በተለያየ ምክንያት ጠፍቶ የነበረ የውስጥ አርበኛችን ይህንን መረጃ ይዞ ብቅ ብሏል። አራዊት ሰራዊቱ በተለይ በጎጃም ቀጠና አዲስ የውጊያ እቅድ አውጥቶ ለትግበራ በዝግጅት ላይ ይገኛል።
1) በምስራቅ ጎጃም ግንደወይን፣ መርጦለማርያም ያለውን የአፋብን ፋኖዎች ከየጁቤና ደብረኤሊያስ ካሉ የፋኖ ኃይሎች ጋር አለመግባባቶችን መፍጠር አቅደዋል፤ ለዚህም እነ አሳማው ማስረሻ እየሰሩ እንደሚገኙ ተነግሯል። አለመግባባቶችን ለመፍጠርም እንደምሳሌ በፋኖ አመራሮች መካከል "እገሌ ከገሌ ይበልጣል" የሚል ፉክክር መፍጠር፣ ስብሰባዎች ያለ ስምምነት እንዲያልቁ ማድረግ ወዘተ ይገኝበታል ተብሏል።
2) ሌላው "ለፋኖ የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት ስቦ መምታት" የሚል እቅድም አውጥተዋል። ለዚህ ከተመረጡ ቀጠናዎች ውስጥም ሰሜን ጎጃም ብራቃት 19ኪሜ ቀጠና ፋኖን ስቦ መቶ መቆጣጠር፣ ግንደወይን የሳሙኤል ክ/ጦር ማክሰም እና የሞጣ እና የ ግንደወይን ሙሉ ለሙሉ ነጻ ማውጣት፣ መርጦለማርያም መካነሰላም ቀጠና በተመሳሳይ ሁለት ተራራዎችን መቆጣጣር፣ ጮቄ ዙሪያ የቦቅላ፣ቁይ፣ጁቤ ዋብር ፋኖን በመሳብ ጮቄን መቆጣጠር፣ ወዘተ መሰል ዝርዝር እቅዶች ደርሰውናል። ለዚህ መፍትሔው አፋብን ከሚደርሱት የውጭ መረጃዎች ባሻገር፣ የእራሱን የደህንነት መዋቅር በማንቀሳቀስም ከእንቅስቃሴና ጥቃት በፊት መረጃ መሰብሰብና መተንተን ያስፈልጋል እንላለን።
3) ሌላው ደግሞ የፋኖ ስልጠና ቦታዎች ብለው ባሰቧቸው አካባቢዎች ለምሳሌ በቢቸና እና ደብረወርቅ አካባቢዎች የአየር ጥቃቶችን መፈፀም የሚል እቅድም ማውጣታቸው ተነግሯል።
የሆነው ሆኖ ይህ የተንኮታኮተ አራዊት ሰራዊት የሚያድነው ወይም የሚያፀናው የኦህዴድ ስርዓት አይኖርም፤ ነገሮች ወደ መቋጫው ተቃርበዋል።









