ኢትዮ መረጃ - NEWS Telegram channel photo

ኢትዮ መረጃ - NEWS

@ethio_mereja_newsPublic Channel

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት ማክበር ባትችል አታዋርዳት ማራመድ ባትችል አታዘግያት መጠበቅ ባትችል አትበትናት። ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም። ለአስታየት @ethio_merjabot @B_promotor

3.9k

Last views

45.8k (45,817 subscribers)
Membros
—
Rating
80
Total Posts
Oct 20, 2026, 10:12 PM
Atualizado
Mar 31, 2026
Created
Stats

Você está vendo conteúdo em português. Para ver conteúdo em outros idiomas, mude o idioma do site.

Channel Information

Channel Information
Channel Nameኢትዮ መረጃ - NEWS
Username@ethio_mereja_news
CategoryNotícias e Jornais
Languageportuguês
CountryBrasil
Membros45,817
Channel TypePublic Channel
Created31 de mar. de 2026
Last Updated20 de out. de 2026 • há 18 horas
StatusActive

Classificação

Classificação Global
#107202-4313
Classificação por Idioma
#2233-63
Classificação por Categoria
#1009-41

Crescimento de Participantes

Total: 45.8K30 Days growth: +6871.5%
09/2109/2610/0110/0610/1110/1610/20
Crescimento de Participantes - 30 Days
DateSubscribers
21:09:202645,130
22:09:202645,130
23:09:202645,130
24:09:202645,130
25:09:202645,130
26:09:202645,130
27:09:202645,130
28:09:202645,130
29:09:202645,130
30:09:202645,130
01:10:202645,130
02:10:202645,130
03:10:202645,130
04:10:202645,130
05:10:202645,130
06:10:202645,130
07:10:202645,130
08:10:202645,130
09:10:202645,130
10:10:202645,130
11:10:202645,130
12:10:202645,130
13:10:202646,068
14:10:202646,068
15:10:202646,068
16:10:202646,068
17:10:202646,068
18:10:202646,068
19:10:202646,068
20:10:202645,817
Crescimento de Participantes - Weekly
DateSubscribers
Week of 30:03:202649,202
Week of 06:04:202649,102
Week of 13:04:202648,889
Week of 20:04:202648,643
Week of 27:04:202648,643
Week of 04:05:202648,643
Week of 11:05:202648,113
Week of 18:05:202648,113
Week of 25:05:202648,113
Week of 01:06:202647,276
Week of 08:06:202647,276
Week of 15:06:202646,988
Week of 22:06:202646,741
Week of 29:06:202646,741
Week of 06:07:202646,741
Week of 13:07:202646,327
Week of 20:07:202646,127
Week of 27:07:202645,979
Week of 03:08:202645,979
Week of 10:08:202645,979
Week of 17:08:202645,665
Week of 24:08:202645,476
Week of 31:08:202645,296
Week of 07:09:202645,296
Week of 14:09:202645,130
Week of 21:09:202645,130
Week of 28:09:202645,130
Week of 05:10:202645,130
Week of 12:10:202646,068
Week of 19:10:202645,817
Crescimento de Participantes - Monthly
DateSubscribers
March 202649,312
April 202648,643
May 202648,113
June 202646,741
July 202646,127
August 202645,476
September 202645,130
October 202645,817
Crescimento de Participantes - Yearly
DateSubscribers
202645,817

Top 10 posts

Most viewed posts from this channel

By views
  1. #1ማልሁልሽ ቃል ኪዳንም ገባሁልሽ አላት🙏7.2K
  2. #2በኢራንና እስራኤል መካከል ያለው ውጥረት አይሏል‼7.2K
  3. #3የተሳፈሩበት ዶልፊን ተሽከርካሪ ነዳጅ በመጨረሱ ምክንያት ሴኖትራክ ላይ የተሳፈሩ 8 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወ7.2K
  4. #4አለምን ጨለማ አደርጋለሁ-ኢራን‼️7.1K
  5. #5ሽሮ ሜዳ በፖሊስ የተገደለው ወጣት‼️6.9K
  6. #6Post #245256.8K
  7. #7ኢማኑኤል ማክሮን ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ሊመጡ ነው6.8K
  8. #8እንኳን ለልደታ ማርያም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!6.8K
  9. #9ፓኪስታን በኢራን ጦርነት ዙሪያ የሳዑዲ፣ የቱርክ እና የግብፅ ከፍተኛ ዲፕሎማቶችን ለስብሰባ ጠርታለች6.8K
  10. #10ሰበር‼️6.5K

Últimos Posts

ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 22:00

መኪና መውረስ ተጀመረ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በክልሎች በወጡ የንግድ ፈቃዶች ተጠቅመው በመዲናዋ ውስጥ ያለ ፈቃድ እና በየመንገዱ ዳር ተሽከርካሪዎችን ለሽያጭ የሚያቀርቡ አስመጪዎች ላይ ከውይይትና ከማስጠንቀቂያ ያለፈ ቀጥተኛ የህግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ ጀመረ። በዚህም መሰረት ቢሮው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡ ፍርድ ቤት አካባቢ በህዝብ መንገድ ዳር ያለ ከተማ አስተዳደሩ እውቅና ለሽያጭ ቀርበው የነበሩ ሶስት ቢዋይዲ እና አንድ ቻንጋን የተሰኙ አዳዲስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። ይህ እርምጃ በዋናነት ያነጣጠረው የንግድ ፈቃዳቸውን ከአዲስ አበባ ውጪ በሆኑ ክልሎች አውጥተው፣ የሽያጭ ስራቸውን ግን በመዲናዋ ውስጥ በማከናወን የከተማዋን የታክስ ገቢ በሚያሳጡ ነጋዴዎች ላይ ነው። የገቢዎች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ አንድ አስመጪ በድንበር ላይ የጉምሩክ ቀረጥ መክፈሉ ወይም የማስመጣት ፈቃድ መያዙ ብቻውን በአዲስ አበባ ውስጥ የችርቻሮ ሽያጭ ለማከናወን ህጋዊ አያደርገውም። በመሆኑም በክልል ፈቃድ የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎች ወደ መዲናዋ የታክስ መረብ መግባት እና ከመንገድ ዳር የድለላ ሽያጭ ወጥተው እውቅና ባለው የመሸጫ ስፍራ ብቻ መስራት ይጠበቅባቸዋል።

ይህ የከተማ አስተዳደሩ እርምጃ በኢትዮጵያ የታክስ አስተዳደር እና በታዳጊው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ገበያ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት የሚሹ መሰረታዊ ጉዳዮችን ያስነሳል። በመጀመሪያ ደረጃ የሚጠቀሰው በክልሎች እና በፌዴራል ከተሞች መካከል ያለው የታክስ ወሰን ውዝግብ ነው። ነጋዴዎች አነስተኛ የታክስ ተመን ወይም ላላ ያለ ቁጥጥር ባለባቸው ክልሎች የንግድ ፈቃድ አውጥተው፣ ትልቁ ገበያና ሸማች ወዳለባት አዲስ አበባ መጥተው መስራታቸው በከተማ አስተዳደሩ የገቢ አሰባሰብ ላይ ከፍተኛ ክፍተት ፈጥሯል። ይህ ድርጊት በክልሎች እና በመዲናዋ መካከል የተናበበ የንግድ ምዝገባ እና የታክስ ክትትል ስርዓት አለመኖሩን የሚያጋልጥ ሲሆን፣ አዲስ አበባ የምታቀርበውን መሰረተ-ልማት እየተጠቀሙ ግብር ግን ለሌላ ክልል የሚከፍሉ ተቋማትን ለመግታት የተወሰደ ስልታዊ እርምጃ መሆኑን ያሳያል።

ከዚህም ባሻገር ጉዳዩ ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ገበያ መስፋፋት እና ከቁጥጥር ክፍተት ጋር በቀጥታ ይያያዛል። የፌዴራል መንግስቱ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ማገዱን ተከትሎ፣ የቻይና የኤሌክትሪክ መኪኖች የመዲናዋን ገበያ በፍጥነት ተቆጣጥረውታል። መንግስት የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማበረታታት በጉምሩክ ቀረጥ ላይ ማበረታቻ ቢሰጥም፣ የሀገር ውስጥ የሽያጭ ሰንሰለቱ ግን በህገ-ወጥ ደላሎች እና መንገድ ዳር በሚደረግ ኢ-መደበኛ ንግድ የተዋጠ ሆኗል። በመሆኑም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የወሰደው እርምጃ፣ መንግስት በጉምሩክ በኩል ያጣውን ገቢ በሀገር ውስጥ የሽያጭ እና የትርፍ ግብር ለማካካስ መቁረጡን በግልጽ ያመላክታል።

ይሁን እንጂ በህግ ማስከበር ሂደቱ ውስጥ የሚታየው የመረጃ ግልጽነት እጥረት የራሱን ጥያቄዎች ማስነሳቱ አልቀረም። ቢሮው መኪኖቹን ከመውረሱ በፊት ተደጋጋሚ ውይይትና ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ቢገልጽም፣ እስካሁን በዚህ የህግ ክፍተት ምን ያህል ገቢ እንደታጣ፣ ምን ያህል ነጋዴዎች በክልል ፈቃድ እንደሚሰሩ እንዲሁም የተያዙት መኪኖች ዋጋና የሚጣልባቸው የቅጣት መጠን ምን ያህል እንደሆነ ይፋ አለማድረጉ የአሰራር ግልጽነት ጥያቄን ያስነሳል። በቀጣይ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተጠናክሮ ይቀጥላል የተባለው ይህ የጋራ የህግ ማስከበር ዘመቻ፣ የመኪና ገበያውን ወደ ህጋዊ ስርዓት ከማስገባት ባለፈ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተሽከርካሪዎች የመሸጫ ዋጋ ላይ ተጨማሪ ጭማሪ ሊያስከትል እንደሚችል የዘርፉ ታዛቢዎች ይገምታሉ።
3,9400017
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 21:53

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏

ቤተክርስቲያናችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን ሁሉ በላይ በማለት ክብሯን ትገልጻለች። ኦርቶዶክሳዊያን ከሕጻንነታችን ጀምረን የእመቤታችንን ምስጋና እንማራለን፣ ሁልጊዜም በአባታችን ሆይ ጸሎት ጀምረን በመልኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ብለን ድንግል ማርያምን እናመሰግናታለን። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱሳን ሁሉ የምትመሰገን ናት። እርሷ ያላትን ክብር እንዴት እንደሚገልጹት ተጨንቀው በምን በምን እንመስልሻለን በማለት በሰው ህሊና የሚለካ ምሳሌ ማጣታቸውን ብዙ ቅዱሳን ተናግረዋል። የብህንሳው ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስ፣ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምና ኢትዮጵያዊው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ክብሯን ገናንነቷን በስፋት ተናግረዋል፣ አመስግነዋታል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት።

ጌታችን አምላካችን ኢየሱ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሳ፤ በእርሷም የመለኮትና የስጋ ፍጹም ተዋህዶ ተፈጸመ፡፡ የማይወሰነውን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኗ ወሰነችው፡፡ ከዓለም በፊት ከአብ ያለእናት እንደተወለደ፣ ከእርሷ ደግሞ ድህረ ዓለም ያለ አባት ተወለደ፡፡ አምላክ እኛን ለማዳን ሰው ሆነ፣ ሰው አምላክ ሆነ ስንል በተዋህዶ ነውና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አማላክ ትባላለች፡፡ እመቤታችን በሀሳብም በሥጋም ዘላለማዊት ድንግል ናት። በሀሳቧ በህሊናዋ ከአምላክ ህግና ሀሳብ በስተቀር ስጋዊ ሀሳብ ፈጽሞ ኖሮ አይውቅምና ከሰው ወገን ተለይታ የህሊና ድንግልና አላት፡፡

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች መሆኗን በመመስከር ይህን የህሊና ድንግልና ያስረዳናል። መልአኩም ልጅ ትወልጃለሽ ብሎ ሲያበስራት “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል” ብላ መናገሯ “ስለ ወንድ ፈጽሞ አስቤ አላውቅም” ማለቷ ነውና የህሊና ወይም የሀሳብ ድንግልናዋን ያስረዳናል። ከመፅነሷ በፊት፤ በፀነሰች ጊዜ፤ ከፀነሰች በኋላ፤ ከመውለዷ በፊት፤ በወለደችም ጊዜ፤ ከወለደች በኋላ ድንግል ናት፡፡ ገዳማውያን ይህን ክብሯንና አማላጅነቷን አምነው ዘወትር አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡ 

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ 

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921
3,7600015
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 19:13

የእለቱ የውጭ አበይት ዜናዎች ፦

✅የስፔኑ  ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ በኢራን ጦርነት ምክንያት የአውሮፓ ሀገራት ከ100 ቢሊዮን ዩሮ በላይ በኪሳራ ማጣታቸውን ተናገሩ።

✅ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈፀመችው ጥቃት 8 ሰዎች ተገደሉ።

✅የኬንያ የጤና ሚኒስቴር በሃገሪቱ በኢቦላ የተያዘ 3ኛ ሰው መገኘቱን አረጋገጠ።

✅የየመኑ ሁቲ ታይዝ በተባለችው ከተማ በፈፀመው ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ።

✅ፕሬዚዳንት ትራምፕ  የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን ኬቲ ዛካሪያን አሰናበቱ።
3,8300010
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 19:09

ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!

መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ🙏

በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ ትጸንሻለሽ፤ አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል” አላት። ሴቲቱም ለባልዋ የሆነውን ሁሉ ነገረችው፡፡ ማኑሄም የተላከው ሰው ዳግመኛ ወደኛ ይምጣ፤ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም።

ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ባልዋንም ጠራችው። ማኑሄም “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? አለው። መልአኩም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው፡፡ መልአኩ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” ብሎ መለሰለት። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው።

መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም በግምባራቸው በምድር ተደፉ። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ሶምሶን ከተወለደ በኋላም የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። ይህ ሶምሶንና ወላጆቹን የረዳው ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

ታላቁ አለቃ ቅዱስ  ሚካኤል ዛሬም ገዳማውያንን በተጋድሏቸው ሁሉ እየተራዳ አብሯቸው ይኖራል፡፡ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ትተው ወጥተዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
3,8800017
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 17:49

Photo
ውሸት ነው‼️

በማኅበራዊ ሚዲያ የተሠራጨው የሐሰት ወሬ ውሸት መሆኑ ተረጋገጠ፡- አቶ ለማ በሰላም በሕይወት ይገኛሉ!

በዛሬው እለት በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ "ለዓመታት ፍቅረኛውን ሲጠብቅ የነበረው አቶ ለማ ሕይወቱ አልፏል" በሚል በሰፊው ተዘዋውሮ የነበረው መረጃ ፍጹም ሐሰተኛ መሆኑ ተገለጸ።

እንደ ብርሃኑ ዘ ሸገር መረጃ እና ማስተባበያ ከሆነ፤ አቶ ለማ በሰላም በጤና ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ አሁን ላይ በአንድ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለቀቀው የሞት ወሬ መሰረት የሌለው እና የተሳሳተ መረጃ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

የሐሰት ወሬ አቀናባሪዎችና አሰራጪዎች ትክክለኛውን ሁኔታ ከመረመረ ይልቅ ለግል ትኩረት ሲሉ የሚለቁት እንዲህ ዓይነት መረጃዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ስጋትና ግራ መጋባትን የሚፈጥሩ በመሆናቸው ተቀባይነት የሌላቸው መሆናቸው ተመልክቷል።

የሚዲያ ባለሙያዎችና ዜጎች ማንኛውንም መረጃ ከማጋራታቸው በፊት ከታመኑ ምንጮች ማረጋገጥ እንደሚገባቸው ተሳስቧል። አቶ ለማ በልዩ ጽናቱ የሚታወቅበት ማህበራዊ ታሪኩ እንዳለ ሆኖ፣ በአሁኑ ሰዓት በጤና እና በደህና እንደሚገኝ በድጋሚ ተረጋግጧል።
ጉርሻ
4,2300025
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 15:27

#ሩሲያ በ #ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት ፈቃደኛ መሆኗን ገለጸች‼️

ሩሲያ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት ለማርገብ በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል የሚደረገውን ውይይት ለማመቻቸት ፈቃደኛ መሆኗን ገለጸች። የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መበላሸት ለሞስኮ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑንም አስታውቃለች።

የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር አሊሞቭ እንደተናገሩት፤ ሞስኮ ሁለቱም ሀገራት ከግጭት ራስን የመቆጠብ እርምጃዎችን እንዲወስዱ፣ የእርስ በእርስ እምነትን የሚያጠናክሩ አሰራሮችን እንዲከተሉ እና ልዩነቶቻቸውን በውይይት ለመፍታት እንዲጥሩ ጥሪ አቅርባለች።

«ሁለቱም ወገኖች ፍላጎት ካላቸው፣ በሞስኮ በሚካሄደው ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤን ጨምሮ በተወካዮቻቸው መካከል ግንኙነቶችን ለማደራጀት እና አወዛጋቢ ጉዳዮች ላይ የጋራ መፍትሔዎችን ለማግኘት የሚያስችል የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት ዝግጁ ነን» ሲሉ አሌክሳንደር ተናግረዋል።
አስ
4,2500010
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 15:13

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት እና ምልጃዋ አይለየን🙏

በ325 ዓ.ም በጉባኤ ኒቂያ በነበረው የሲኖዶስ ውይይት ላይ በአደባባይ ተከራክረው ከሐዲያንን ካሳፈሩ 318 ሊቃውንት አንዱ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ነበረ።
የጌታችንን የመድኅኒታችንን መለኮታዊ ባህርይ ለሚጠራጠሩ አርዮሳውያንና በተዋሕዶ ሰው ሆኖ መክበሩን ለሚክዱ ቅዱስ ኤጲፋኒዮስ ስለ ተዋሕዶ ምሥጢርና ቅድስት ድንግል ማርያም የመለኮት እናት ስለመሆኗ ሲያስተምር “ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውና አምላክ በተዋሕዶ የከበረ ነው፡፡ በአምላክነቱ መለኮታዊ ባሕርይ ቢኖረውም እንደ ሰውነቱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር ተፀንሶ በድንግልና ተወልዷል። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ በትንቢቱ 7፣14 እንደጻፈው “እግዚአብሔር ምልክት ይሰጠናል ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፡፡ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ እርሱም ድንቅ መካር ኃያል የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።” በመሆኑም እመቤታችን የአምላክ እናት የእግዚአብሔር እናት ትባላለች ።

በሉቃስ ወንጌል ላይ ማርያም ነገርን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ስለነበር ከቅዱሳን የከበረች ከመላዕክትም የበለጠች እንደነበር አያውቅም ነበር። በሌላው ጌታን በፀነሰች ጊዜ ገጽዋ ይለዋወጥ ነበር ይህንንም ሲያይ ዮሴፍ ጻድቅም ስለነበር ሳይገልጣት ተዋት። አበው እንዳስተማሩን እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ፣ በተዋሕዶ ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣልና። ድንግል ማርያም ጌታን ከመፅነሷ በፊት በፀነሰች ጊዜ ከፀነሰችም በኋላ ድንግል ናት። እንዲሁም ከመውለዷ በፊት በወለደችም ጊዜ ከወለደችም በኋላ ድንግል ናት። ይህንንም እግዚአብሔር ስለገለጸለት ከአበይት ነቢያት መካከል አንዱ ቅዱስ ሕዝቅኤል በምዕራፍ 44÷1-4 “ወደ ምስራቅ ወደሚመለከተው በር አመጣኝ ይህ በርም ዝግ ነበር፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ለዘላለም ዝግ ሆኖ ይኖራል።” አለኝ ይላል፡፡

ምስራቅ ያላት ድንግል ማርያምን ነው ፀሐይ ከምስራቅ እንዲወጣ ጨለማውንም ዓለም ብርሃን እንዲያደርግ፤ ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስም ከአማናዊት ምስራቅ ከድንግል ማርያም ተልወዶ በኅጢያት ለጨለመው ዓለም የጽድቅ ብርሃን ሆኖ ተገልጧልና፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም በመኃልዬ መኃልይ 4÷12 "እህቴ ሙሽራዬ ሆይ የተዘጋ ገነት የታተመ ፈሳሽ ነሽ" በማለት ስለዘላለማዊ ድንግልናዋ ጽፏል። በቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ 4÷4 እንደጻፈው የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ያለ ዘርአ ብእሲ ወይም ያለ ወንድ ዘር ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአምላክ እናት የተወለደውን አንድያ ልጁን ላከልን፣ እርሱም የእኛን ባህርይም ባህርይ አድርጎ ተወለደ። ልጆችም ስለሆንን እግዚአብሔር አባ አባት ብለን የምንጠራበት የልጅነት መንፈስ ሰጠን፡፡ እመቤታችንም በሕቱም ድንግልና ይህን ጌታ ወለደችልን፡፡ ገዳማውያንም ይህችን እናት ዘወትር አማልጅን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡ ከበረከቱ እንካፈል።

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ 

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921
4,2700020
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 10:51

ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ በግዙፍ ኢኮኖሚ ለአምስት ዓመታት ይዛው የቆየችውን የአንደኝነት ደረጃ ለኬንያ አስረከበች።

የኢትዮጵያ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት ዋጋ 126 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የኬንያ  ግን ወደ 135 ቢሊዮን ከፍ ማለቱን የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሪፖርት ያመለክታል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ በግዙፍ ኢኮኖሚ ደረጃ ከ7ኛ ወደ 8ኛ ደረጃ ዝቅ ስትል፣ ኬንያ ባንጻሩ ከስምንተኛ ወደ ሰባተኛ ደረጃ ከፍ ብላለች።

ኢትዮጵያ የቀዳሚነት ደረጃዋን ለማስረከቧ ዋናው ምክንያት የምርት ማነስ ሳይኾን፣ የብር ምንዛሬ ዋጋ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ከዶላር አንጻር ማሽቆልቆሉ እንደኾነ ተገልጧል።

ከዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገት አንጻር፣ ኢትዮጵያ አሁንም በኬንያ ላይ ከፍተኛ ብልጫ አላት።


@Ankuar_mereja
@Ankuar_mereja
4,1100025
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

17 de out. de 2026, 10:11

አጋዝእተ ዓለም ሥላሴ ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልሉን፤ የልባችንን መልካም መሻትም ይሙሉልን🙏

የሥላሴን አኗኗር በስጋዊ ስሌት የማንመረምረውም መንፈሳዊ በመሆኑ ነው፡፡ የምሥጢረ ሥላሴን ትምህርት ስንማር ከሂሳብ ቀመር ሕግ አስተሳሰብ ነጻ መሆን ያሻል። ምክንያቱም መንፈሳዊዉ ጥበብ ሥጋዊዉን ጥበብ ወይም ፍልስፍና ይመረምረዋል እንጅ መንፈሳዊ ጥበብና ምሥጢር በዓለማዊ ዕውቀትና ምርምር ሊደረስበት አይቻልምና የሃይማኖት ነገር ቁሳዊ ሳይሆን መንፈሳዊና በሃይማኖት ሆኖ በመንፈሳዊነት የሚታወቅና የሚታመን ነው። ሥላሴ፣ ሠለሰ ሶስት አደረገ፤ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን፤ ሥላሴ ማለት ሶስትነት ማለት ነው። በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን፣ ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ አምላክ ቅድስት ሥላሴ፡፡ ቅድስት ሥላሴ ስማቸው ከአካላቸው፣ አካላቸው ከስማቸው ሳይቀድም ከዓለም በፊት የነበረ ነው እንጂ ኋላ የተገኘ አይደለም፡፡

ቅድምናቸው ዘመኑን ቢወስነው እንጂ ዘመኑ ቅድምናቸውን አይወስነውምና፡፡ የሥላሴ አንድነት በባህርይ፣ በህልውና፣ በፈቃድ፣ በሥልጣን፣ በመፍጠር በመሳሰሉት ነው፡፡ ሥላሴ የሚለው ስም የአንድነትና የሦስትነት ስም ነውና በስም፣ በግብርና በአካል ሦስት እንላለን፡፡ የሰው ነፍስ የቅድስት ሥላሴ ምሳሌ ናት፡፡ ይኸውም አብ በልብ፣ ወልድ በቃል፣ መንፈስ ቅዱስ በእስትፋስ ይመሰላሉ፡፡ በእግዚአብሔርነቱ፤ ልብ፣ ቃልና ሕይወት አለ። ነፍስ ሶስት ባህርያት ቢኖሯትም አንድ እንደምትባል እግዚአብሔርም ሶስት ስም፤ ሶስት ግብር፤ ሶስት አካል፤ ቢኖረውም አንድ አምላክ እንጅ ሶስት አማልክት አይባልም፡፡

ለአብ፣ ለወልድ፣ ለመንፈሰ ቅዱስ ለየራሳቸው ፍፁም ገጽ፣ ፍፁም መልክ፣ ፍፁም አካል፣ አላቸው። የፍጡራን አካል የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣ የሚመጠን፤ የሚወሰን፣ ሲሆን የሥላሴ አካል ግን፤ የማይታይ፣ በእጅ የማይዳሰስ፣ በቦታ የማይወሰን፣ በሁሉም ምሉዕ ነው። የቅድስት ሥላሴ ምሕረትና ቸርነት አይለየን፡፡ ገዳማውያኑ ዓለምን ትተው ሲመንኑ ይህን ምሕረትና ቸርነት ተስፋ አድርገው ስጋዊውን ክብር ንቀው ነው፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡ 

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
4,2500027
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

16 de out. de 2026, 22:01

በእነዮሐንስ ቧያሌው የክስ መዝገብ የሚገኙና መንግስት ያቀረበው የይቅርታ ሰነድ ላይ ለመፈረም ፈቃደኛ ያልሆኑ አራት ተከሳሾች ክሳቸውን እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማሳለፉን ጠበቃቸው ለአዲስ ማለዳ ገለጹ

በእነ ዮሐንስ ቧያሌው የክስ መዝገብ ውስጥ 52 ውስጥ 36ቱ በሌሉበት፣ 16ቱ በችሎት ተገኝተው ሲከታተሉ ነበር። ከ16ቱ ውስጥ 12ቱ በመንግስት የቀረበውን የይቅርታ ሰነድ በመፈረም የተፈቱ ናቸው።

በዚሁ የክስ መዝገብ ፍርድ ቤቱ እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው 4 ተከሶሾች፤ ዮሐንስ ቧያሌው፣ ዶክተር ዘሪሁን ባህሪው፣ ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ እና ደሳለኝ እጅጉ ናቸው።

የ2019 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የፌደራሉ መንግስት በኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ጥረት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከእስር እንዲፈቱ የተደረገ ቢሆንም 30ዎቹ ግን ለመፈረም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ከእስር አልተለቀቁም፡፡

በእነ ዮሐንስ ቧያሌው የክስ መዝገብ ሥር ፊርማ ለመፈረም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በእስር ላይ የሚገኙ አራት ተከሳሾች ክሳቸውን እንዲከላከሉ የከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑን ጠበቃቸው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

እነዚህ አራት ተከሳሾች ክሳቸውን በፍርድ ቤት የመከላከል መብታቸውን ለመጠቀም ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን፣ በዛሬው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎትም ይግባኛቸው ተቀባይነት ማግኘቱን ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ገልጸዋል።

በዚሁ መሠረት አራቱ ተከሳሾች በቀረበባቸው ክስ ላይ መከላከያቸውን እንዲያቀርቡ መወሰኑን ጠበቃቸው አስረድተዋል።

ውሳኔው ተከሳሾቹ ክሳቸውን የመከላከል እድል እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ የሚቀጥለው የሕግ ሂደት ምን እንደሚሆን በቀጣይ የፍርድ ቤት ሂደቶች የሚታይ ይሆናል።   አንኳር መረጃ
5,0600012
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

16 de out. de 2026, 21:44

ቅዱስ ገብርኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!

በቅዱስ መጽሐፍ ስማቸው ከገነኑ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ የሚጠራው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ መልአኩ ገብርኤል በቅድስናው ቅዱስ ይባላል፡፡ የዙፋን መልእክተኛ ነውና መልአክ ወይም መልእክተኛ ይባላል፡፡ የሠራዊት አዛዥ ነውና ሊቀ መላእክት ይባላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል አብሳሬ ትስብዕት ነው፡፡ እመቤታችን አምላክን እንደምትወልድ ታላቁን የምሥራች ይዞ የደረሰው እርሱ ነው፡፡ የሰው ልጆችን መዳን ታላቁን የምሥራች ይዞ በመምጣቱና በሀዲስ ኪዳን ስሙ ተደጋግሞ በመጠቀሱ መጋቤ ሐዲስ ይባላል፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። በሉቃስ 1÷19 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የተሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ነው፡፡ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ መጥምቁ ዮሐንስን እንደሚወልድ የዘመናትን የጸሎት ምላሽ ይዞ የመጣ፣ በባቢሎን ምርኮ ሆኖ ስለሕዝቡ የሚያለቅሰውን የነቢዩ ዳንኤልን የጸሎት መልስ ይዞ የመጣው፣ ራእዩንም ያብራራለት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን በመስጠት ያሉ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡ ይህም ደግሞ እውነት ነው፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚወዱት የሚሆን ጠባቂ በዙሪያቸው ያቆማል።

በዕምነታቸው የጸኑት ሦስቱ የባቢሎን ሕጻናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል በንጉሡ ፊት ቆመው “ንጉሥ ሆይ እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፡፡ ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድ ዕወቅ” አሉት፡፡ ወደ እቶን እሳት ተጣሉ፡፡ ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው፡፡ ናቡከደነጾርም ተደንቆ በእሳቱ ላይ ሦስት ሰዎች ሰዎች ጥለን ነበር አሁን ግን አራት ሰዎች አያለሁ፤ የአራተኛውም መልክ የአምላክን መልክ ይመስላል አለ፡፡ ይህ የአምላክን መልክ ይመስላ የተባለው  ቅዱስ ገብርኤልን ገዳማውያን በመንፈሳዊ ውጊያቸው ሁሉ ይረዳቸዋል፡፡ የጸሎታቸው በረከት ተካፋይ እንድንሆን በዓታቸውን እናጽና ገዳማቸውን እንደግፍ፡፡   

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ 

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921
4,6400027
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

16 de out. de 2026, 20:11

ዜና: #ካናዳ በ #ኢትዮጵያና #ኤርትራ ውጥረት በተባባሰበት ወቅት ጠብአጫሪ ቃላትን እንዲቀንሱ ስትጠይቅ፣ #ዩናይትድ_ኪንግደም የድንበር ጥሰትን እንደምትቃወም ገለጸች

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ፣ ካናዳ ሁለቱም ወገኖች ጠብአጫሪ የሆኑ ድንበር ተሻጋሪ የቃላት ጦርነቶችን እንዲያቆሙ እና ወደ ዲፕሎማሲያዊ ውይይት እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበች፤ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በበኩሉ የድንበር ጥሰቶችን እንደሚቃወም አስታውቆ መቆጠብ እና አዲስ ውይይት እንዲደረግ አሳሰበ።

ካናዳ በኢትዮጵያ የቀጠለው ግጭት እና ወደ ቀጣናው የመባባስ አደጋ እንዳሳሰባት ገልጻ፣ ሁሉም ወገኖች ከፍተኛ መቆጠብ እንዲያደርጉ እና ተጨማሪ ውጥረት አባባሽ ከሆኑ እርምጃዎች እንዲቆጠቡ ጠይቃለች።

የካናዳ መግለጫ «ካናዳ በኢትዮጵያ እየቀጠለ ያለውን ግጭት በቅርበት እየተከታተለች የምትገኝ ሲሆን፣ ወደ ቀጣናው የመባባስ አደጋው ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮባታል» ብሏል።
4,6100022
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

16 de out. de 2026, 20:08

የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ልመናችንን ይስማን፤ምልጃ እና ረድኤቱም አይለየን🙏

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል፡፡ ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አምነው ለሚጠሩት ረዳት ነው፡፡ በመዝሙር 33÷7 እደተጻፈው ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፡፡ እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል እንደተናገረው ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው፡፡ ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ ይህንን ድንቅ ተአምር መስከረም ዘጠኝ ቀን መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን ትመሰክራለች፡፡ በቀድሞው የሮም ግዛት 'ሩፍምያ' የምትባል ከተማ ነበረች፡፡

ይህች ከተማ በእምነታቸው ጠንካሮች የሆኑ ጥቂት ክርስቲያኖችና በርካታ ኢአማንያን ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት፡፡ በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ፍጹም የእምነት ሰው ነበር፡፡ በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረግ ስለነበር ተበለጥን የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ “ዮናናውያን”ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ፡፡ በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን መከሩና ወሰኑ፡፡ በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ አለ፡፡ በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር፡፡ ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን መንገድ ዘግተው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት ከቀናት በኋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ፡፡
ወንዙ ትልቅ ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ፡፡ በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ ቤተ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በስተቀር ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ሲወጣ ወንዙ እየደነፋ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው፡፡ ከደቂቃዎች በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ እንደሚሆን የተረዳው መጋቢ በታላቅ ድንግጤ ውስጥ ወደቀ፡፡ እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ በመላዕክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ምስለ ስዕል ፊት ወድቆ ተማጸነ፡፡ ታላቁ ወንዝ ቤተ ክርስቲያኑን ጠርጎ የሚወወስደው ከሆነም የሚሆነውን ነገር ለመቀበልና ከዚያም ላለመውጣትም ወሰነ፡፡ ትንሽ ቆይቶ በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ፡፡ በዚህ ጊዜ የመላዕክት ሁሉ አለቃቸው ለጠራውም ፈጥኖ የሚደርሰው ቅዱስ ሚካኤል በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ፡፡

መጋቢውንም "ጽና አትፍራ፣ እኔ ካንተ ጋር ነኝና" ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት፡፡ በዚያች ቅጽበትም ትልቅ ሸለቆ ተፈጠረ፡፡ በአስፈሪ ሁኔታ ሲመጣ የነበረው ወንዝም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ፡፡ የሚገርመው ነገር የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሸለቆው የተፈጠረው ከቤተ ክርስቲያኑ በታች መሆኑ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ ግን ጸንቶ ቆመ፡፡ መጋቢውም እግዚአብሔርንና ቅዱስ ሚካኤልን አመሰገነ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ፡፡ በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው፣ መልአኩንም አከበሩት፣ አሕዛብ ግን አፈሩ፡፡

ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያስገዙ ገዳማውያንና ቅዱሳን ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
4,8600024
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

10 de set. de 2026, 16:46

"መንግስት ከፋኖ እግር ስር ወድቆም ቢሆን እርቅ ያውርድ!" — ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ

በአገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲወርድ ከተፈለገ መንግስት እስከ መጨረሻው ዝቅ ብሎ ''ከፋኖ እግር ስር ወድቆም'' ቢሆን አስቸኳይ እርቅ ሊፈፅም እንደሚገባ አስገንዝበዋል። 

ሌላው ነገር ሁሉ ቀላልና ሁለተኛ ደረጃ ነው ሲሉ የቀድሞው ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ ተናግረዋል።

በሻዕብያ እና በህወሓት መካከል የሚታየው ጊዜያዊ የፖለቲካ ፍቅር 15 ቀን እንኳ የሚዘልቅ አይደለም። 

መሰረታዊውን የፋኖን ጥያቄና ሀይል ወደ ጎን ብሎ የሚደረግ ማንኛውም አይነት ስምምነትም ሆነ ህብረት የትም ሊደርስ አይችልም ብለዋል።''

ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ጥይት ስትተኩሱ ክርስቲያኖች በስመአም፣ መስሊሞች ቢስሚላህ እያላቸው ተኩሱ በሚለው ምክራቸው ይታወሳሉ።
4,2100036
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

10 de set. de 2026, 16:46

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏

በመጽሐፍ ቅዱስ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ያህል ትንቢት የተነገረላት ስለእርሷ የተጻፈላት ሴት የለችም። በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ብዙ ምሳሌዎች ተጠቅሰዋል፤ የኖኅ መርከብ፣ ሰላማዊት ርግብ፣ የአብርሃም ድንኳን፣ ሙሴ በሲና ያያት ሐመልማል፣ ጽላተ ሙሴ፣ የኢያሱ የምስክርነት ሐውልት፣ የኤልያስ የወርቅ መሶብ፣ የአሮን በትረ፣ የጌዴዎን ፀምር፣ የኖኅ የቃል ኪዳኑ ቀስተ ደመና፣ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት መሰላል፣ የነቢዩ ኤልሳዕ ማሰሮና ሌሎች ምሳሌዎች በሰፊው የተነገሩላት የተጻፉላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ቤተ ክርስቲያን እርስዋን ለመጥራት የምትጠቀምባቸው ቅጽል ስሞቿና ውዳሴዎቿ ምንኛ ድንቅ ቢሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ገላጭነት በቅዱሳን የተነገሩ ምስጋናዎቿስ እጅግ ቢለዩ የክብሯን ያህል የሚገልጿት አይደሉም፡፡    

እርሷ የሰው ሁሉ ረዳትና ርኅሩኅ እናት ናት፤ የብርሃን፣ የምሕረት፣ የድኅነትና የአማናዊው ወይን እናት ናት። ከንጉሡ በስተቀኝ የምትቆመው ንግሥት እርስዋ ናት፤ በመስቀል ስር የተቀበልናት የሁላችንም እናት እርሷ ናት፤ እርሷ ዘለዓለማዊ ድንግል ናት፤ እርሷ የእግዚአብሔር ጸጋ የሞላባት ንጽሕት ቅድስት ድንግል ናት፡፡ ከፍጥረት ሁሉ ተለይታ ወላዲተ አምላክ ለመሆን የተመረጠችበት አንዱ ምክንያት እመቤታችን እጅግ ትሑት፣ ፍጽምትና ንጽሕት ስለሆነች ነው። በሉቃስ 1÷48 እንደተጻፈው የአምላክ እናት እንደምትሆን ተነግሯት እንኳን ክብር ይግባትና ከመኩራትና ሌሎችን ከመናቅ ይልቅ ዘመዷ ኤልሳቤጥን ልትጠይቃት ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ወጣች፡፡ ከኤልሳቤጥ ፍጹም ምስጋናና በማሕጸን ያለው ዮሐንስ የሰላምታ ድምጿን ሰምቶ መዝለሉንከሰማች በኋላም “የባሪያይቱን መዋረድ ተመልክቷልና” በማለት በትሕትና ምስጋናዋን አቀረበች እንጂ የትዕቢት ቃል ከአፏ አልወጣም፡፡

ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ “እርሷ በእግዚአብሔር ዓይን በታየ የቅድስና ውበት የተሞላች ነበረችና በእርሷ ንጹሕ ማሕፀን ሊያድር ወደደ፤ እንደ ድንግል ማርያም ራሱን ዝቅ ያደረገ ትሑት ማንም የለም” ይላል። ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም “በትሕትና የተናገርሽ ተራራ ሆይ…” ብሎ ያመሰገናት ይህች ድንግል ከተራሮች አናት ሁሉ ከፍ ያለች ስትሆን ራሷን ዝቅ አድርጋ “እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንደምን ይደረግልኛል” የሚል ምላሽ ለቅዱስ ገብርኤል ሰጠችው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ማርያም ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛው አምላክ ልጇ ነውና ማርልኝ ስትለው ምልጃዋ ፍጹም ነው፡፡ በእግዚአብሔር መመረጧ፣ ከሴቶች ሁሉ መለየቷ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆኗ ይህን ክብር አጎናጽፏታልና፡፡ ገዳማውያንም ይህን ልዩ እናትነቷንና ቅድስናዋን አምነው ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሯታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ 

262281132


የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921
3,9400016
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

10 de set. de 2026, 16:46

ቴስላ ያለ መሪ እና ፔዳል የሚሰራውን “ሳይበር ካብ” (Cybercab) የሮቦት ታክሲ አገልግሎት በይፋ አስጀመረ...

​የኤሎን መስክ ኩባንያ የሆነው ቴስላ, በዘመናዊ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተውን ሙሉ በሙሉ በራስ ሰር (Driverless) የሚንቀሳቀሰውን “ሳይበር ካብ” (Cybercab) የተሰኘውን የሮቦት ታክሲ አገልግሎት በአሜሪካ (ቴክሳስ ኦስቲን) በይፋ ሥራ አስጀምሯል።

​ቁልፍ መረጃዎች ፡-

​ዲዛይን እና አሰራር፡ ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) እና ካሜራዎች ብቻ የሚመራ ሲሆን፣ የመሪ መሽከርከሪያ (Steering Wheel) ወይም የፍሬን/አክሰለሬተር ፔዳሎች የሉትም።

​ምቾት እና አገልግሎት፡ ለሁለት ተሳፋሪዎች ብቻ የተነደፈ ሲሆን፣ ውስጡ እንደ ሰፊ መዝናኛ ላውንጅ የተዘጋጀ ግዙፍ የክትትል ስክሪን እና እጅግ ዘመናዊ የድምፅ አቀንቃኝ ተካትቶለታል። ተሳፋሪዎች በልዩ የሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት ታክሲውን ጠርተው መጠቀም ተጀምረዋል።

​የወደፊት ዕቅድ፡ ኤሎን መስክ የዚህ ተሽከርካሪ የሽያጭ ዋጋ ወደፊት ከ30,000 ዶላር በታች እንደሚሆን ገልፆዋል።
4,230009
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

10 de set. de 2026, 16:46

ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ ምልጃው እና ረድኤቱም አይለየን🙏

የተወለደው በገሊላ አውራጀ በቤተ ሳይዳ ነው፣ አባቱ ዘብዴዎስ ይባላል ገና በወጣትነቱ ዘመን ከወንድሙ ከያዕቆብ ጋር ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮ የጌታውን እግር ተከትሎ አድጓል ቅዱስ ዮሐንስ፡፡ ወልደ ዘብዴዎስ፣ ወልደ ነጎድጓድ፣ ነባቤ መለኮት /ታኦሎጎስ/፣ ቁጽረ ገጽ በመባል ይታወቃል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዩሐንስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን የመጀመሪያው ወጣት የመጨረሻው ሽማግሌ ሐዋርያ እሱ ነበር፡፡ የጌታ ደቀ መዝሙር ከመሆኑ በፊት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ከነበሩት አንዱ ነው፡፡ ለጌታችን ባሳየው ልዩ ቀረቤታና ፍቅር ምክንያት “ፍቁረ እግዚእ” የሚል ስያሜ አግኝቷል፡፡ ፍቅሩንና ታማኝነቱንም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ “እሱን ያገኘ ያገኘኛል” ብሎ ሳይፈራ ከመስቀሉ ስር በመዋል አስመስክሮአል፡፡

በዩሐንስ 19÷26 እንደተጻፈው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ በመጨረሻዋ ሰዓት ቅዱስ ዮሐንስን ሲያየው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን “እነኋት እናትህ ታጽናናህ” ብሎ ሰጥቶታል፡፡ እኛንም እመቤታችሁ እናታችሁ ቅድስት ድንግል ማርያም ናትና ታጽናናችሁ፣ ተስፋ አለኝታ ትሁናችሁ ማለቱ ነው፡፡ እርሷንም “እነሆ ልጅሽ፣ ይርዳሽ ያጽናናሽ” ብሎ ለእኛ ለክርስቲያኖችም በቅዱስ ዮሐንስ አማካኝነት ለእመቤታችን መስጠቱን እናያለን፡፡ እመቤታችን በቤተ ዮሐንስ እንደኖረች ሁሉ በልበ ምእመናንም አድራ በሃይማኖት የምታጸና፣ ምግባረ ሃይማኖትን፣ ሕገ ትሩፋትን የምታሰራ፣ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ክርስቶስ ድኀነተ ስጋንና ድኀነተ ነፍስን፣ በረከተ ስጋንና በረከተ ነፍስን የምታሰጠን መሆንዋን ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ጌታው ቃል እመቤታችንን ወደ ቤቱ ይዟት ሄደ ከእርሱ ጋርም አስራ አምስት ዓመት ተቀምጣለች፡፡ ሐዋርያው የጌታ ትንሣኤ በተነገረ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስን ቀድሞ ከመቃብረ ክርስቶስ እንዲገኝ ያደረገው የፍቅሩ ጽናት ነበር፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ የድንግልና ሕይወትም ረቂቁን ምስጢረ መለኮት ለማየት አስችሎታል፡፡ ምስጢረ ሥጋዌን አስተካክሎ አደላድሎ በመጻፍ አምልቶ አስፍቶ አስተምሯል፡፡ የፍቅረ እግዚአብሔርንና የፍቅረ ቢጽን ጠቃሚነት በስፋት ጽፏል፡፡ ሰማያትን ሰንጥቆ የሚበር ንስር፣ ልዑለ ስብከት፣ ምሥጢራትን የሚያይ ወንጌላዊ ዮሐንስ፣ ነገሩ ሁሉ በምስጢረ መለኮት የተቀመመ ነው፡፡ ገዳማውያንም ቅዱሳንን አብነት አድርገው ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ንቀው ይመንናሉና ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጸና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
4,1100017
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

10 de set. de 2026, 16:46

የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚከፍተው ቢሮ በነገው ዕለት ስራ ሊጀምር ነው።

በቢሮው ለመስተናገድ የሚሹ ኢትዮጵያውያን አስቀድመው ቀጠሮ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው አገልግሎቱ ገልጿል።

መቀመጫውን በአዲስ አበባ የሚያደርገው አዲሱ ቢሮ ለቪዛ ማመልከቻዎች ውሳኔ የሚሰጥ እንዳልሆነ የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

ሆኖም ቢሮው ኢትዮጵያውያን ለፍልሰት ማመልከቻዎቻቸው የሚያቀርቧቸውን ሰነዶች ትክክለኛነት የማረጋገጥ ስራን የሚያከናውን መሆኑን አገልግሎቱ አስገንዝቧል።

የተጠረጠሩ የሰነድ “ማጭበርበሮችን” የሚመረምሩት እና የቤተሰቦችን ዝምድና ለማረጋገጥ የዘረ-መል (DNA) ናሙናዎችን የሚሰበስቡት በአዲስ አበባ የሚከፈተው የአገልግሎቱ ቢሮ ሰራተኞች ይሆናሉ።

እነዚህ ስራዎች ከዚህ ቀደም ሲከናወኑ የነበረው፤ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት እንደነበር ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ጠቁሟል።

የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት “ወሳኝ የስራ ኃላፊነቶች” ያላቸውን እነዚህን ተግባራት፤ አዲሱ ቢሮ “በቀጥታ ለማከናወን የሚያስችለውን ልዩ ውክልና ይሰጠዋል” ተብሏል።
4,7000013
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

10 de set. de 2026, 16:46

እንኳን ለቅዱስ ሩፋኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏

ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲሆን፤ “ሩፋ” ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፡፡
ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በመጽሐፈ አክሲማሮስ “በራማ ሰማይ የሚገኘውን ሁለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚህም ረቂቅ የሆነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲሆኑ በራማ በሁለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ነገደ መናብርት የሚባሉትን ራማ በሚባለው ሰማይ የሚኖሩትን ነገደ መላእክት የሚመራቸው ናቸው፡፡ አባ ጊዮርጊስም በሰዓታቱ “ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ በሚበርቅ፣ በሚል ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ” ይላል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚህ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡” ይለናል፡፡ በመጽሐፈ ሄኖክ 6÷3 ላይም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ተብሏል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስም “በፊቱ የሚቆሙ የመላእክት ሰራዊትም ሁሉ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ የመላእክት አለቆችም ለማይታይ ለባለዚህ ስም ዘንበል ብለው ይሰግዳሉ፤ ዙፋኑን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ ዕጣንን የተመሉ የወርቅ ማዕጠንት በእጆቻቸው ያለ ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይኸውም የቅዱሳን ጸሎት ነው እስከ ዘላለሙ ሕያው በሆነው ፊት የሚቀበለው መሥዋዕት አድርገው ወደ ላይ ያሳርጋሉ” በማለት አስተምሯል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ፈታሔ ማኀፀን ወሰፋድል። መወለድ መንፈሳዊ። ወሐኪም ሰማያዊ ይባላል። የወላድ ማኀፀን እንዲፈታ በእግዚአብሔር ስለተሾመ አዋላጅ ብትኖርም ባትኖርም ቅዱስ ሩፋኤል በዚያ አይታጣም፡፡ በተለይ በባላገር ያሉ ሴቶች በምጥ ጊዜ ሁሉ መልክአ ሩፋኤል በአንገታቸው ያነግታሉ፣ ይጸልያሉ፣ የተጸለየበትንም ጸበል ይጠጣሉ፤ በፍጥነትም ይወልዳሉ። በየወሩ በ13 ቀን መታሰቢያ በዓሉ የሚከበር ሲሆን ጳጉሜ 3 ደግሞ ዓመታዊ በዓሉ ነው፡፡ የቅዱስ ሩፋኤል በረከትና ረድኤቱ አይለየን፤ ምልጃው ይጠብቀን፡፡ ገዳማውያንም ይህን ተራዳኢነቱን በመታመን ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሩታል፡፡ ገዳማቸውን በመደገፍና በዓታቸውን በማጽናት የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
4,4200019
ኢትዮ መረጃ - NEWS logo
ኢትዮ መረጃ - NEWS

10 de set. de 2026, 16:46

ቻይና ዓለም አቀፍ ቀዳሚ የሆነውን አእምሮን ከኮምፒውተር ጋር የሚያገናኝ ቴክኖሎጂ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቀደች

የቻይና ብሔራዊ የመድኃኒትና የሕክምና ምርቶች አስተዳደር NEO የተሰኘውን የሳንቲም ያህል መጠን ያለው አእምሮን ከኮምፒውተር ጋር የሚያገናኝ (BCI) ቴክኖሎጂ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቃድ ሰጥቷል።

በጽንግሁዋ ዩኒቨርሲቲ እና በኒውራክል ቴክኖሎጂ የተገነባው ይህ መሳሪያ፣ ከምርምር ማዕከላት ውጭ የሰዎችን የእንቅስቃሴ አቅም ለመመለስ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቃድ ያገኘ በዓለማችን የመጀመሪያው በአእምሮ ውስጥ የሚተከል ቴክኖሎጂ ሆኗል።

የኢሎን መስክ ኒውራሊንክ (Neuralink) አሁንም በሰው ልጅ ላይ በሚደረግ የሙከራ ደረጃ ላይ ብቻ የሚገኝ ሲሆን፣ NEO ግን ደህንነቱን ባስቀደመው ልዩ ዲዛይኑ ምክንያት በፍጥነት የንግድ ፈቃድ ማግኘት ችሏል።

መሳሪያው የአእምሮ ክፍሎችን ጥሶ ከመግባት ይልቅ ስምንት ሴንሰሮቹ ከአእምሮ ውጫዊ ሽፋን (dura mater) ላይ በደህና ሁኔታ የሚያርፉ በመሆናቸው የህብረህዋሳት ጉዳትንና ደም መፈሰስን በእጅጉ ይቀንሳል። ይህ ፈቃድ በፅኑ የአንገት አጥንትና የሕብረ-ሰstandard አደጋ ምክንያት ሙሉ በሙሉ የእጅና የእግር ሽባነት ለገጠማቸው ነገር ግን የተወሰነ የእጅ እንቅስቃሴ ላላቸው ከ18 እስከ 60 ዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ አዋቂዎች ብቻ የሚያገለግል ነው።

በ11 ሆስፒታሎች ውስጥ በተደረጉ የሕክምና ሙከራዎች፣ ስርዓቱ በቤት ውስጥ በአእምሮ እዘዛ ዕቃዎችን የመጨበጥ ድጋፍ በመስጠት 100 በመቶ ስኬት አስመዝግቧል።

ይህ ቴክኖሎጂ የሰዎችን የሃሳብ ፍላጎት በመተርጎም ከሮቦቲክ የእጅ ጓንት ጋር በማያያዝ፣ ታካሚዎች እንደ መብላትና መጠጣት ያሉ የዘወትር ተግባራቸውን በራሳቸው እንዲያከናውኑ አስችሏቸዋል።
4,5400015

Showing 30 of 80 posts

Avaliação

Login necessário

Frequently Asked Questions

Sobre o que é o canal Telegram ኢትዮ መረጃ - NEWS?+

ኢትዮ መረጃ - NEWS (@ethio_mereja_news) é um canal Telegram listado em Notícias e Jornais no tgdio. Ranking, avaliações, reviews e posts recentes para decidir antes de assinar. Atualmente lista cerca de 45.817 inscritos no tgdio.

Como entrar em ኢትዮ መረጃ - NEWS (@ethio_mereja_news) no Telegram?+

Abra o perfil no tgdio e use Join / Open in Telegram para assinar @ethio_mereja_news de graça.

ኢትዮ መረጃ - NEWS é um bom canal de Notícias e Jornais?+

No tgdio você pode ver avaliação, reviews, ranking e posts de ኢትዮ መረጃ - NEWS antes de entrar. Atualmente lista cerca de 45.817 inscritos no tgdio. Compare com canais similares de Notícias e Jornais.

Onde ver estatísticas e posts de ኢትዮ መረጃ - NEWS?+

No tgdio, abra @ethio_mereja_news para stats de inscritos, ranking, avaliações e posts. Use Stats para gráficos.