1/2ስለ ፕሬዚዳንትነት ሥልጣን፦ በግንቦት 2018 ዓ.ም. በህወሓት የሚመራው የትግራይ ምክር ቤት የትግራይ መንግሥት ፕሬዚዳንት አድርጎ እንደመረጣቸው ዶ/ር ደብረጽዮን ገልጸዋል።
ስለ ጦርነቱ አቋም፦ የትግራይ ሠራዊትና አጋር ኃይሎች የመከላከል ውጊያ እያካሄዱ እና ጥሩ ድሎች እያስመዘገቡ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ጦርነቱ በቴክኖሎጂ፣ በድሮን ወይም በባንዳዎች ብዛት ሳይሆን በሕዝብ ተሳትፎ የሚወሰን መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
የሰፉ ጥሪዎች እና ዛቻ፦ ትግሉ ከበርካታ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በመሆን የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመው፤ «ትግራይ የገባው የመንግሥት ኃይል አይወጣም፣ እዚሁ ይቀበራል፤ ጦርነቱን በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች እናደርገዋለን» የሚል ንግግር ማድረጋቸው ተመላክቷል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱትም ዶክተሩ ይህንን መግለጫ የሰጡት ከኤርትራ ሰንዓፌ ሆነው ነው።
@Esat_tv1
@Esat_tv1








