ መጥተናል” አሉት። ይህንንም በተናገረ ጊዜ ጌታችን በሦስትነቱ ተገልጦ ታየው። በኅዳር 26 ቀን ነፍሱ ከሥጋው በሰላም ተለየች።

ቅዱሳን መላእክትም በታላቅ ደስታ እያመሰገኑ አሣረጓት። ገዳማውያን የዓለምን ክብር ንቀው ሔደዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ በዓታቸውን እናጽና ገዳማቸውን እንደግፍ የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡   

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
5,4000020
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

20 de out. de 2026, 19:12

ጥቅምት 10 2019

በአዲስ አበባ ጥሬ ስጋ በኪሎ እስከ 6 ሺህ ብር የሚሸጥባቸው ቦታዎች አሉ፡፡

ይህን ተከትሎም ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚድያ ጭምር መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

የከተማዋ ንግድ ቢሮም በጉዳዩ ላይ ከልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ጋር ሊነጋገር ቀጠሮ መያዙ ተሰምቷል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ሸማቾችን፣ የልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበርን፣ የሸማቾች ፣ መብት ተቆርቋሪ ድርጅትን ሃሳብ ጠይቀናል፡፡

የስጋ ተወደደብን ድምፆች ደጋግመን ሰምተናቸዋል፤ ይሁንና ስጋ በገበያው ላይ ያለው ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ እየጨመረ መጥቶ በከተማችን አዲስ አበባ በሸማች ህብረት ስራ ምህበራት 1200 ብር በየልኳንዳ ቤቶቹ ደግሞ ከዝቅተኛው 1 ሺህ 800 ብር እስከ 6 ሺህ እየተሸጠ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሰሞኑን ባወጣው የመስከረም ወር 2019 ዓ.ም የዋጋ ግሽበት 14.9 መድረሱን ይፋ ባደረገበት መረጃው የስጋ ዋጋ ግሽበት 22 በመቶ መድረሱን ተናግሯል፡፡

ሃሳባቸውን የሰጡን ሸማቾች እንደሚያነሱት እንደ አብዛኞቹ ሸቀጦች በስጋ ላይ እየተደረገ ያለው የዋጋ ጭማሪ ምክንያታዊ አይደለም፡፡

በየልኳንዳ ቤቶቹ የሚጠራው ዋጋ መካከል በኪሎ እስከ 4 ሺህ ብር የሚደርስ የዋጋ ልዩነት ያለው መሆኑ በመንግስት ምን ያህል ቁጥጥር እንደማይደረግበት የሚያሳይ ነው መንግስት ጣልቃ መግባት አለበት ባይ ናቸው ሸማቾቹ፡፡

ስለ ጉዳዩ ሃሳቡን የጠየቅነው የሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት በበኩሉ ባለፉት ዓመታት ስሰራ የቆየሁት ሸማቹ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ሲደረግበት በአግባቡ ጥያቄ እንዲያነሳ፤ ምርቱን ለተወሰነ ጊዜ አለመጠቀምን ጨምሮ ነጋዴው እና መንግስትንም ላይ ጫና በማሳደር መፍትሄ እንዲመጣ እንዲያደርግ ነበር፡፡

አሁን በስጋ ላይ እየተነሳ ያለው ጥያቄ ሸማቹ የባህሪ ለውጥ ማምጣቱን የሚያሳይ ነው ብሏል፡፡

መንግስት ንግዱን ነፃ ገበያ በሚል እንዲሁ ከመተው ይልቅ በአንድ ምርት ላይ እስከ 4 ሺህ ብር የደረሰ የዋጋ ልዩነት ሲፈጠር ምን ተፈጥሮ ነው? ብሎ ወረድ ብሎ በማየት የማስተካከል ሃላፊነት አለበት ያሉን የኢትዮጵያ የሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቁምላቸው አበበ ናቸው፡፡

ቅሬታው የተነሳባቸውን የልኳንዳ ነጋዴዎች በአባልነት የያዘው የአዲስ አበባ የልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ጥቂት ልኳንዳ ቤቶች አሉ፤ ይህ አግባብ አይደለም ብሎናል፡፡

የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ አየለ ሳህሌ በሰጡን ምላሽ ጉዳዩ መነሳቱ እንድንነጋገር በር ይከፍታል፤ እንደ ማህበር እነዚህን ነጋዴዎች መቆጣጠር አንችልም ይህ የመንግስት ስራ ነው ብለውናል፡፡

ችግር ያለባቸው ነጋዴዎችን መቆጣጠሩ የምንደግፈው ሆኖ ሳለ ህብረተሰቡ ሊያውቅልን ይገባል ያሉትን የእንሰሳቱ ዋጋ መወደድ፣ የሚጣልባቸውን ተደራራቢ ግብር፣ የቤት ኪራይና የሰራተኛ ወጪ ከፍተኛ መሆኑ ከግምት ውስጥ ይግባልን ይላሉ።

ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል በሚል ከማህበረሰቡ ቅሬታ ስለተነሳበት የጥሬ ስጋ ጉዳይ ለመነጋገር የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ጋር ቀጠሮ መያዙን ማህበሩ ነግሮናል፡፡

ውይይቱ በሁሉም ወገን ያሉ ችግሮች ተነስተው አሁን ላለው የስጋ ዋጋ መናር መፍትሄ ይዞ ይመጣል የሚል እምነት እንዳላቸው የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ አየለ ሳህሌ ነግረውናል፡፡
5,7800035
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

20 de out. de 2026, 19:11

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏

ቤተክርስቲያናችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን ሁሉ በላይ በማለት ክብሯን ትገልጻለች። ኦርቶዶክሳዊያን ከሕጻንነታችን ጀምረን የእመቤታችንን ምስጋና እንማራለን፣ ሁልጊዜም በአባታችን ሆይ ጸሎት ጀምረን በመልኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ብለን ድንግል ማርያምን እናመሰግናታለን። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱሳን ሁሉ የምትመሰገን ናት። እርሷ ያላትን ክብር እንዴት እንደሚገልጹት ተጨንቀው በምን በምን እንመስልሻለን በማለት በሰው ህሊና የሚለካ ምሳሌ ማጣታቸውን ብዙ ቅዱሳን ተናግረዋል። የብህንሳው ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስ፣ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምና ኢትዮጵያዊው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ክብሯን ገናንነቷን በስፋት ተናግረዋል፣ አመስግነዋታል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት።

ጌታችን አምላካችን ኢየሱ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሳ፤ በእርሷም የመለኮትና የስጋ ፍጹም ተዋህዶ ተፈጸመ፡፡ የማይወሰነውን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኗ ወሰነችው፡፡ ከዓለም በፊት ከአብ ያለእናት እንደተወለደ፣ ከእርሷ ደግሞ ድህረ ዓለም ያለ አባት ተወለደ፡፡ አምላክ እኛን ለማዳን ሰው ሆነ፣ ሰው አምላክ ሆነ ስንል በተዋህዶ ነውና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አማላክ ትባላለች፡፡ እመቤታችን በሀሳብም በሥጋም ዘላለማዊት ድንግል ናት። በሀሳቧ በህሊናዋ ከአምላክ ህግና ሀሳብ በስተቀር ስጋዊ ሀሳብ ፈጽሞ ኖሮ አይውቅምና ከሰው ወገን ተለይታ የህሊና ድንግልና አላት፡፡

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች መሆኗን በመመስከር ይህን የህሊና ድንግልና ያስረዳናል። መልአኩም ልጅ ትወልጃለሽ ብሎ ሲያበስራት “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል” ብላ መናገሯ “ስለ ወንድ ፈጽሞ አስቤ አላውቅም” ማለቷ ነውና የህሊና ወይም የሀሳብ ድንግልናዋን ያስረዳናል። ከመፅነሷ በፊት፤ በፀነሰች ጊዜ፤ ከፀነሰች በኋላ፤ ከመውለዷ በፊት፤ በወለደችም ጊዜ፤ ከወለደች በኋላ ድንግል ናት፡፡ ገዳማውያን ይህን ክብሯንና አማላጅነቷን አምነው ዘወትር አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡ 

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
5,3500025
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

20 de out. de 2026, 17:14

Photo1/2
"ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ" የሚለው መረጃ ሀሰተኛ ነዉ

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ የሚለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ተገለጸ።

​የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ ተሹመዋል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የቆየው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀና ሀሰተኛ መሆኑን ኩባንያው ለካፒታል ጋዜጣ አስታወቀ።

​በአሁኑ ወቅት ኩባንያውን በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት (Acting CEO) እየመሩ የሚገኙት በኢትዮ ቴሌኮም የዳይሬክተሮች ቦርድ ኃላፊነት የተሰጣቸው አቶ ታሪኩ ደምሴ መሆናቸው ተረጋግጧል።

Via ካፒታል
5,5500013
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

20 de out. de 2026, 11:19

ህወሃት ላይመለስ ሄዷል-ጄ/ል ታደሰ ወረደ‼️
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በወቅታዊ የትግራይና የሀገሪቱ የፖለቲካ እና የደህንነት ሁኔታዎች ላይ ከአውራ አምባ ታይምስ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

​የእገታው ሂደት እና የተፈጠረው ውዝግብ
​ጀነራል ታደሰ ወረደ በቃለ መጠይቁ ወቅት በቅርቡ ስለገጠማቸው እገታ ሂደት ዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል፦
​የእገታው አጀማመር፦ ሌሊት በቁጥጥር ስር ለማዋል የተደረገው ሙከራ ተገቢ እንዳልነበር እና በፖሊስ ሽፋን የመጡ አካላት እንደነበሩ ገልጸዋል።
​የተወሰደው እርምጃና ዝውውር፦ ከቤት ከተወሰዱ በኋላ በኤች ዜድ (HZ) ሆቴል እንዲቆዩ መደረጉን፣ በመቀጠልም በአክሱም፣ አድዋ እና ራማ አቅጣጫዎች እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ ተናግረዋል።
​የውሳኔው አካላት፦ ውሳኔውን ያሳለፉትና ያስፈጸሙት ይፋዊ የነበረው መንግስታዊ መዋቅር ሳይሆን፣ በፖለቲካ እና በሚሊተሪ ስብስብ የተዋቀረ “የአቋቋምት ኮሚቴ” እና ራዲካል አካላት እንደሆኑ ጠቁመዋል።

​ከመከላከያ ሰራዊት ጋር የተደረገ ግንኙነት፦ ከራማ ከተማ በመውጣት ከአድበራና ከአሮህ መካከል ከአገኘው የመከላከያ ሰራዊት አባላትና አመራሮች ጋር በሰላም መገናኘታቸውን አብራርተዋል።

​በእሳቸው ላይ ለሚነሱ ወቀሳዎችና ዘመቻዎች የተሰጠ ምላሽ
​በተለያዩ ማህበራዊና መደበኛ ሚዲያዎች በጀነራል ታደሰ ወረደ ላይ ለሚሰነዘሩ ቅሬታዎችና ጥርጣሬዎች የተሰጡ ምላሾች፦
​የህወሓት ሃይል በማደራጀትና ደንብ በማውጣት ሂደት፦ በወቅቱ የተሰሩ ስራዎች በሙሉ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ እና ከካቢኔው አሰራር ጋር የተያያዙ እንደነበሩ ገልጸዋል።

​የአቋም ልዩነቶችና ተቃውሞዎች፦ በየደረጃው በነበሩ ውሳኔዎች ላይ የነበራቸው ተቃውሞና ልዩነት በሰነድና በሪኮርድ የተያዘ መሆኑን አብራርተዋል።

​የጦር መሳሪያዎች ምዝገባና አመጣጥ፦ በስልጣን ዘመናቸው የተከናወኑ የደህንነት ስራዎች ግልጽ እንደነበሩና ከእሳቸው እውቅና ውጪ በድብቅ የተሰሩ ነገሮች ካሉ ማጣራት እንደሚቻል ገልጸዋል።
​ስለ ህወሓት የወደፊት እጣ ፈንታ እና የሽግግር ወቅት
​ጀነራል ታደሰ ወረደ ስለ ድርጅቱ ህልውና እና ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፦

​የህወሓት የፖለቲካ ማብቂያ፦ ህወሓት በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ማብቂያው ላይ እንደሚገኝና ድርጅቱን በሰላም ማሳረፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።
​ለድርጅት ህልውና የሚከፈል መስዋዕትነት ማብቃት አለበት፦ “ህወሓት ከሌለ ትግራይ የለችም” የሚለው አስተሳሰብ የተሳሳተ መሆኑንና ድርጅቱ ሳይኖርም ትግራይ እንደምትቀጥል አስረድተዋል።
"ሰራዊቱም ከሞተ ጋር መሞት የለበትም የTPLF አመራሮች አንድ የተሳካላቸው ነገር ቢኖር፣ ድርጅቱን ወደ መቃብር አውርደውታል፣ላይመለስ ሄዷል" ብለዋል።
​የወጣቱ እና የአዲሱ ትውልድ ድርሻ፦ አመራሩ ከወጣቱ ትውልድ ጋር መቆራረጡን ጠቅሰው፣ የትግራይ ህዝብና አዲሱ ትውልድ የራሱን እድልና ህልም መቅረፅ እንዳለበት አሳስበዋል።
​የሰላም አስፈላጊነት፦ ህዝቡ ተጨማሪ ጦርነትና ውድመት መሸከም የማይችል በመሆኑ ትኩረቱ በፖለቲካዊና በሰላማዊ መፍትሔዎች ላይ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
5,8200032
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

20 de out. de 2026, 11:16

ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ፣ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ ነበረ 🙏

ነቢዩ ዳንኤል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ “ዐይኖቼንም አነሣሁ እነሆም በፍታ የለበሰውን፣ ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡ በዳንኤል 10÷5-9 የተገለጸው የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም ከእሳት ያወጣ እርሱ ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “አምላክ ወሰብእ” ሰውና አምላክ ማለት ሲሆን ከዋነኞቹ የመላዕክት አለቆች አንዱ ነው፡፡

አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ውሃ በተሞላውና ወላፈኑ በማያስቀርበው ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ አዳናቸው። ቅድስት ኢየሉጣ ልጇ እንዳይገደል ለራሷም ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው ሥጋዊ ፍርሀት ቢያድርባትም የሦስት ዓመት ልጇ እናቴ ከእቶን እሳቱ የተነሳ አትፍሪ ሶስቱን ሕጻናት ያደነው ያድነናል እያለ በቀሚሷ ጎተታት፤ ወደ ጌታችን ሲጸልይላት ፍርሃቱ ርቆላታል፡፡ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤልም ከሰማይ ወርዶ የሚንተከተከውን ውሃ አቀዝቅዞ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ከዐበይት የመላእክት ነገዶች መካከል አንዱ በሆነው አርባብ፣ አጋእዝት ወይም ጌቶች በሚባለው ዐቢይ ነገድ ላይ የተሾመ ሲሆን ከበታቹም የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉ፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ በቈላስያስ 1÷16 በቅዱሳን መላእክት ዘንድ ስላሉት ነገዶች ሲገልጽ “… በሰማይ ያለውን በምድር ያለውን የሚታየውንምና የማይታየውን መናብርትም ቢሆኑ አጋእዝትም ቢሆኑ መኳንንትም ቢሆኑ ቀደምትም ቢሆኑ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ” በማለት ነገደ መላዕክትን ይዘረዝራቸዋል፡፡ ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው ልጆች ጠላት ዲያብሎስን ተዋግተው ድል ከመንሳታቸው አስቀድሞ መላዕክት ማን ፈጠረን ብለው ግራ ሲጋቡ ቅዱስ ገብርኤል ፈጣሪ ነኝ ያለውን ሳጥናኤልን በመቃወም “አይዞአችሁ ፈጣሪያችን ፈጥሮ አይጥለንምና አስክናገኘው፣ እስክናውቀው ድረስ በያለንበት ጸንተን እንቁም፡፡” በማለት አረጋግቷቸዋል፡፡ በኢሳይያስ 14÷16ም በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ተጽፏል፡፡

“አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምድር ጥልቅም ትወርዳለህ” ይለናል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ፣ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡
ዛሬም ዓለምን ትተው የመነኑ ገዳማውያ አማላጅነቱንና ፈጣን ተራዳኢነቱን አምነው ሲጠሩት ይራዳቸዋል፡፡ እኛም ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጸና ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
5,6000017
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 22:00

መኪና መውረስ ተጀመረ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በክልሎች በወጡ የንግድ ፈቃዶች ተጠቅመው በመዲናዋ ውስጥ ያለ ፈቃድ እና በየመንገዱ ዳር ተሽከርካሪዎችን ለሽያጭ የሚያቀርቡ አስመጪዎች ላይ ከውይይትና ከማስጠንቀቂያ ያለፈ ቀጥተኛ የህግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ ጀመረ። በዚህም መሰረት ቢሮው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡ ፍርድ ቤት አካባቢ በህዝብ መንገድ ዳር ያለ ከተማ አስተዳደሩ እውቅና ለሽያጭ ቀርበው የነበሩ ሶስት ቢዋይዲ እና አንድ ቻንጋን የተሰኙ አዳዲስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። ይህ እርምጃ በዋናነት ያነጣጠረው የንግድ ፈቃዳቸውን ከአዲስ አበባ ውጪ በሆኑ ክልሎች አውጥተው፣ የሽያጭ ስራቸውን ግን በመዲናዋ ውስጥ በማከናወን የከተማዋን የታክስ ገቢ በሚያሳጡ ነጋዴዎች ላይ ነው። የገቢዎች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ አንድ አስመጪ በድንበር ላይ የጉምሩክ ቀረጥ መክፈሉ ወይም የማስመጣት ፈቃድ መያዙ ብቻውን በአዲስ አበባ ውስጥ የችርቻሮ ሽያጭ ለማከናወን ህጋዊ አያደርገውም። በመሆኑም በክልል ፈቃድ የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎች ወደ መዲናዋ የታክስ መረብ መግባት እና ከመንገድ ዳር የድለላ ሽያጭ ወጥተው እውቅና ባለው የመሸጫ ስፍራ ብቻ መስራት ይጠበቅባቸዋል።

ይህ የከተማ አስተዳደሩ እርምጃ በኢትዮጵያ የታክስ አስተዳደር እና በታዳጊው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ገበያ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት የሚሹ መሰረታዊ ጉዳዮችን ያስነሳል። በመጀመሪያ ደረጃ የሚጠቀሰው በክልሎች እና በፌዴራል ከተሞች መካከል ያለው የታክስ ወሰን ውዝግብ ነው። ነጋዴዎች አነስተኛ የታክስ ተመን ወይም ላላ ያለ ቁጥጥር ባለባቸው ክልሎች የንግድ ፈቃድ አውጥተው፣ ትልቁ ገበያና ሸማች ወዳለባት አዲስ አበባ መጥተው መስራታቸው በከተማ አስተዳደሩ የገቢ አሰባሰብ ላይ ከፍተኛ ክፍተት ፈጥሯል። ይህ ድርጊት በክልሎች እና በመዲናዋ መካከል የተናበበ የንግድ ምዝገባ እና የታክስ ክትትል ስርዓት አለመኖሩን የሚያጋልጥ ሲሆን፣ አዲስ አበባ የምታቀርበውን መሰረተ-ልማት እየተጠቀሙ ግብር ግን ለሌላ ክልል የሚከፍሉ ተቋማትን ለመግታት የተወሰደ ስልታዊ እርምጃ መሆኑን ያሳያል።

ከዚህም ባሻገር ጉዳዩ ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ገበያ መስፋፋት እና ከቁጥጥር ክፍተት ጋር በቀጥታ ይያያዛል። የፌዴራል መንግስቱ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ማገዱን ተከትሎ፣ የቻይና የኤሌክትሪክ መኪኖች የመዲናዋን ገበያ በፍጥነት ተቆጣጥረውታል። መንግስት የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማበረታታት በጉምሩክ ቀረጥ ላይ ማበረታቻ ቢሰጥም፣ የሀገር ውስጥ የሽያጭ ሰንሰለቱ ግን በህገ-ወጥ ደላሎች እና መንገድ ዳር በሚደረግ ኢ-መደበኛ ንግድ የተዋጠ ሆኗል። በመሆኑም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የወሰደው እርምጃ፣ መንግስት በጉምሩክ በኩል ያጣውን ገቢ በሀገር ውስጥ የሽያጭ እና የትርፍ ግብር ለማካካስ መቁረጡን በግልጽ ያመላክታል።

ይሁን እንጂ በህግ ማስከበር ሂደቱ ውስጥ የሚታየው የመረጃ ግልጽነት እጥረት የራሱን ጥያቄዎች ማስነሳቱ አልቀረም። ቢሮው መኪኖቹን ከመውረሱ በፊት ተደጋጋሚ ውይይትና ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ቢገልጽም፣ እስካሁን በዚህ የህግ ክፍተት ምን ያህል ገቢ እንደታጣ፣ ምን ያህል ነጋዴዎች በክልል ፈቃድ እንደሚሰሩ እንዲሁም የተያዙት መኪኖች ዋጋና የሚጣልባቸው የቅጣት መጠን ምን ያህል እንደሆነ ይፋ አለማድረጉ የአሰራር ግልጽነት ጥያቄን ያስነሳል። በቀጣይ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተጠናክሮ ይቀጥላል የተባለው ይህ የጋራ የህግ ማስከበር ዘመቻ፣ የመኪና ገበያውን ወደ ህጋዊ ስርዓት ከማስገባት ባለፈ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተሽከርካሪዎች የመሸጫ ዋጋ ላይ ተጨማሪ ጭማሪ ሊያስከትል እንደሚችል የዘርፉ ታዛቢዎች ይገምታሉ።
3,9400017
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 21:53

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏

ቤተክርስቲያናችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን ሁሉ በላይ በማለት ክብሯን ትገልጻለች። ኦርቶዶክሳዊያን ከሕጻንነታችን ጀምረን የእመቤታችንን ምስጋና እንማራለን፣ ሁልጊዜም በአባታችን ሆይ ጸሎት ጀምረን በመልኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ብለን ድንግል ማርያምን እናመሰግናታለን። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱሳን ሁሉ የምትመሰገን ናት። እርሷ ያላትን ክብር እንዴት እንደሚገልጹት ተጨንቀው በምን በምን እንመስልሻለን በማለት በሰው ህሊና የሚለካ ምሳሌ ማጣታቸውን ብዙ ቅዱሳን ተናግረዋል። የብህንሳው ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስ፣ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምና ኢትዮጵያዊው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ክብሯን ገናንነቷን በስፋት ተናግረዋል፣ አመስግነዋታል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት።

ጌታችን አምላካችን ኢየሱ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሳ፤ በእርሷም የመለኮትና የስጋ ፍጹም ተዋህዶ ተፈጸመ፡፡ የማይወሰነውን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኗ ወሰነችው፡፡ ከዓለም በፊት ከአብ ያለእናት እንደተወለደ፣ ከእርሷ ደግሞ ድህረ ዓለም ያለ አባት ተወለደ፡፡ አምላክ እኛን ለማዳን ሰው ሆነ፣ ሰው አምላክ ሆነ ስንል በተዋህዶ ነውና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አማላክ ትባላለች፡፡ እመቤታችን በሀሳብም በሥጋም ዘላለማዊት ድንግል ናት። በሀሳቧ በህሊናዋ ከአምላክ ህግና ሀሳብ በስተቀር ስጋዊ ሀሳብ ፈጽሞ ኖሮ አይውቅምና ከሰው ወገን ተለይታ የህሊና ድንግልና አላት፡፡

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች መሆኗን በመመስከር ይህን የህሊና ድንግልና ያስረዳናል። መልአኩም ልጅ ትወልጃለሽ ብሎ ሲያበስራት “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል” ብላ መናገሯ “ስለ ወንድ ፈጽሞ አስቤ አላውቅም” ማለቷ ነውና የህሊና ወይም የሀሳብ ድንግልናዋን ያስረዳናል። ከመፅነሷ በፊት፤ በፀነሰች ጊዜ፤ ከፀነሰች በኋላ፤ ከመውለዷ በፊት፤ በወለደችም ጊዜ፤ ከወለደች በኋላ ድንግል ናት፡፡ ገዳማውያን ይህን ክብሯንና አማላጅነቷን አምነው ዘወትር አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡ 

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ 

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921
3,7600015
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 19:13

የእለቱ የውጭ አበይት ዜናዎች ፦

✅የስፔኑ  ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ በኢራን ጦርነት ምክንያት የአውሮፓ ሀገራት ከ100 ቢሊዮን ዩሮ በላይ በኪሳራ ማጣታቸውን ተናገሩ።

✅ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈፀመችው ጥቃት 8 ሰዎች ተገደሉ።

✅የኬንያ የጤና ሚኒስቴር በሃገሪቱ በኢቦላ የተያዘ 3ኛ ሰው መገኘቱን አረጋገጠ።

✅የየመኑ ሁቲ ታይዝ በተባለችው ከተማ በፈፀመው ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ።

✅ፕሬዚዳንት ትራምፕ  የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን ኬቲ ዛካሪያን አሰናበቱ።
3,8300010
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 19:09

ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!

መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ🙏

በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ ትጸንሻለሽ፤ አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል” አላት። ሴቲቱም ለባልዋ የሆነውን ሁሉ ነገረችው፡፡ ማኑሄም የተላከው ሰው ዳግመኛ ወደኛ ይምጣ፤ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም።

ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ባልዋንም ጠራችው። ማኑሄም “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? አለው። መልአኩም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው፡፡ መልአኩ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” ብሎ መለሰለት። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው።

መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም በግምባራቸው በምድር ተደፉ። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ሶምሶን ከተወለደ በኋላም የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። ይህ ሶምሶንና ወላጆቹን የረዳው ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

ታላቁ አለቃ ቅዱስ  ሚካኤል ዛሬም ገዳማውያንን በተጋድሏቸው ሁሉ እየተራዳ አብሯቸው ይኖራል፡፡ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ትተው ወጥተዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
3,8800017
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 17:49

Photo
ውሸት ነው‼️

በማኅበራዊ ሚዲያ የተሠራጨው የሐሰት ወሬ ውሸት መሆኑ ተረጋገጠ፡- አቶ ለማ በሰላም በሕይወት ይገኛሉ!

በዛሬው እለት በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ "ለዓመታት ፍቅረኛውን ሲጠብቅ የነበረው አቶ ለማ ሕይወቱ አልፏል" በሚል በሰፊው ተዘዋውሮ የነበረው መረጃ ፍጹም ሐሰተኛ መሆኑ ተገለጸ።

እንደ ብርሃኑ ዘ ሸገር መረጃ እና ማስተባበያ ከሆነ፤ አቶ ለማ በሰላም በጤና ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ አሁን ላይ በአንድ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለቀቀው የሞት ወሬ መሰረት የሌለው እና የተሳሳተ መረጃ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

የሐሰት ወሬ አቀናባሪዎችና አሰራጪዎች ትክክለኛውን ሁኔታ ከመረመረ ይልቅ ለግል ትኩረት ሲሉ የሚለቁት እንዲህ ዓይነት መረጃዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ስጋትና ግራ መጋባትን የሚፈጥሩ በመሆናቸው ተቀባይነት የሌላቸው መሆናቸው ተመልክቷል።

የሚዲያ ባለሙያዎችና ዜጎች ማንኛውንም መረጃ ከማጋራታቸው በፊት ከታመኑ ምንጮች ማረጋገጥ እንደሚገባቸው ተሳስቧል። አቶ ለማ በልዩ ጽናቱ የሚታወቅበት ማህበራዊ ታሪኩ እንዳለ ሆኖ፣ በአሁኑ ሰዓት በጤና እና በደህና እንደሚገኝ በድጋሚ ተረጋግጧል።
ጉርሻ
4,2300025
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 15:27

#ሩሲያ በ #ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት ፈቃደኛ መሆኗን ገለጸች‼️

ሩሲያ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት ለማርገብ በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል የሚደረገውን ውይይት ለማመቻቸት ፈቃደኛ መሆኗን ገለጸች። የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መበላሸት ለሞስኮ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑንም አስታውቃለች።

የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር አሊሞቭ እንደተናገሩት፤ ሞስኮ ሁለቱም ሀገራት ከግጭት ራስን የመቆጠብ እርምጃዎችን እንዲወስዱ፣ የእርስ በእርስ እምነትን የሚያጠናክሩ አሰራሮችን እንዲከተሉ እና ልዩነቶቻቸውን በውይይት ለመፍታት እንዲጥሩ ጥሪ አቅርባለች።

«ሁለቱም ወገኖች ፍላጎት ካላቸው፣ በሞስኮ በሚካሄደው ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤን ጨምሮ በተወካዮቻቸው መካከል ግንኙነቶችን ለማደራጀት እና አወዛጋቢ ጉዳዮች ላይ የጋራ መፍትሔዎችን ለማግኘት የሚያስችል የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት ዝግጁ ነን» ሲሉ አሌክሳንደር ተናግረዋል።
አስ
4,2500010
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 15:13

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት እና ምልጃዋ አይለየን🙏

በ325 ዓ.ም በጉባኤ ኒቂያ በነበረው የሲኖዶስ ውይይት ላይ በአደባባይ ተከራክረው ከሐዲያንን ካሳፈሩ 318 ሊቃውንት አንዱ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ነበረ።
የጌታችንን የመድኅኒታችንን መለኮታዊ ባህርይ ለሚጠራጠሩ አርዮሳውያንና በተዋሕዶ ሰው ሆኖ መክበሩን ለሚክዱ ቅዱስ ኤጲፋኒዮስ ስለ ተዋሕዶ ምሥጢርና ቅድስት ድንግል ማርያም የመለኮት እናት ስለመሆኗ ሲያስተምር “ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውና አምላክ በተዋሕዶ የከበረ ነው፡፡ በአምላክነቱ መለኮታዊ ባሕርይ ቢኖረውም እንደ ሰውነቱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር ተፀንሶ በድንግልና ተወልዷል። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ በትንቢቱ 7፣14 እንደጻፈው “እግዚአብሔር ምልክት ይሰጠናል ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፡፡ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ እርሱም ድንቅ መካር ኃያል የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።” በመሆኑም እመቤታችን የአምላክ እናት የእግዚአብሔር እናት ትባላለች ።

በሉቃስ ወንጌል ላይ ማርያም ነገርን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ስለነበር ከቅዱሳን የከበረች ከመላዕክትም የበለጠች እንደነበር አያውቅም ነበር። በሌላው ጌታን በፀነሰች ጊዜ ገጽዋ ይለዋወጥ ነበር ይህንንም ሲያይ ዮሴፍ ጻድቅም ስለነበር ሳይገልጣት ተዋት። አበው እንዳስተማሩን እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ፣ በተዋሕዶ ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣልና። ድንግል ማርያም ጌታን ከመፅነሷ በፊት በፀነሰች ጊዜ ከፀነሰችም በኋላ ድንግል ናት። እንዲሁም ከመውለዷ በፊት በወለደችም ጊዜ ከወለደችም በኋላ ድንግል ናት። ይህንንም እግዚአብሔር ስለገለጸለት ከአበይት ነቢያት መካከል አንዱ ቅዱስ ሕዝቅኤል በምዕራፍ 44÷1-4 “ወደ ምስራቅ ወደሚመለከተው በር አመጣኝ ይህ በርም ዝግ ነበር፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ለዘላለም ዝግ ሆኖ ይኖራል።” አለኝ ይላል፡፡

ምስራቅ ያላት ድንግል ማርያምን ነው ፀሐይ ከምስራቅ እንዲወጣ ጨለማውንም ዓለም ብርሃን እንዲያደርግ፤ ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስም ከአማናዊት ምስራቅ ከድንግል ማርያም ተልወዶ በኅጢያት ለጨለመው ዓለም የጽድቅ ብርሃን ሆኖ ተገልጧልና፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም በመኃልዬ መኃልይ 4÷12 "እህቴ ሙሽራዬ ሆይ የተዘጋ ገነት የታተመ ፈሳሽ ነሽ" በማለት ስለዘላለማዊ ድንግልናዋ ጽፏል። በቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ 4÷4 እንደጻፈው የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ያለ ዘርአ ብእሲ ወይም ያለ ወንድ ዘር ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአምላክ እናት የተወለደውን አንድያ ልጁን ላከልን፣ እርሱም የእኛን ባህርይም ባህርይ አድርጎ ተወለደ። ልጆችም ስለሆንን እግዚአብሔር አባ አባት ብለን የምንጠራበት የልጅነት መንፈስ ሰጠን፡፡ እመቤታችንም በሕቱም ድንግልና ይህን ጌታ ወለደችልን፡፡ ገዳማውያንም ይህችን እናት ዘወትር አማልጅን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡ ከበረከቱ እንካፈል።

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ 

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921
4,2700020

Showing 30 of 100 posts

Avaliação

Login necessário

Frequently Asked Questions

Sobre o que é o canal Telegram ኢትዮ መረጃ - NEWS?+

ኢትዮ መረጃ - NEWS (@ethio_mereja_news) é um canal Telegram listado em Notícias e Jornais no tgdio. Ranking, avaliações, reviews e posts recentes para decidir antes de assinar. Atualmente lista cerca de 45.817 inscritos no tgdio.

Como entrar em ኢትዮ መረጃ - NEWS (@ethio_mereja_news) no Telegram?+

Abra o perfil no tgdio e use Join / Open in Telegram para assinar @ethio_mereja_news de graça.

ኢትዮ መረጃ - NEWS é um bom canal de Notícias e Jornais?+

No tgdio você pode ver avaliação, reviews, ranking e posts de ኢትዮ መረጃ - NEWS antes de entrar. Atualmente lista cerca de 45.817 inscritos no tgdio. Compare com canais similares de Notícias e Jornais.

Onde ver estatísticas e posts de ኢትዮ መረጃ - NEWS?+

No tgdio, abra @ethio_mereja_news para stats de inscritos, ranking, avaliações e posts. Use Stats para gráficos.